Sunday, May 14, 2017

ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!

   


የጫት ነገር!!
…. ጫት ሽንት ሽንት ስለሚል ረጅም መንገድ እንኳ አያስጉዝም፡፡ ደግሞ ያቃዣል፡፡ከዛ ዱካክ ይለቃል!!!!
ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!
የሺሃሳብ አበራ

ኢትዮጲያ ካላት 70 ሚሊየን ሄክታር የሚታረስ መሬት 7 % (500 ሺ ሄክታር ) በጫት ተሸፍኗል፡፡ከአፍሪካ ጅቡቲ፣ሶማሊያ ፣በከፊል ኬኒያ ጫት መቃም ህጋዊ የሆነባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ … የሶማሊያ ወታደር ጫት ሲቅም በአልሸባብ በራሱ መሳሪያ ይገደላል፡፡ጫት ለሶማሊያ አለመረጋጋት የራሱ አሉታዊ አስተዋፅኦ አለው፡፡ የየመንም እንደዚሁ፡፡በየመን 40% ውሃዋ ለጫት ይውላል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ግን በ 1972 ዓም ጫትን ጎጂ እፅ ብሎ ከፈረጀው በኋላ በአውሮፓ ና በአሜሪካ ተከልክሏል፡፡ የሙስሊም ሀገራት ሊቃውንት በሂጅራ የዘመን ስሌት በ 1402 5 ኛ ወር ላይ ከቀን 27-30 በተካሄደ ጉባኤ ጫት መቃም ተወግዟል፡፡ሀራም ሆኗል፡፡በሳውዲ፣በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
…… ጫት መቃም ወንጀል ነው፡፡ባለፈው ወር 20 ኢትዮጵያውያን ጫት ይዘው ተገኝተው በኩዌት እስርቤት ይገኛሉ፡፡
…….. በየመን በሄክታር ከጫት ገቢ 2.5ሚሊየን ዶላር በዓመት ገቢ ይገኛል፡፡እናም የየመን አርሶአደሮች ጫት አምራች ናቸው፡፡ግን ጫት ህዝቡን አደንዝዞ ዛሬ ላይ የመን የሞት ባድማ ሁናለች፡፡ …. ከወሎ ዮኒቨርሺቲ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው አማኑኤል ካሉ የአዕምሮ ሁሙማን መካከል 80% በጫት ና መሰል ሱሶች የታመሙ ናቸው፡፡ጫት የዕለት ምግብ እየሆነ ነው፡፡በ 2004 ዓ/ም ገቢዎች ና ጉምሩክ ባለስልጣን በጫት ላይ ተጨማሪ ታክስ 5% ጥሎ ነበር ፡፡ግን ተግባራዊ አልሆነም፡፡
… ዛሬ ላይ ጫት የጎጃምን ና የጎንደርን ማሳ ተቆጣጥሮታል፡፡ሀይ ባይ ካልተገኘ የፎገራ-ሩዝ፣ የጎንደር ሰሊጥ፣የጎጃም ጤፍ በጫት መተካቱ አይቀርም፡፡እንዲያውም ጣናም በጫት ተክል ስለተከበበ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ ይችላል፡፡ጫት ሲበዛ ውሃ መጣጭ ተክል ነው፡፡ .. በጣና የሚመረተው የባህርዳር ጫት ከድሬዳዋ እስከ ሀዋሳ ስሙ ይጠራል፡፡.እያሳሳቀ፣የዋህ፣ብሩህ ስሜትን ለጊዜው እየፈጠረ ጫት ነገን ይገላል፡፡በአማራ ክልል ከሚመረት ጫት 80% በሀገር ውስጥ ይቃማል፡፡ምንዛሬም አያመጣም፡፡በእርግጥ የጫት ገበያን እነ ሶማሊያ ሊዘጉት ዳር ደርሰዋል፡፡የመንም 20% ተጨማሪ ታክስ ስለጣለች ከጫት የሚገኝ ምንዛሬ አይኖርም፡፡የጫት ዓለም አቀፍ ገበያ እየተዘጋ ነው፡፡ የምንዛሬ አማራጭ ሊሆን አይችልም፡፡ስለዚህ የሚመረተው ሁሉ በሀገር ውስጥ መቃም ከተጀመረ ሀገሪቱ ሙሉ ቃሚ ትሆናለች፡፡አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ከሰዓት በኋላ ቢሮ ይዘጋል፡፡ሱቅ ዝግ ነው፡፡በቃ በጫት በስራ ላይ አድማ ይመታል፡፡ጫት ሲበዛ አስናፊ ነው፡፡ በእስልምናም በክርስትናም ጫት እንዲቃም አይበረታታም፡፡
…. ጫት ሽንት ሽንት ስለሚል ረጅም መንገድ እንኳ አያስጉዝም፡፡ ደግሞ ያቃዣል፡፡ከዛ ዱካክ ይለቃል፡፡ከሁሉም ነገር የከፋው ግን ለሌሎች ሱሶች መንገድ መሪ መሆኑ ነው፡፡ጫት የሚቅም በብዛት ያጨሳል፡፡ይጠጣል፡፡ጫት ብዙ ችግር ያስከትላል ፡፡ ያም ሆኖ ግን ጫት ጉባኤ ጠርቶ የሚያገናኘው ብዙ ደንበኛ አለው፡፡ …. ጫት በየቦታው እንዳይቃም፣ የጎጃሟ ሞጣ ከተማ በህግ ከልክላለች!!!ሌሎች ከተሞችም አካባቢኛ ህግ እየሰሩለት ነው፡፡
ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

2 comments:

  1. ወሬ ብቻ
    1. ቢነግድ አትርፎ ሳይሆን ተበድሮና ተገዶ ግብር የሚከፋ ወጣት የመጨረሻ አማራጩ ጫት መቃም ብቻ ሳይሆን መዝረፍ በስርቆት ስራ ላይ መደራጀትም ሊሆን ይችላል እውነት ለወጣቱ እንዲህ ከተጨነቅን እስካሁን ምን ስራ ተሰራ ወሬ ስንቅ ይሆናል እንዴ አቅም ያለው ሳይሆን ምላስ ያለው ባለሙያ የበዛበት የተማረው ሳይሆን የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ያለው እስኪ የህዝብ ቤተመፅሐፍቱን እንይ በሉ አታናዱኝ

    ReplyDelete
  2. ወሬ ብቻ
    1. ቢነግድ አትርፎ ሳይሆን ተበድሮና ተገዶ ግብር የሚከፋ ወጣት የመጨረሻ አማራጩ ጫት መቃም ብቻ ሳይሆን መዝረፍ በስርቆት ስራ ላይ መደራጀትም ሊሆን ይችላል እውነት ለወጣቱ እንዲህ ከተጨነቅን እስካሁን ምን ስራ ተሰራ ወሬ ስንቅ ይሆናል እንዴ አቅም ያለው ሳይሆን ምላስ ያለው ባለሙያ የበዛበት የተማረው ሳይሆን የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ያለው እስኪ የህዝብ ቤተመፅሐፍቱን እንይ በሉ አታናዱኝ

    ReplyDelete