Thursday, May 18, 2017

ሰበር_ዜና …. አዲሱ ለገሰ …በረከት ሥምኦን…አቡሃይ ፀሃየ ከወልቃይት ሽማግሌወችንና ካህናትን ባህርዳር በሆቴሎች ሰብስባ አደረጉ



ገብርየ ገብርየ
ህወሃቶች አሁንም ባንዳው ብአዴንን በመጠቀም ወልቃይት ላይ አላርፍ ብለዋል። ባላፈው ሀሙስ ለት ጀምሮ የወልቃይት ሽማግሌወችንና ካህናትን ባህርዳር በሆቴል ብሉናይል አባንቲ ሪዞርት ሰብስበዋቸው ነበር። ሰብሳቡወቹም አዲሱ ለገሰ …በረከት ሥምኦን…አቡሃይ ፀሃየ እና ሌሎችም የህወሃት አመራሮች ናቸው። ሽማግሌወቹንና ካህናቱንም ደረጃ አንድ መኝታ ክፍል በመያዝ፤ የተለያዩ ሥጦታወችን እና ልዩ ልዩ መደለያወችን በመስጠት ሊያባብሏቸው ቢሞክሩ ሊሣካላቸው አልቻለም። ገዳዮቹ እነበረከት ስምኦንም ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት እየሠበኩ የወልቃይቴወችን አንጀት ለመብላት ሞክረዋል። ትንታጎቹ ወልቃይቴወች ግን ” አማራነት እየጠፋ ምን ሚሉት ኢትዮጵያዊነት ነው? ትግሬ የበላይ ሆኖ በዘር ቦለቲካ አገር እየጨፈጨፈ ምን ሚሉት አንድነት ነው? አማራ ነን ሥንል ትግሬ ናችሁ እየተባልን በግድ የዘር እንክርዳድ እየተደፋብን ሥለምን ኢትዮጵያዊነት ነው ምትሠብኩልን? የታለች ኢትዮጵያ…ከሁሉም በፊት አማራነታችን ይከበር” ሲሉ በወኔ እና በድፍረት መልሠውላቸዋል። ይልቅ ከወልቃይት ያመጡትን ሽመላቸውን እያማቱ ወልቃይትን ትግሬ ሊያደርጓት ቢሞክሩ ዘላለማዊ የማያባራ ጦርነት እንደሚሆን ከትልቅ ዛቻ ጋር የተናገሩ ሲሆን በመጨረሻም ለአንድ ሣምንት ይቆያል የተባለው ሥብሠባ በወልቃይት አማሮች እምቢተኝነት በዛሬው ለት ተቋርጦ ቀርቷል

No comments:

Post a Comment