ትራምፕ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ያቀኑበት ምስጢር ምንድን ነዉ? እስከ 400 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት ያደረጉት አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ የ110 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭን ተስማምተዋል። የባህረ ሰላጤዉ አገራት የአሰብን ወደብ በመከራየታቸዉ፣በጅቡቲና በሶማሊያ ወደብም የሚገለገሉ በመሆናቸዉ ሒደቱን ኢትዮጵያዉያንን አትኩሮት ሊሰጡት ይገባል የሚል ምልከታ አለ። ሳኡዲ አረቢያ ሽብር መፈጠራን ለመከላከል ልክ እንደ ኔቶ የ34 የሙስሊም አገራት ህበረ-ጦርን አቋቁማለች። ኔቶን “ግዜ ያለፈበት!” በማለት ቀደም ሲል ያጣጣሉት ዶናልድ ትራምፕ ሳኡዲ አረቢያ ለምትመራዉ ህበረ-ጦር ይሁንታቸዉን የሰጡ ይመስላል።
ከኢትዮጵያ ጋር የአባይን ወንዝ የሚጋሩት ሱዳንንና ግብጽ የህብረ-ጦሩ አባላት ናቸዉ። ለኢትዮጵያ ወደብ የሚያከራዩት ሶማሊያ እና ጅቡቲም የህበረ-ጦሩ አባላት ናቸዉ።ወደቧን ለባህረ ሰላጤዉ እገራት ያከራየቸዉ ኤርትራ ህበረ-ጦሩን ስልታዊ ትብብር በማድረግ ትደግፋለች። በጥቅሉ አራት ከኢትዮጵያ ጋር ድንበር የሚጋሩ አገራት ከህበረ-ጦሩ የሚያገናኛቸዉ ነገር አለ። የትራምፕ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መሔድ ኢትዮጵያ ካለችበት መልከዓምድራዊ የፖለቲካ ሁናቴ ( Geopolitics) ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዉያኑ አትኩሮት በመስጠት ጉዳዩን ይከታተሉት ዘንድ ይመከራል። ልብ ያለዉ ልብ ይበል።
No comments:
Post a Comment