Thursday, June 23, 2016

በሻሸመኔ ወንጀለኞች ታስረዋል ቢባልም ወንጀሉ ግን እንደቀጠለ ነው። By Minilik Salsawi


ባለፈው ሳምንት በሻሸመኔ ከተማ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ወንጀለኞች ተብለው የተያዙ ሰዎች ካለምንም ምርመራ ከ23 ኣመት እስከ እድሜ ልክ ድረስ የተፈረደባቸው ቢሆንም ኣሁንም ወንጀሎች መቀጠላቸውን የከተማው ነዋሪዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።እነዚህ ግለሰቦች ታስረው ከተያዙ እንኳን በፊት በተፈፀመው መልኩ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች በከተማዋ ተወግተዋል።
ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው ስማቸው የተዘረዘሩትና ተይዘው የታሰሩት ግለሰቦች በከተማዋ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው እራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ድሆች ናቸው።
፩። ተስፋዬ በቀለ ወልደየስ ፡ በእድሜ ልክ እስራት
፪። እዮብ ዋዳ ዋለልዬ ፡ በእድሜ ልክ እስራት
፫ ጌታሁን ሙሉጌታ መንግሥቱ ፡ በእድሜ ልክ እስራት
፬ እሸቱ ታደስ ለማ ፡ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት
፭። ጠንክር ጀሊላ ጎቶሮ ፡ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
እነዚህ ግለሰቦች ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው ትክክለኛ የምርመራ ሂደት ሳይከናወን እስራት ተፈርዶባቸዋል። እውነትም እነዚህ ሰዎች ወንጀሉን ፈፅመውት ከሆነ ህዝቡ በግልፅ ሊያየው በሚችል መልኩ አግባብ ያለው ምርመራ ተደርጎባቸው፤ አስፈላጊው የሰውና የቴክኒክ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለምን አልተፈረደባቸውም።
እንዚህ ግለሰቦች ታስረው ከተያዙ እንኳን በፊት በተፈፀመው መልኩ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች በከተማዋ ተወግተዋል። ወያኔዎች በድራማዊ ቅንብራቸው ሊያታልሉን እንደሞከሩት የወንጀሉ ፈፃሚዎች ታስረው ፍርድ ከተሰጠባቸው ዳግም የሻሸመኔን ህዝብ እያደነ የሚገኘው አካል ማን ይሆን፧ በርግጥ ታስረው ከተፈረደባቸው መካከል በወንጀሉ ውስጥ ሚና ያላቸው ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን እነዚህ ግለሰቦች ታስረው ፍርድ ተሰቷቸዋል እየተባለ ወንጀሉ መቀጠሉ አሁንም ቢሆን የወንጀሉ ትክከለኛ ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላት አዳዲስ ግለሰቦችን በማሰማራት በነፃነት ህዝቡን እያጠቁ መሆኑን ነው።

No comments:

Post a Comment