Saturday, May 20, 2017

ዶክተር ደብረጽዮን ካለመንግስት ይሁንታ ቴዲ አፍሮን ቃለምልልስ እንዲደረግ ያደረጉ የኢቢሲ ሠራተኞች እንዲቀጡ አዘዙ




(ዘ-ሐበሻ) የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ካለመንግስት ኃላፊዎች እውቅና እና ይሁንታ ከቴዲ አፍሮ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ የኢቢሲ ሠራተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ አስተላለፉ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ትናንት ሕወሓቱ ዶክተር ደብረጽዮን የኢቢሲን አስተዳደሮች በቴዲ አፍሮ ቃለምልልስ ዙሪያ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን አርቲስቱን ቃለምልልስ እንዲደረግ ማን እንደፈቀደ እንዲመረመር አዘዋል:: ካለባለስልጣናት ይሁንታ ቃለምልልሱ መደረጉና ቃለምልልሱ ሳይተላለፍ በፊት ማስታወቂያ መለጠፉና በኋላም አለመተላለፉ መንግስትን አሳጥቶታል ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን ቴዲ ቃለምልልስ ባይደረግ ኖሮ ይህ ሁሉ ውዥንበር አይፈጠርም ነበር ሲሉ በቁጣ መናገራቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
ደብረጽዮን ትናንት የኢቢሲን ማኔጅመንት የሰበሰቡት የመዝናኛ ክፍሉ ኃላፊ; ማስታወቂያውን በፌሰቡክና ዩቱብ በለቀቀው ሠራተኛና በጋዘጠኛ ብሩክ ላይ ቅጣት እንዲፈጸም ለማወጅ የነበረ ሲሆን ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ቀድሞ የሥራ መልቀቂያ በማስገባቱ ዶክተር ደብረጽዮን ምስጢር የሚያሾልክ አለ ማለት ነው በሚል በማኔጅመንቱ ላይ መጮሃቸውን ምንጮች አስታውቀዋል::

No comments:

Post a Comment