Wednesday, May 10, 2017

የመለስ ዜናዊ የጥላቻ ጥግ የፈጠራት ለተማረ ሰው ገሐነም የሆነችዋ ኢትዮጵያ ይቺ ናት !!!

   


Tesfaye Ru : የአንድ ሰው ፌስ ቡክ አካውት ላይ “እንዴት አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ከሰመራ ዮኒቨርሲቲ ጋር ይወዳደራል፡፡ ጎንደርስ ከጋምቤላ ዮኒቨርሲቲ ጋር እንዴት ይወዳደራል” ብሎ የፃፈውን አይቼ ሳቄ መጣብኝ፡፡
አንድ AAU የተማረ ጎደኛዬ አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ እኮ ፀዴ ነው አለኝ፡፡ ከምንድነው የፀዳው ስለው “ከእውቀት” ብሎ ቀለደብኝ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉንም ዮኒቨርሲቲዎች ማወዳደር ከንቱ ድካም ነው፡፡ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁሉም የተማረ ስታፍ የላቸውም፡፡ የተሻለው ሁሉ ይከዳል፡፡ ደግሞም መክዳትም አለበት፡፡ በደርግ ዘመን ተቃዋሚ በሚረሸንበት ሰዓት እንኳን አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ምሁራም ነበር፡፡ አሁን ግን አአዮ በኢኮኖሚ ድቀት ሳቢያ በምሁር ድርቅ እየተመታ ነው፡፡
ምሁር በማንኛውም አገር ንኡስ-ከበርቴ ነው፡፡ ያለ ምሁራን አገር የትም ስለማትደርስ፤ ሁሉም የአለም አገሮች በንጽጽር ለምሁራኖቻቸው ጥሩ ይከፍላሉ፡፡ ከኢትዮጵያ በስተቀር፡፡
መለስ ዜናዊ የበደሉት መስሎ የተሰማውን ከመበቀል ወደ ኃላ ያለበት ጊዜ የለም፡፡
አዲስ አበባ ተማሪ በነበረ ሰዓት የአዲስ አበባ ህዝብ አማረኛ ቋንቋ ሲናገር ሰምቶ ለምን እነሱ ከተማ ኖሩ በሚል ቅናት ነው መሰለኝ “አማራ ጠላት ነው መጥፋት አለበት አለ”፡፡
ፕሮፌሰር አስራት አስተማሪው በነበሩ ሰዓት ዝቅተኛ ነጥብ ሰጥተውት ነው መሰል ከዚያ ጀምሮ እሳቸውንም አስሮ ገደለ ምሁር ጠል ሆኖም ቀረ፡፡ የሱ ዘሮች ለጣሊያን እንቁላል ያቀርቡ ስለነበር ውስጡ በአድዋ ድል መደሰት አልቻለም፤ ስለዚህ ምኒሊክን ይጠላል፡፡ መለስ የተማረ ይጠላል፣ አማራ ይጠላል፣ የአድዋ ድልን ይጠላል፡፡ ይህ ሁሉ ጥላቻው የመነጨው ከበታችነት ስሜት የመነጨ ነው፡፡ ሂትለር አይሁድን ይጠላ ነበር፥ የሚጠላበት ምክንያት እሱ ጫማ ጠራጊ ሆኖ አይሁዶች ተሰደው መጥተው በንግድ የተሻለ ቦታ ደርሰው ሀብታም ስለሆኑ ነበር፡፡
ሂትለር ምቀኛ ነው፤ መለስም ምቀኛ ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የተማረ ሰው የአንዲት አነስተኛ የኮንቴነር ኪዮስክ ያክል እንኳን ገቢ እንዳያገኝ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የዶክተር ደሞዝ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለመካከለኛ ቤት ኪራይ እንኳን አይበቃም፡፡ ያልተማሩትና ራሳቸውን ጄኔራል ኮሮኔል እያሉ የሰየሙት እነ ጎብሩ ደግሞ ያለከልካይ የአገሪቱን ሀብት በሚሊየን ሳይሆን በቢሊየን ሲዘርፉት ህሊናቸውን አይሰቀጥጣቸውም፡፡ ኢጎና ሱፐር ኢጎ በውስጡ የሰለጠነበት ሰው ሲጀመር መች ወያኔ ይሆንና፡፡
ኬኒያ ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ በብድር መኪና መግዛትና ቤት መስራት ወይም መግዛት መብቱ ነው፡፡ ክፍያቸውም ጥሩ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ለልጁ ዳይፐር መቀየር ይከብደዋል፡፡ ከቤት ኪራይ፣ታክሲና ቂጣ አልፎ የሚተርፈው ብር የለውም፡፡ ሶፍት መግዛት ሌግዠሪ ሆኖበት ሽንት ቤት የሚጠቀመው ተማሪዎቹን ኪዊዝ በፈተነበት የፈተና ወረቀት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በቶዮታ የቤት መኪና ላይ ከ 150 – 300% ቀረጥ ትጥላለች፡፡ በአለም ላይ እንዲህ የሚያደርግ አገር የለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መኪና የሚያስገዛህ ገንዘብ ምናልባት ኬኒያ ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት መኪና ሊገዛ የሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡
ናይሮቢ ላይ ጥሩ እየተከፈለ እንኳን የቤት ኪራይና የኑሮ ውድነት አዲስ አበባ ይከፋል፡፡
ናይሮቢ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ፔይፓል መጠቀም ይችላል፡፡ ምክንያቱም የአለም አቀፍ ባንኮች ኬኒያ ውስጥ ስላሉ በ Equity bank አካውንት የከፈተ ገንዘቡን እንደፈለገ ማንቀሳቀስ ይችላል፡፡ መጽሀፍ ኦን ላይን መግዛት ለኬኒያዊያን ብርቅ አይደለም፡፡ የኤኒያ ምሁራን አገራቸውን አይከዱም፡፡
የኢትዮጵያ ባንኮች ለተራው ህዘዝብና ለመንግስት ሰራተኛ እንዳያበድሩ ብሔራዊ ባንክ በህግ ይገድባቸዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኛ መኖሪያ ቤት ለመስራት መበደር አይችልም፤ ከኮኒዲምየም በስተቀር፡፡ ለኮንዶሚኒየምም ቢሆን የመጀመሪያውን ክፍያ ለመክፈል ማጠራቀም የሚችሉበት አቅም የላቸውም፡፡
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የክፍለ ሐገር ከተሞችና አዲስ አበባ ዳር ላይ መኖሪያ ቤት ለመስራት የሚፈቀደው G+1 ሲሆን በማህበር ተደራጅተው ግማሽ ሚሊየን ብር በዝግ አካውንት ሲያሳዮ ቦታው ይሰጥና የ950ሺ ብር ቤት እንዲሰሩ ይፈቀዳል፡፡ እንግዲህ ምሁር እንኳን ቤት ሊሰራ የአንድ ዶክተር የ10 አመት ጠቅላላ ክፍያው እንኳን ይህንን ያህል አይሆንም፡፡
በተቃራኒው ኢትዮጵያ ውስጥ ሰርቀህም ቀምተህም ወይም ዘመድ ሰጥቶህ 3ሚሊየን ብር ከያዝክ፤ ህንፃ እሰራለሁ ብትል የደሃ ቤት አፍርሰው ቦታ ይሰጡህና 7ሚሊየን ከባንክ ተቀድረህ የ10ሚሊየን ብር ህንፃ ትገነባለህ፡፡ ወይም ደግሞ የ10 ሚሊየን ብር ህንፃ አስይዘህ የ50 ሚሊየን ብር ሆቴል ልገነንባ ብትል ባንኮች እኔ እኔ እያሉ ይራኮቱብሀል፡፡ የ50 ሚሊየን ብር ሆቴል ስትገነባ የቀጠርከው ሲቪል አኢንጂነር፤ ሆቴሉ ከተገነባ በኀላ አንተ ሆቴል ገብቶ የመጠቀም አቅም የለውም፡፡ ምክንያቱም ለመሀንዲሱ በወር እየከፈልከው ያሰራሀው ደሞዝ ሆቴል ሰርተህ ከጨረስክ በኀላ የአንዷ አልቤርጎ የቀን ኪራይ ከመሐንዲሱ የወር ደመወዝ ልትበልጥ ስለምትችል፡፡
ይቺ ናት የመለስ ዜናዊ የጥላቻ ጥግ የፈጠራት ለተማረ ሰው ገሐነም የሆነችዋ ኢትዮጵያ!!!

No comments:

Post a Comment