Tuesday, May 2, 2017

የሕወሓት ወታደሮች የአምቦን ነዋሪ እያዋከቡ ነው | ወጣት ሆኖ በምሽት የሚንቀሳቀስ ይታሰራል



(ዘ-ሐበሻ) በአምቦ ከተማ ቀስ በቀስ እየተነሳ ያለው የወጣቶች እና የተማሪዎችን አልገዛም ባይነት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የሕወሓት አጋዚ ሠራዊት ነዋሪዎችን እያዋከበ መሆኑ ተዘገበ::
አምቦ ከተማ ፎቶ ከዘ-ሐበሻ ፋይል
ከአምቦ አካባቢ የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጋብ ብሎ የነበረው የአምቦ ነዋሪዎች አልገዛም ባይነት ሰሞኑን በስፋት እየታየ መምጣቱን ተከትሎ የሰፈረው ሠራዊት ዓይኑ ያላማረውን እያጋዘ እንደሚያስርና እንደሚደበድብ ታውቋል::
ምሽት ላይ በከተማዋ ድንገት ሲንቀሳቀስ የተገኘም በተለይ ወጣት ከሆነ እንደሚታሰር አልያም በአጋዚዎቹ ትንኮሳ እንደሚያጋጥመው የሚገልጹት ምንጮቹ በአደባባይ የፈለጉትን ሰው እያስቆሙ ጥያቄ በመጠየቅ አፍሰው እንደሚወስዱ ገልጸዋል::
በአምቦ የህዝብ አልገዛም ባይነቱ ከ ዕለት ወደ ዕለት እየታጋጋለ ሲሆን በአካባቢውም በርካታ የሕወሓት ሠራዊት መስፈሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
በአምቦ ያለውን ሁኔታ ዘ-ሐበሻ ተከታትላ ትዘግባለች::

No comments:

Post a Comment