Sunday, May 14, 2017

ወያኔ በናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሽንፈት ገጠመው።

   


ወያኔ በናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሽንፈት ገጠመው።
በናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ጥቂት ዓመታትን  ያስቆጠረ ዉዝግብ በፍርድ ቤት የመጀምሪያው ዉሳኔ May 11, 2017 አገኘ።  በተፈጠረው ዉዝግብ የተመሰረተው ክስ ያለአግባብ ቤተክርስቲያኗን የሚመሩት የሰባካ ጉባኤ ያለአግባብ (ህገወጥነት ባለው መስኩ) ከአቡነ ፋኑኤል ጋር በመመሳጠር ጥፋት አድርገዋል የሚል ነው። ከሳሾቹ በአቶ ሲራክ ሰብስቤ መዝገብ የሚገኙት ሲሆኑ በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗን ወክለው የሚከራከሩት ( እኔ አቶ ሳሙኤል) ጉድለት የፈፀምነው፣ አባላትንም ያጉላላነው ወ.ዘ.ተ. እስከአሁን በቅንነት (in good intention) ነው የሚለው  በዳኛዋ ተቀባይነት አላገኘም።
ስለዚህ ዉሳኔው የከሳሾቹን የጠበቃ ወጪ መክፈልን ይጨምራል።  ተከሳሾቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ከ $3000 ያልበለጠ ገንዘብ ይቀነስልን የሚል ነበር። ይህ ገንዘብ አቡነ ፋኑኤል የናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ው ሲኖዶስ እንዲገባ መደረጉን ተከትሎ በተነሳው ዉዝግብ  ምክንያት የዘመቻው ፊታውራሪ  የሆኑት አቡነ ፋኑኤል ለፍርድ ቤት የወጣ ወጪ ስለሆነ ናሽቪልን አይመለከትምና አቡነ ፋኗኤል ራሳቸው ይክፈሉ አይነት ይመስላል።
[ዝርዝሩን ለመመልከት መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.  (April 6, 2016) የወጣውን ሰንሰለት ይጫኑ። አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ተከሰው በዲሲ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው]
ተከሣሾች ( ቤተክርስቲያኗ) በ10 ቀናት ዉስጥ (ማለትም የዛሬ ሳምንት ) ድረስ የይግባኝ ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ። የይጋባኙ ጥያቄ ይህችን $3000 (ሶስት ሺህ ዶላር) ይቀነስልን የሚል ነው። ለዚህ ብቻ ብለው ይግባኝ መጠይቅ የበለጠ ለቤተክርስቲያኗ የበለጠ ክሳራ ይዳርጋታል።  ከልምድ እንደሚታወቀው የወያኔ እጅ በእጅ አዙር ስላለበት ነገሩን ለማጓተትና ከሳሽ ምዕመናን ለማዳከም ሊያደርጉ ይችላሉ። የዋሁ ምዕመን በሁሉም ወገን ገንዘቡን ያባክናል። እንደተለመደው ለምሳሌ በለንዶን፣ በሚኖሶታ፣ በዲሲ ማርያም ‘አሸንፈናል ደስ ይበላችሁ’ የሚል ቅጥፈት ሊናገሩ እንደሚችሉም ይጠረጠራል። ይህ አይነቱ ቅጥፈት ባድሜ ለኢትዮጵያ ተወሰነች ተብሎ የአዲስ አበባን ሕዝብ ሰልፍ እንዳሶጡት ማለት ነው።
ዳኛዋ የፍርድ ቤት ትዛዝ ትፅፋለች ተብሎ ይጠበቃል።
ቀደም ብሎ የወጣው የፍርድቤት ትዛዝ ቀጥሎ የመልከቱ።
ዉሳኔው እንደተደረገ ዝርዝሩን ይዘን እንደምናቀርብ ከወዲሁ ለአንባቢ አስገነዝባለን።

No comments:

Post a Comment