Tuesday, May 9, 2017

የመቐለ ባለ ባጃጅ ወጣቶች ዛሬ 01/09/09ዓ/ም ኣድማ መትው ኣርፍደዋል።

    



ባጃጅ ፕሮቴስት !
======
#Bajaja_Protest_Mekelle_Tigray_Ethiopia
የመቐለ ባለ ባጃጅ ወጣቶች ዛሬ 01/09/09ዓ/ም ኣድማ መትው ኣርፍደዋል።
የማህበር ኣመራሮቹ ከመቐለ ዞን መንገድ ትራንስፖርት ሃላፊዎችና ከከንቲባው ባካሄዱት ስብሰባ “እኛ ከስረን ከስራና ከኣገራችን እንድንወጣ የሚያስገድድ ፀረ ህዝብ ኣሰራር ጭናቹብናል። ካሁን በኋላ በዚህ ኣሰራራቹ ኣንሰራም በማለት ኣድመዋል።
የወጣቶቹ ቁርጠኝነት የታዘቡን ሃላፊዎቹ “እስከ ሃሙስ ብቻ በትእግስት ጠብቁን። ማስተካከያ እናደርጋለን” ብለው ቃል ገብተዋል።
ሃሙስ ማስተካከያ ካልተደረገበት ወጣቶቹ ዛሬ ጥዋት የጀመሩት ስራ የማቆም ኣድማ ወይም ተቃውሞ እንደሚቀጥሉበት ኣስጠንቅቀዋል።
ሓሙስ ኣዲሱ ኣስገዳጅ ስሚሪት ተቀይሮ ወደ ድሮው ይመለሳል ያልያም ጀግኖቹ የመቐለ ወጣቶቹ ከሁለት ዓመት በፊት ለ4 ቀን ያካሄዱት የስራ ማቆም ኣድማ ይደግሙታል።
የጉምቦት ወር በመቐለና የተቀሩት የትግራይ ከተሞች ህዝባዊ መነቃቃት የሚታይባት ሳትሆን ኣትቀርም።
የባቡር ጉዳይም ከባጃጅ ኣድማ ጎንለጎን ሊቀጥል ይችላል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው !

No comments:

Post a Comment