Sunday, May 28, 2017

የሲያትል ስብሰባ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወለደማሪያም እና ግንቦት 7 (ቬሮኒካ መላኩ)

May 28, 2017 17:48      




ማኔ ቴቄል ፋሬስ (በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ !) ትን. ዳንኤል ፭፡፳፭
የዛሬው ፅሁፌ የሚያጠነጥነው ሰሞኑን አሜሪካ ሲያትል ተደርጎ የነበረውን የተለያዩ “ድርጅቶችና “ግለሰቦች የተሳተፉበትን ስብሰባ ተከትሎ በሁለት ጉዳዮች ላይ ይሆናል ።
አንድ በፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ዙሪያ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ አርበኞች ግንቦት 7 በተባለው ድርጅት ላይ ይሆናል።
ከላይ እንደጠቀስኩት የዚህ ፅሁፍ ቆስቋሽ በሲያትል በውስጠ ታዋቂነት በግንቦት7 ዋና አስተባባሪነት የተጣመሩ ድርጅቶች ያዘጋጁት ስብሰባ ነው።
ለሳምንታት ይሄ ስብሰባ ከመደረጉ በፊት በማህበራዊ ድረገፅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ላይ የተሳታፊ ተጋባዥ እንግዶችን ስብጥር ስመለከት ቀድሞውንም ጥርጣሬ ነበረኝ። ይሄው እንደጠረጠርኩት አማራ ባልተጋበዘበትና ባልተሳተፈበት ስብሰባ ሲብጠለጠል ዋለ።
“ጨቋኟ አማራ ጠላታችን ነው!” ብሎ ደደቢት የገባው አረጋዊ በርሄ፣ “አማራ የሚባል ህዝብ የለም” ያለው ፕሮፌሰር መስፍን፣ የአርባጉጉና የበደኖ አርበኞች የተሳተፉበትና አማራ ያልተወከለበት ስብሰባ ከመሆኑ አንፃር የጉባኤውን ውጤት ቀድሞ መተንበይ የሚያስቸግር አልነበረም።
ፕሮፌሰር መስፍን ረጅም የህይወት ዘመናቸውን አወዛጋቢ ሆነው እንደኖሩ ብዙዎች ይስማማሉ። ቀኑ እየገፋ እየተዋገደ እና እየመሸ ሲመጣ “ኑዛዜ” ያደርጋሉ ብለን ስንጠብቅ አሁንም አወዛጋቢነታቸው ቀጥሏል።
እዚህ ላይ አንባቢ እንድገነዘብልኝ የምፈልገው ለአንድ ክፍለ ዘመን ትንሽ የቀረው አመታት የኖሩትን አረጋዊ “ለመዘርጠጥ” አስቤ የፃፍኩት እንዳይመስልብኝ ነው። ፕሮፌሰሩ አማኝ እንደሆኑ አውቃለሁኝ። ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ “የለም” ብለው የካዱትን ህዝብ ተፀፅተው ጥፋታቸውን በንስሃ ያጥባሉ ብዬ ስጠብቅ ጭራሽ ሌላ አጀንዳ ይዘው ብቅ አሉ።
በሌላ በኩል ኑዛዜ ማለቴ ምሁሩን ለመክሰስ ሳይሆን በአንድ ወቅት “ጠመንጃው ያለው በእጃችሁ ሆኖ ጊዜውም ሁኔታውም እየፈቀደላችሁ የኛን የብእር ብትር እንደት ትጠብቃላችሁ? መርማሪ ኮሚሽን ምናምን እያላችሁ ስታመነቱ በስፔን አቢዮት እንደደረሰው ጎርፉ እኛንም እናንተንም ጠራርጎ እንዳይወስድ አፈራለሁ።”
የሚል ወኔ ቀስቃሽ ንግግር ለደርግ አድርገዋል የሚል ክስ ከብዙ ሰዎች ስለተነሳባቸው እንደው ይሄን ጉዳይ በደንብ ቢያብራሩት ለማለት ነው።
ይሄ ነገር መንግስቱ ሃይለማሪያምም ተናገረው። ጠቅላይ ሚንስቲር የነበረው ፍቅረስላሴም ወግደረስም ደገመው፣ ምክትል ፕሬዚደንት የነበረው ፍስሃ ደስታም ሰለሰው። ፕሮፌሰሩም የትርጉም ልዩነት እንዳለው ነገሩን እንጅ የተባለውን ማለታቸውን አልካዱም።
“አውቄ በስህተት ሳላውቅ በድንቁርና የሰራሁት ሃጢያት ካለ ይደምሰስልኝ?” ማለት ባህላችን ነው። ቢያንስ እርምጃ ከተወሰደባቸው 90 በመቶ የሚሆኑት አማራ ናቸው በማለት ነው።
አሁን ይዘው የመጡት አጀንዳ ደሞ ” ማንነትን መስረቅ መመንተፍ” ነው። አርበኛው በላይ ዘለቀ “ኦሮሞ” ነው የሚል ነው።( https://www.youtube.com/watch?v=_uK66IcXfHs ) ይሄ ነገር ቆየት ያለ ነው። መጀመሪያ ተስፋዬ ገ/አብ ያለው መሰለኝ። ኦነጎቹ ዘፈን ዘፍነውበት ኢሳት ላይ ሰምቸዋለሁኝ። አሁን ፕሮፌሰሩ የተስፋዬ ገ/አብ ቃለአቀባይ ሆነው ቁጭ አሉ። ይሄ የበላይ ዘለቀ ማንነት ጉዳይ የግለሰብ ብቻ ሳይሆን ውስጡም ፖለቲካዊ ተንኮል አለበት። ለጊዜው ያን መግለፅ አልፈልግም።

No comments:

Post a Comment