Wednesday, June 22, 2016

የቀድሞ አንድነት ም/ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ፕሬዚዳንት የነበሩትአቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ ብሩ ዲሞክራሲና ፍትህ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ሲታገሉ የነበሩ፣ በ1997ዓ.ም ከሌሎች የትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ቅንጅትን ወክለው የተወካዮች ም/ቤት አባል በመሆን የበኩላቸውን የተወጡ፣ እንዲሁም አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሲመሰረትም ከመሥራቾቹ አንዱ በመሆን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አቶ ብሩ ቢርመጂ ለነፃነት ለፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን የበኩላቸውን ሲወጡ የነበሩ ጠንካራ ታጋይ ነበሩ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለፍትህና ዲሞክራሲ ታጋይ ጉዋደኞቻቸው መጽናናትን ይስጣችሁ፡፡
የአቶ ብሩ ቢርመጅ የቀብር ስነስርዓት የሚፈፀመው ዛሬ ሰኔ 15/2008 ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መሆኑ መረጃው ለሌላቸው በማካፈል ተባበሩ፡፡ መኖሪያ ቤታቸው ገርጂ አካባቢ ወደ ፓርላማ ቤቶች መውረጃ በስተግራ በኩል በሚያስገበው መንገድ ሲሆን የቀበር ስዓቱም ዘጠኝ ሰዓት መሆኑ ከቤተሰቦች ተነግሯል፡፡ አስከሬኑ ከትግራይ ዛሬ ጠዋት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment