Tuesday, June 28, 2016

በኢሳት ሪዲዮና ቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ የሽብር ድርጊት አለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ ሰጠ


ፍርድ ቤቱ በእነ መቶ ኣለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ብይን ሰጠ !
“በኢሳት ሪዲዮና ቴሊቪን ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ የሽብር ድርጊት
አለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ ሰጠ”
በእነ መቶ ኣለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ስር የሚገኙ 16 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጠ። ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት በእነመቶ-አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ስር በሚገኙ ተከሳሾች ላይ ብይን የተሰጠ ሲሆን ፤ በ5ኛ ተካሽሽ አቶ ዘሪሁን በሬ ፣በ6ኛ ተካሳሽ አቶ ወርቅየ ምስጋናው እና በ7ኛ ተከሳሽ አቶ አማረ መስፍን ላይ የቀረበው ክስ፤ አቃቤ ሕግ በበቂ ሁኔታ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በተከሰሱበት ወንጀል ያስረዳ ባለመሆኑ ሦስቱ ተከሳሾች ፤በተከሰሱበት ክስ መከላከል የማይሰፈልጋቸው በመሆኑ ፍረድ ቤቱ ከተከሰሱበት ክስ ነፃ ናችሁ ብላቸዋል፡፡
በእነ-መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙት 13ቱ ተከሳሾች ማለትም፡-1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን ፣2ኛ በላይነህ ሲሳይ፣ 3ኛ አለባቸው ማሞ፣ 4ኛ አወቀ ሞኝሆዴ ፣8ኛ ተስፋየ ታሪኩ፣ 9ኛ ቢሆነኝ አለነ ፣10ኛ ተፈሪ ፈንታሁን ፣11ኛ ፈረጀ ሙሉ፣ 12ኛ አትርሳው አስቻለው ፣13ኛ እንግዳው ቃኘው ፣14ኛ አንጋው ተገኘ ፣15ኛ አግባው ሰጠኝ እና16ኛ አባይ ዘውዱ ፣ በተከሰሱበት ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡
በእነ-መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የሚገኙት አብዛኛው ተከሳሾች፣ አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ማስረጃ ከኢሳት ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ማለትም መሳይ መኮንን ፣ፋሲል የኔአለም እና ወንድምአገኝ ጋሹ ጋር በተለያየ ወቅት ቃለ መጠይቅ ማድረጋቸው በማስረጃ ዝርዝር ወስጥ ተካቶ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ “በአገሪቷ የበሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ ኢሳት አይገኝበትም፡፡ በእርግጥ ኢሳት የተባለው ጣቢያ የሽብር ድርጅት አቋም እና መልዕክት የሚተላለፍበት ቢሆንም፣ ጣቢያው በራሱ የሽብር ድርጅት ነው ማለት የሚያስችል ምን አይነት የህግ አግባብ የለውም በማለት ፍርድ ቤቱ ከኢሳት ጋር ተያይዞ የቀረበውን ማስረጃ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ይሁን እንጂ 15ኛ ተከሳሽ አቶ አግባው ሰጠኝ “ቀኑ በትክክል ተለይቶ ባልታወቀ በጥር እና በየካቲት ወር 2006 ዓ.ም ከኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን፣ እያሰረና እያሰቃየ በመሆኑ በሰላማዊ መንገድ መታገል አይቻልም” በማለት ቃለ መጠይቅ በማድረጉ በቀረበበት ክስ እንዲከላከል ፍርድ ቤቱ የወሰነበት ሲሆን፤ ለብይኑ መነሻ ያደረገውም “በሰላማዊ መንገድ መታገል አይቻልም” የሚለው አረፍተ ነገር “በሕገመንግስቱ የተደነገገውን በሰላማዊ መንገድ የመደራጀትና ሃሳብን የመግለፅ መብትን የሚፃረር ነው” በማለት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በ13ቱ ተከሳሾች ላይ የመከላኪያ መስክር ለመስማት ለነሐሴ 18፣19 እና 20 ቀጠሮ ይዟል፡፡
Yidnekachew Kebede's photo.
L

No comments:

Post a Comment