Monday, May 8, 2017

እነ ንግሥት ይርጋ ለግንቦት 15 ተቀጠሩ




ዛሬ (ሚያዝያ 30፣ 2009) የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማድመጥ ተቀጥረው የነበሩት ንግሥት ይርጋ እና 5 አባሪዎቿ፣ ሁለት ምስክሮች ተደመጡ። ንግሥት ይርጋ የመኪና እጥረት በሚል ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ባትቀርብም፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው ሦስት ምስክሮች 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ቴዎድሮስ ተላይን ብቻ የሚመለከቱ በመሆናቸው እንዲደመጡ ልደታ የተሰየመው አራተኛ የፌዴራል ከፍተኛ ወንጀል ችሎት ፈቅዷል። ሆኖም ሁለቱ ምስክሮች ከተደመጡ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ሦስተኛው ምስክር አያስፈልገኝም በሚል ችሎቱ ተጠናቅቋል። ቀሪ ምስክሮችን ለማድመጥ ለግንቦት 15፣ 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
Source: የፍርድ ቤት ውሎዎች

No comments:

Post a Comment