የሌላ ሀገር ዜጋን እየወደድን የሌላ ብሔር ተወላጅን እንጠላለን!
እስኪ አንድ ኢትዮጲያዊን ዝም ብላችሁ ታዘቡት። ወደ ቤተ-እምነት ሲሄድ “የሰው-ልጅ በአምላክ አምሳል የተፈጠረ ነው። ሰዎች እርስ-በእርስ ተዋደዱ፣ ጠላትህን እንደ ራስህ ውደድ፣…ወዘተ” የሚለውን ሃይማኖታዊ አስተምህሮት “አሜን” ይቀበላል። ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ደግሞ ስለ ሰው ልጆች እኩልነት ይማራል። በሁሉም የትምህርት ደረጃ የታሪክና የሲቪክ መማሪያ መፅሃፍት ውስጥ በጥቁር-አሜሪካዊያን ላይ ስለደረሰው ባርነትና የጉልበት ብዝበዛ፣ በአፓርታይድ አገዛዝ ወቅት በጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ ስለተፈፀመው የዘር መድሎና ጭቆና፣…ወዘተ በሰፊው ያስተምራሉ። የግል ሆነ የመንግስት ሚዲያ ተቋማት ዘወትር “ዘር-ቀለም ሳንለይል…” እያሉ ዘወትር ይዘምራሉ።
አብዛኛው ኢትዮጲያዊ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የቀድሞ ታሪክ ወይም ወቅታዊ ፖለቲካ በሰዎች ላይ ስለሚፈፀም የዘረኝነት መድልዎና መገለል፣ አስተዳደራዊ በደልና ጭቆና፣ ፖለቲካዊ እስራትና ግድያ፣…ወዘተ በየሚዲያው ይሰማል፣ በየትምህርት ቤቱ ይማራል፣ እርስ-በእርሱ ይወያያል፣ በጋራ ያወግዛል። በጦርነቶች ወይም በሽብር ጥቃቶች በሰዎች ላይ የሞትና አካል ጉዳቶች ሲደርሱ ሰብዓዊ ርህራሄ ይሰማዋል። ከማንም ቀድሞ ለተጎዱ ወገኖች የተሰማውን “ጥልቅ ሃዘን” በይፋ ይገልፃል።
ከዚህ በተጨማሪ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ በሀገሪቱ የቀድሞ ታሪክ ወይም በወቅታዊ ፖለቲካ አማካኝነት በዜጎች ላይ ስለተፈፀሙ በደሎች፣ ጭቆናዎች፣ አድልዎች፣ ግድያና እስራቶች ከቤተሰብ ወይም ከቅርብ ወዳጆቹ ጋር በግልፅ ይነጋገራል፥ ይወያያል፣ ይግባባል። በሌሎች ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ታሪካዊና ፖለቲካዊ በደሎችና ጭቆናዎች በቤተሰቡ አባላት ወይም በወዳጆቹ ላይ እንዲፈፀም አይሻም።
እስካሁን ድረስ እንደተመለከትነው፣ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ ለእሱ ቅርብ ከሆኑት የቤተሰብ አባላት ወይም ወዳጆች እና ሩቅ ካሉት የሌላ ሀገር ዜጎች ጋር ያለው ግንኙነትና አመለካከት በዋናነት በበጎ አመለካከትና በሰብዓዊነት የታነፀ ነው። ነገር ግን፣ ስለ ራሱ ሀገር የቀድሞ ታሪክና ወቅታዊ ፖለቲካ ውይይት ሲጀምር በአንድ ግዜ አቅሉን ይስታል። ስለኢትዮጲያ የቀድሞ ታሪክ ሆነ አሁን ስላለው ፖለቲካዊ ስርዓት የሚደረገው ውይይት ወዲያው “አማራ፣ ኦሮሞ፣ “ትግሬ”፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሱማሌ፣….” እየተባባሉ መደናቆር ይጀመራል።
ታሪካዊ በደልና ጭቆና ወይም ፖለቲካዊ እስራትና ሞት በሌላ ሀገር ዜጋ ወይም በቤተሰባችን አባል ላይ ሲደርስ የነበረን ሰብዓዊነት እዚሁ ለሌላ ብሔር ተወላጅ የሀገራችን ዜጎች ሲሆን ከውስጣችን እንደ ጉም በኖ ይጠፋል። ለውጪ ሀገር ዜጋ የነበረን ሰብዓዊ አመለካከት ለሌላ ብሄር ተወላጅ ሲሆን ወደ ፖለቲካ ይቀየራል።
ለምሳሌ፣ ባለፈው አመት አንድ ወዳጄ “በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ብሔር ተወላጆች ከመኖሪያ ቄያቸው ተፈናቀሉ” በሚል አምርሮ ሲቃወም ነበር። በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት መሰረት በአማራ፣ ኦሮሚያና በደቡብ ክልል ከአራት ወር ባነሰ ግዜ ውስጥ 669 ሰዎች መገደላቸው ስነግረው “እነዚህ ፋብሪካ ለማቃጠል የወጡ ወንጀለኞች ናቸው” አለኝ። ይሄው ሰው ግን፣ ባለፈው በለንደን ከተማ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት አንዲት የፓርላማ አባል መገደሏን እንደሰማ ጥቃቱን በማውገዝ ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ሲገልፅ ማንም አልቀደመውም። ታዲያ ይህ ወዳጄ ለውጪ ሀገር ዜጋ የነበረውን ሰብዓዊ አመለካከት ለሌላ ብሔር ተወላጅ ሲሆን በአንዴ ወደ ፖለቲካ ለምን ቀየረ?
በተመሣሣይ ስለ ሀገራችን የቀድሞ ታሪክና ወቅታዊ ፖለቲካ ሁኔታ ከውጪ ሀገር ዜጎች ጋር መወያያት እየቻልን የሌላ ብሔር ተወላጅ ከሆነ ኢትዮጲያዊ ዜጋ ጋር ግን መግባባት ቀርቶ መደማመጥ አንኳን አይቻልም። ለምሳሌ፣ ባለፈው ሳምንት ከአንድ ኢጣሊያናዊትና ኤርትራዊት ጋር ለመወያያት እድሉ ገጥሞኝ ነበር። ከኢጣላናዊቷ ጋር ስለ አደዋ ጦርነትና አፄ ሚኒሊክ በመግባባት ላይ የተመሰረተ ውይይት አድረገን። በተመሣሣይ፣ ከኤርትራዊቷ ጋር በኤርትራና በኢትዮጲያ ስላለው ፖለቲካዊ ሁኔታ በግልፅ ተወያየን። ወደ ሀገሬ ስመጣ ግን ስለ ኢትዮጲያ የቀድሞ ታሪክ ሆነ ስለ ወቅታዊ ፖለቲካ በግልፅ መወያያት አይቻልም። ስለ አደዋና አፄ ሚኒሊክ ከኢጣሊያን ዜጋ ጋር መወያያት ከቻልኩ ከአንድ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር መወያያትና መግባባት የሚሳነኝ ለምንድነው? ከኤርትራዊቷ ጋር ያደረኩትን ግልፅ ውይይት ከአንድ የትግራይ ተወላጅ ጋር ማድረግ የሚከብደኝ ለምንድነው? ከሌላ ሀገር ዜጋ የነበረን ግልፅ ውይይት ከሌላ ብሔር ተወላጅ ጋር ሲሆን በጭፍን ጥላቻ መደናቆር የሚሆነው ለምንድነው?
በአጠቃላይ፣ ከሌላ ሀገር ዜጋ ጋር በግልፅ እየተወያየን ከሌላ ብሔር ተወላጅ ጋር እንኮራረፋለን። ለሌላ ሀገር ዜጋ የነበረን ስብዓዊነት ለሌላ ብሔር ተወላጅ ሲሆን ፖለቲካ ይሆናል። የሌላ ሀገር ዜጋን እየወደድን የሌላ ብሔር ተወላጅን እንጠላለን። በቤተሰባችን አባላት ላይ ቀርቶ በሌላ ሀገር ዜጋ ላይ እንኳን እንዲደርስ የማንፈልገውን መጥፎ ነገር በሌላ ብሔር ተወላጅ ላይ ለማድረስ እንዝታለን። ለመሆኑ ለኢትዮጲያዊ ከሌላ ሀገር ዜጋ እና ከሀገሩ ልጅ ማን ይቀርበዋል?
የ“እኛ” እና “እነሱ” ፖለቲካ፡ ከሰብዓዊነት እስከ አውሬነት
የሰው-ልጅ እርስ-በእርሱ የሚያደርገው ማህበራዊ ግንኙነት እና አንቅስቃሴ በዋናነት “እኛ” እና “እነሱ” በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። በቋንቋ አጠቃቀማችን እና ትምህርት አሰጣጣችን መሰረት እያንዳንዱ ሰው ራሱን “እኛ” በሚል የቡድን እሳቤ ውስጥ ነው የሚመለከተው። ሌሎችን ደግሞ “እነሱ” በሚል የተፃራሪ ቡድን አባል አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለ። ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህ “እኛ” እና “እነሱ” የሚለው እሳቤ እንደ ሁኔታ የሚለያይ ነው። ለምሳሌ፣ “እኛ” ኢትዮጲያዊያን ከሆንን “እነሱ” ኢጣሊያዊያን፣ እንግሊዛዊያን፣ ኤርትራዊያን፣…ወዘተ፤ “እኛ” ኦሮሞ ከሆንን “እነሱ” አማራ፣ “ትግሬ”፣ ጉራጌ፣…ወዘተ፤ “እኛ” የአበበ ቤተሰቦች ከሆንን “እነሱ” የጫላ ቤተሰቦች፣ የሃጎስ ቤተሰቦች፣…ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። በአጠቃላይ፣ “እኛ” እና “እነሱ” የሚለውን እሳቤ እንደ ሁኔታው በቤተሰብ፣ ብሔርና ሀገር ደረጃ ከፋፍሎ ማየት ይቻላል።
በሦስቱም ደረጃ “እኛ” እና “እነሱ” የሚለው አመለካከት የሚወሰነው በመካከላችን ካለው ግንኙነት አንፃር ነው። በዚህ መሰረት፣ ለአንድ ኢትዮጲያዊ የኢጣሊያኖችን ሃሳብና እንቅስቃሴ ማወቅና መገመት ከባድ ነው። ነገር ግን፣ የሁለቱ ሀገር ዜጎች በኢትዮጲያዊው ማህበራዊ ሕይወትና የዕለት-ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ውስን ነው። የኦሮሞዎች ሕይወት ከሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሃሳብና እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘ ስለሆነ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ ስለ አማራ፣ ትግራይ ወይም ጉራጌ ብሔር ተወላጆች ሃሳብና እንቅስቃሴ ማወቅና መገመት ይፈልጋል። ይሁን እንጂ፣ ሁሉም የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ከማንም በፊት የቤተሰቡንና የቅርብ ወዳጆቹን ሃሳብና እንቅስቃሴ በትክክል ማወቅና መገመት አለበት።
እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ በሕይወቱ ውስጥ ቀጥተኛ ግንኘነትና ተፅዕኖ ስላላቸው ቤተሰቦቹና የቅርብ ወዳጆቹ ሃሳብና እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት ማወቅ ይችላል። እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ የቤተሰቡ አባላት ወይም የቅርብ ወዳጆቹ ከሆኑት “እነሱዎች” ጋር በቃላሉ መነጋገርና መግባባት ይችላል። ማህበራዊ ግንኙነቱም በውይይትና ሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ነገር ግን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ስለ ሌላ ሀገር ዜጎች ሃሳብና እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም። ይሁን እንጂ፣ የውጪ ሀገር ዜጎች ከእሱ ጋር ያላቸው ግንኙነትና በዕለት-ከእለት ሕይወቱ ውስጥ ያላቸው ተፅዕኖ ውስን ነው። ስለዚህ፣ ሩቅ ያሉ የሌላ ሀገር ዜጎች “እነሱዎች” ጥሩ ሥራና ምግባር እንዳላቸው ይገምታል።
“Edmund Leach” የተባለው ምሁር፣ ቅርብ ባሉት “እነሱዎች” እና ሩቅ ባሉት “እነሱዎች” መካከል ሌላ ሦስተኛ “እነሱዎች” እንዳሉ ይገልፃል። እንደ እሱ አገላለፅ፣ ብዙውን ግዜ ሰዎች ስለ ከሦስተኛው “እነሱዎች” ጋር ያላቸው ግንኙነት በውይይት ላይ ያልተመሰረተና ለሌሎች ያላቸው አመለካከት ሰብዓዊነት የጎደለው ነው፡-
“But lying in between the remote Heavenly other and the close predictable other there is a third category which arouses quite a different kind of emotion. This is the other which is close at hand but unreliable. If anything in my immediate vicinity is out of my control, that thing becomes a source of fear. This is true of persons as well as objects. If Mr X is someone with whom I cannot communicate, then he is out of my control, and I begin to treat him as a wild animal rather than a fellow human being. He becomes a brute. His presence then generates anxiety, but his Jack of humanity releases me from all moral restraint: the triggered responses which might deter me from violence against my own kind no longer apply.” REITH LECTURES 1967: A Runaway World, Lecture 3: Ourselves and Others: 26 November 1967 – Radio 4ከውጪ ሀገር ዜጋ ጋር በግልፅ መወያየትና መግባባት እንችላለን። ከእነሱ ጋር መወያየትና መግባባት ባንችል እንኳን የእነሱ ሃሳብና እንቅስቃሴ በእኛ ሕይወት ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ዝቅተኛ ስለሆነ ይህን ያህል አሳሳቢ አይደለም። ሆኖም ግን፣ በአንድ ሀገር ውስጥ አብረን እየኖርን እርስ-በእርስ መነጋገርና መግባባት ከተሳነን፤ የጠበቀ ማህበራዊ፥ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት እያለን አንዳችን የሌላችንን ሃሳብና እንቅስቃሴ ማወቅና መገመት ከተሳነን፣ እንደ ሰው ያለን ምክንያታዊ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊ አመለካከታችን ከውስጣችን ይጠፋል። ከቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን፣ ከጎጥ፣ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞንና ክልል ነዋሪዎች ጋራ የነበረን በውይይትና ምክንያታዊ ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ አመለካከት፣ እንደ ሰው የነበረው ሰብዓዊነት ለሌላ ክልል ነዋሪዎች ወይም ብሔር ተወላጆች ሲሆን ከውስጣችን ተሟጥጦ ይጠፋል።
የሌላ ሀገር ዜጋን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር እያየ፣ የሌላ ብሔር ተወላጅን ግን እንደ ዱር አውሬ አድኖ መግደል ይሻል። በእርግጥ ለአንዳንዶቻችሁ አገላለፁ በጣም የተጋነነ ሊመስላችሁ ይችላል። ነገር ግን፣ የራሱን ዝርያ እንደ አውሬ ወይም ጠላት አድኖ የሚገድል ፍጡር ቢኖር የሰው ልጅ ብቻ ነው። በጣም ውስን በሆኑ አጋጣሚዎች ካልሆነ በስተቀር ሌሎች እንስሳት የሚያድኑትና የሚገድሉት ሌላ የእንስሳት ዝርያን ነው። እንደ “Edmund Leach” አገላለፅ፣ የራሱን ዝርያ እንደ አውሬ ማደንና መግደል የሚሻው የሰው-ልጅ ብቻ ሲሆን ይህም
No comments:
Post a Comment