Wednesday, June 1, 2016

የሱዳን መንግሥት 442 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው አባረረ * የግድቡ ሥራ 70 ከመቶ ተጠናቋል በማለት የወያኔው ባለሥልጣን ሀሰት ዜና አሰራጨ – (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

የግንቦት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (May 31, 2016 NEWS)
#የግድቡ ሥራ 70 ከመቶ ተጠናቋል በማለት የወያኔው ባለሥልጣን ሀሰት ዜና አሰራጨ
#የኢትዮጵያ ፖሊቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ላለፉት 25 ዓመታት ወያኔ ሲያካሄድ የቆየውን የመብት ረገጣ አወገዘ
#የአገር ውስጥ ሴኩርቲ ኃላፊ የነበረውን ግለስብ ለመፍታት ስምምነት ተደረሰ
#የወያኔና የሱዳን ባለሥልጣናት በፖርት ሱዳን ስብሰባ አካሄዱ
#የሱዳን መንግሥት 442 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው አባረረ
#የቀድሞ የአቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት ባለቤት በሰው ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀረቡ
#የግብጽ የጋዜጠኞች ማህበር መሪ ከሁለት ባልደረቦቻቸው ጋር ታሰሩ
#በደቡብ ናይጄሪያ ከአማጽያን በተካሄደ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ሞቱ
አባይ ላይ ይሰራል የሚባለው ግድብ በግብጽና በወያኔ መሀል እንደገና ንትርክን የቀሰቀሰ ሲሆን ሀሰት ዜናዎችን ማሰራጨት ሥራው የሆነው የወያኔ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ደግሞ የግድቡ ሥራ ሰባ በመቶ ተጠናቋል ሲል መዋሸቱም ተጋለጠ። የግድቡ ሥራ በወያኔ ባለሥልጣናት ሙስና ማለትም የሜቲክ ሀላፊ ጄኔራል ክንፈ የግድቡን ትላልቅ ተርባይኖች ማሰራት በሚመለከት በፈጠረው ዕንቅፋት ያልቅበታል ከተባለው ዓመት ለሁለት ዓመት እንዲዘገይ መደረጉን የገለጹ ክፍሎች፣ ግድቡ 70 በመቶ ተጠናቋል የሚለው ሀሰት ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ትገኛለች የተባለችው አዜብ ጎላም ትልቅ ልጇን ሳሊኒ እንዲቀጥርላት ጫና እያደረገች መሆንዋ ተሰምቷል፤
የወያኔ አመራር አባል ሆኖ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ሁሉ አንደኛው ተጠያቂ የሆነው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን በዓለም የጤና ድርጅት ሀላፊነት ለማሾም ወያኔ በአፍሪካ ሀገሮች ከፍተኛና በገንዘብም የታጀበ ቅስቀሳ እያካሄደ ሲሆን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ግን ይህን በመቃወም እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ደብዛው የሚታይ አይደለም ሲሉ ታዛቢዎች ተቹ።

No comments:

Post a Comment