Monday, May 15, 2017

በእነ ጉርሜሳ አያና ክስ ዙሪያ አዲስ መረጃ


 0  34  34


(ግንቦት 7/2009) እነ ጉርሜሳ አያኖ ለዛሬ ግንቦት 7/2009 ተቀጥረው የነበረው አቃቢ ህግ ባቀረበው የሰው፣ የሰነድ እና የድምፅ ከምስል ማስረጃዎችን መርምሮ ብይን ለማሰማት ነበር። ሆኖም መዝገቡን የሚያዩት የ4ኛ ችሎት ዳኞች መዝገቡን የመመርመር ስራ እንዳላለቀላቸው በመናገር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን እንዲተረጉማቸው ከተላኩ የድምፅ ከምስል ማስረጃዎች ውስጥ በ11ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው ተቆርጦ መቅረቱን የተቀሩት ግን ተተርጉመው መቅረባቸውን የገለፁት ዳኛው ትርጉሙ ተሟልቶ ቢቀርብም ኖሮ የምርመራ ስራውን ማጠናቀቅ እንደማይችሉ እንደነበር ተናግረው ለግንቦት 30/2009 ቀጠሮ ሰጥተዋል።
የአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ተሰምቶ ካለቀ 4ት ወር የሆነው መሆኑን ጠቅሶ መዝገቡን የመመርመር ስራው ተጀምሮ ከሆነ ተጨማሪ 3ት ሳምንት መጠየቁ ሌላ አላማ ከሌለው በስተቀር ተገቢነቱ እንደማይታየው 1ኛ ተከሳሽ ጉርሜሳ አያኖ በችሎት ተናግሯል።
ዳኞችም መዝገቡ ሰፊ መሆኑን ተናግረው የይድረስ የይድረስ ሳይሆን በአግባቡ ተመርምሮ መሰራት እንዳለበት የገለፁ ሲሆን የቀጠሮውን ቀን ማቅረብ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ከቀጠሮው በፊት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ተቆርጦ የቀረውን ትርጉም እንዲልክ ታዟል፤ እንዲሁም ተከሳሾች በቀረበባቸው ሰነድ ላይ ትችት(አስተያየት) ያላቀረቡ ካሉ ከቀጠሮው በፊት ማስገባት እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል።
በተያያዘ ዜና አክቲቪስቱ እና የሰብአዊ መብት አራማጅ የሆነው ዮናታን ተስፋዬ ግንቦት 2/2009 ቀን ፍርድ ሊነበብለት ቀጠሮ ነበረው። በቀጠሮው መሰረትም ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ችሎት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ ዳኞች መዝገቡን የመመርመር ስራ የተጀመረ መሆኑ ነገር ግን አጠናቀው አለመጨረሳቸውን ገልፀው መዝገቡን መርምሮ ፍርዱን ለማንበብ ተለዋጭ ቀጠሮ ለነገ ግንቦት 8/2009 ተሰጥቶታል።
ዜናውየተገኘው ከየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ነው::

No comments:

Post a Comment