Wednesday, May 10, 2017

ምስጋና ለዳግማዊ መዐሕድ- ቤት አማራ መድኅን ድርጅት (ከአደማሱ በጋሻው)


    

ለህዝብ የሚሰራ ድርጅት የህዝብን አስተያት እና ጥያቄ  ዋና ግብአት አድረጎ መጠቀሙ የግድ ነው፡፡ ምክንያቱም የሚሰራው ለህዝብ ነውና፡፡ህወሓት ትግሬ በአማራ ህዝብ ላይ  እየፈጸመ ያለውን ግፍ ለመመከት ብዙ የአማራ ድርጅቶች መፈጠራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የድርጅቶቹ መፈጥር ራስን ከጥፋት ለመከላከል ለምናደርገው የሞት ሽረት ጥርት የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡
ነገር ግን  ድርጅቶቹ የሚታገሉለት ዓላማ አንድ እስከ  ከሆነ ድረስ  ድርጅቶቹ በተለያየ ስያሜ መጠራታቸውና የሰውም ሆነ የገንዘብ አቅም  መሻማታቸው አግባብ አይደለም፡፡ በአንድ ብሄረ ስም የተለያዩ ድርጅቶች መኖር የሚያመለክተው መጠራጠርንና የዓለማ ልዩነትን ነው፡፡ ጥርጣሬ ባለበት ቦታ ሁሉ ደግሞ ጠንካራ ኃይል ሊፈጠር አይችልም፡፡ ይህም በአማራ ላይ ለረጅም ጊዜ ተቀነባብሮ ሲፈጸም የኖረውና እየተካሄደ ያለውን የህወሓት ትግሬ ፋሺሽታዊ ጭፍጨፋ እንዲቀጥል መፍቀድ  ይሆናል፡፡
ህወሓት ትግሬ  አማራ ታሪካዊ ጠላቴ  ነው ብሎ በይፋ አውጆ በረቀቀ ስልት አማራን  በሁሉም መስክ( በማህበራዊ፤ በፖሊቲካ፤ በኢኮኖሚ፤ በበባህል ፤ በሰው ኃይል፤ በመከላከያና በሌሎችም መስክ) ሽባ እያደርገ ባለበት ወቅት በጥቃቅን ልዩነቶች ተነሳስቶ የተለያዩ የአንድ ብሄረ ድርጅቶችን መፍጠር ለአማራ ህዝብ አለመቆርቆርን ከማመልክት ውጭ ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም፡፡
በርቀት የሚገኝው የህብረተሰቡ ክፍልም የአንድ ብሄር ብዙ ድርጅቶችን አላስፈላጊነት በማህባራዊ ሚዲያው በኩል ሲያስተጋባ ቆይቷል፤አንድ ጠንካራ ድርጅት እንዲፈጠርም  እየወተወት ይገኛል፡፡ ከሁለት ወር በፊት አካባቢ የቤት-አማራና የመድኀን ድርጅቶች በአንድ ተጣምረው ለመስራት መወሰናቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ሳነብ  በጣም   ነበር ድስታ  የተሰማኝ፤ ሌሎች ጓደኞቼም እንዲሁ ነበር ሰሜታቸው፡፡  አሁን ደግሞ ቤተ-አማራ መድኅን እና ዳግማዊ መዐሕድ  ለመዋህድ  በቅድመ ሁኔታዎች  ላይ  መስማማታቸውንና  እስከ ውህደቱ ድርስም የጋራ መጠሪያቸው ዳግማዊ መዓድ-ቤተ አማራ መድኅን  የሚል መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሳነብ እጅግ አስደሰተኝ፡፡ በእውነት የህዝብን ፍላጎት ተረድታችኋልና  ምስጋና ይገባችኋል፡፡  ይህም ደጋፊያችሁና ሁለንተናዊ አቅማችሁ እንዲጎለብት  ትልቅ አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡
አሁን ዳግማዊ መዓድ-ቤተ አማራ መድኅን ድርጅት በድርጅተዊ መግለጫው አንዳስታወቀው ሁሉ ከሌሎች የአማራ ድርጅቶች ጋር ውህደት ለመፍጠር ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ በተለይ ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት እና የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድንት ድርጅቶች ጋር ለውህደት ጠንክሮ ቢሰራና ለውጤት ቢበቃ የአማራ ህዝብ ትግል ወደ ድል ጎዳና እየገሰገሰ ለመሆኑ በቂ ምልክት ሊሆነን ይችላል፡፡ በተለይ በግንቦት 6/2009 ዓ.ም በዳግማዊ መዐሕድ አስተባባሪነት በሚካሄደው የመጀመሪያው የአማራ አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ጎልቶ መውጣት የሚኖርበት በአማራ ስም የተቋቋሙ የድርጅቶች የውህደት ጉዳይ ሊሆን ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡
በተጨማሪም ከፍለ ሀገር ተኮር ድርጅቶች ለምሳሌ ከጎንደር ኅብረትና ከጎጃም አለም አቀፍ ህብረት  ጋርም የቅርብ ውይይት ቢደረግ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ዘመኑ ተኩላ የበዛበት በመሆኑ በአማራ ስም ተደራጅቶ አማራን ለማጥቃት ግቡ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ሊኖር ይችላልና ከውህደት በፊት ስለ እያንዳንዱ በአማራ ስም የተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ድርጅት የአጭርና የረጅም ጊዜ ግቡን  እንዲሁም ድርጅቱን  የሚመሩ የሰዎች ማንነት በሚገባ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ከማንነት አንፃር የትውልድ ቦታ በቂ መመዘኛ ሊሆን አይችልም፡፡ የትውልድ በታ ወሳኝ ቢሆን ኑሮ አሁን ጎንደር ከተማን  እያፈረሰ የሚገኘው አቶ በረከት ስመዖን ተወልዶ ያደገው ጎንደር ከተማ ነበር፡፡
በሌላ ምስጋና እንገናኝ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

No comments:

Post a Comment