Thursday, May 11, 2017

የሕወሓት መንግስት በኦራል የተጫነ ሠራዊቱን ከወልዲያ መስመር ወደ ጋይንት እያጓጓዘ መሆኑ ተጠቆመ

   




ፎቶ ከፋይል
(ዘ-ሐበሻ) በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የሚገለጸው ሕወሓት የሚመራው መንግስት ሠራዊቱን ከወሎ ወልዲያ መስመር ወደ ጋይንት እያጓጓዘ መሆኑን የአይን ዕማኞች ገለጹ::
የአይን እማኞች እንደሚገልጹት በወልዲያ መስመር እየተጓጓዙ የሚገኙት በኦራል መኪና የተጫኑት የጦር ሠራዊቶች ወደ ጋይንት ይሂዱ እንጂ በዚያ በኩል ምን እንደተፈጠረ ያወቁት ነገር የለም::
ወልዲያ ውስጥ የኦራል መኪኖቹ ከማለፋቸው አስቀድሞ መንገዶች መዘጋጋታቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ በፍጥነት እያበረሩ እንደሚነዱ ገልጸዋል::
በአካባቢው የሚገኙ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ ጥሪ አቅርቧል::


No comments:

Post a Comment