ከገለልተኛ ወገን ሰፊ የተጣራ መረጃ ባይገኝም የወያኔ ደጋፊዎች ጦርነት ኣለ ሲሉ የሻእቢያ መንግስትም ጦርነት መኖሩን ኣምኖ በጾረና ግንባር በኩል ወያኔ ጦርነት ከፍቶብኛል ሲል መክሰሱን ቢቢሲ ዘግቧል። ወያኔ ሻእቢያን ፡ ሻእቢያ ወያኔን ተንኳሽ እያሉ እርስበርስ እየተወነጃጀሉ ነው።ከዛላምበሳ ጾረና ግንባር የሚላኩ መረጃዎች ወደ መከላከያ ሚኒስቴር አንዳይላኩ የተደረጉ ሲሆን የግንባሩ ግንኙነት ቀጥታ መቀሌ ከሚገኘው የሃይል ማዛዣ ጋር ብቻ አንደሆነ ከመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ጄነራሎች መረጃ ለማግኘት የተደረገ ሙከራ ያመለክታል።
የጦርነቱ ኣላማ ምን እንደሆነ ባይታወቅም መተነኳኮሱ ምናልባት በሁለቱ ሃገሮች ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት ለማድበስበስ የተሸረበ ሴራ ሊሆን ይችላል የሚሉ ኣስተያየቶች በመድመጥ ላይ ነው፤ ጦርነት እንዳለ በሁለቱም ኣገሮች ቅድመ መግለጫ ወጥቷል ኣፍቃሪ ሻእብያዎች ግን ምንም እንዳልተከሰተ በመናገር ላይ ይገኛሉ፤ ወያኔ ወጣቱን ለማስፈጀት አና በሃገር ውስጥ ያለውን ትኩሳት ለማስተንፈስ የፈጠረው ችግር ቢሆንም በወያኔ ኣገዛዝ ላይ ሕዝቡ እምነት ስላሌለው አንዲሁም ሰራዊቱ ለውጊያ ያለው ስነ ልቡና የወረደ በመሆኑ ጦርነቱን ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ያቆማል የሚሉ መረጃዎች ተሰምተዋል፤ በኣሁን ወቅት ለሶስተኛ ቀን ጦርነቱ ጋብ እያለ እየጋለ እየተካሄደ ሲሆን ተመጣጣኝ መረጃዎችን ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶች ቀጥልዋል።
No comments:
Post a Comment