Sunday, May 7, 2017

‹‹ለዐማራ መኪና አንሰጥም፤ ከፈለግክ አስከሬንህን ፈርመህ ተሸክመህ ሒድ›› የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ዳይሬክተር

   


‹‹ለዐማራ መኪና አንሰጥም፤ ከፈለግክ አስከሬንህን ፈርመህ ተሸክመህ ሒድ›› የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ዳይሬክተር   – Branna Media

ሟች ወታደር ከተማ እንየው ይባላል፡፡ ትውልዱና እድገቱ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አባ ጨራ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነው፡፡ ከተማ እንየው የመከላከያ ሠራዊት አባል ሆኖ ሽሬ አካባቢ ካለ ክፍለ ጦር ነበር የሚኖረው፡፡
ወታደር ከተማ እንየው ከሦስት ሳምንታት በፊት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል የሞተበት ምክንያት ሳይታወቅ የቅርብ ዘመዱ ከሆስፒታሉ ተደውሎ ‹‹አስከሬንህን ውሰድ›› እንደተባለ ተናግሯል፡፡ ሽሬ ከነበረበት ካምፕ መታመሙንም ሆነ ለሪፈራል ወደ ጦር ኃይሎች መላኩን የከተማ እንየው የቅርብ ዘመዶችም ሆነ ጓደኞች አያውቁም ነበር፡፡
ሆኖም የሟች የቅርብ ዘመድ ከሆስፒታል ተደውሎ ጦር ኃይሎች ሲሔድ በአፍና በአፍንጫው ደም ይፈስ እንደነበርና የመሞቱ ምክንያትም በግልጽ እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ ከሆስፒታሉ ሠራተኞች ሕክምና ቢደረግለትም መትረፍ አለመቻሉን ብቻ ነው የገለጹለት፡፡
የሟች የቅርብ ዘመድ አስከሬን ለመውሰድ የሆስፒታሉን ኃላፊዎች አስከሬኑን የሚወስድበት መኪና ቢጠይቅም መከልከሉን ተናግሯል፡፡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሞቱ በክብር በራሳቸው መኪና ወስደው እንደሚያስረክቡ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም አስከሬን ለመቀበል የተደወለለት ዘመድ የተለያዩ ኃላፊዎች እንደማይሰጠው ሲነግሩት ለሆስፒታሉ ዳሬክተር ጥያቄውን በቀጥታ ሲያቀርብ ዳይሬክተሩ ከየት እንደመጣ ከጠየቁት በኋላ ‹‹ለአስከሬን መሸኛ መኪና ሰጥተን አናውቅም፤ ብንሰጥም ለዐማራ አሰከሬን መሸኛ መኪና አንሰጥም፤ ከፈለግክ ፈርመህ አስከሬንህን ተሸክመህ ሒድ›› ብለውታል፡፡
ሟች ወታደር ከተማ እንየው በትክክል ታሞ ነው የሞተው? ለምን ቤተሰብ መንገር አልተፈለገም? ከሞተ በኋላ ለምን ለቤተሰብ መንገር አስፈለገ? የሚሉትን ጥያቄዎች በትክክክ መልስ የሰጠ የመንግሥት አካል የለም

No comments:

Post a Comment