Thursday, May 11, 2017

የመንግስት ባለስላጣናትን በዝርፊያ ለማድለብ ህዝብ ከቀየው የሚፈናቀልባት ሀገር፡- ኢትዮጵያ (ከአደማሱ በጋሻው)

 11, 2017 00:17      



ትናት  ማለት ግንቦት 01/09/2009 ዓ.ም ከአዲስ አበባ  ተነስቼ ጅማ ልደረስ 2 ክሎሚትር ያህል ሲቀረኝ አንድ አስደንጋጭ ትይንት ተመለከተሁ፡፡ ወደ አራት የሚሆኑ የገጠር  አዛውንቶች/ሽማግሌዎች አንድ እራፊ ልብስ አንጥፈው የሚያልፈውን መንገደኛ ሁሉ አትለፉን፤ ያላችሁን ጣል ጣል አድረጉልን ይላሉ፡፡ ከሽማግሌዎቹ  በግምት አስር ሜትር ርቀት በሚገኘው የጅማ ጫካ ስር በረሃብ የተጎዱ ሕፃናት፤ እናቶችና ወጣቶች ሰውነታቸው ዝሎ፤ ልብሳቸው ከአቧራ ጋር ተመሳስሎ  በየዛፉ ስር ተቀምጠዋል፡፡ ሁሉም አይናቸው የሚየተኩረው  በሚያልፍ በሚያገድመው መኪናና በምጽዋቱ ላይ ነው፡፡ ሁኔታው እጅግ ግራ አጋብቶኝ እያለ የምጓዝበት መኪና ለወገኔ የምችለውን ያህል እጄን ሳልዘረጋ በማለፌ ጸጸት ተሰማኝ፡፡ በተለይም ምክንያቱን ባለማወቄ አእምሮየ ሠላም አጣ፡፡ ሹፌሩን እባክህ እንመለስና ለወገኖቼ የምችለውን ላድረግ ፎቶም ላንሳ  ብየ ስጠይቅ ከወቅቱ ፖለቲካ ችግር ጋር በማያያዝ አደገኛ መሆኑን በመግለጽ ወደ ከተማው ገሰገሰ፡፡ በመንገድ ላይ ቢያንስ ሰው እንጠይቀ ተባብለን መኪናውን ቆም አድርርን አንዱን በአካባቢው የነበረ ሰው ስንጠይቅ ከኢልባቡር አካባቢ ከቀያቸው ተፈናቅለው እንደ መጡ ነገረን፡፡ ምክንያቱን ማጣራት ባንችልም ያው የተለመደው የብሄረ ግጭት ይሆናል ብለን ወደ ከተማው እያዘን ገባን፡፡ ነገር ግን ምክንያቱን ለማወቅና የምችለውንም ለወገኖቼ  ለመረዳት ከራሴ ጋር ተስማማሁ፡፡ በማግስቱ ማለትም 02/09/2009 የመስክ ስራ ከጅማ በስተምስራቅ በኩል ስለነበረኝ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ያን ጫካ ስር አካሉ ዝሎ ያየሁትን  ወገኔን ለህሌናየ ስል ትንሽ መረዳትና ምክንያቱንም ለማጣራት ወሰንሁ፡፡
ይህ ተፈናቃዮች ሲያድሩበት የነበረው ከጅማ ወደ አዲስ አበባ ስንወጣ የሚገኘው  የጥድ ደን  ነው


ከጧቱ 3 ሰዓት አካባቢ የሞባይል ካሜራየን አዘጋጅቼ ወደቦታው በመኪና ስገሰግስ ሞባቢትንምትትተ እንድ ቲ-ሻየር ይሰራበት በነበረው  ግቢ ውስጥ ትናንት ያየኋቸው ምስኪን ወገኖቼ አሁንም በየዛፉ ስር ተቀምጠዋል፡፡ ወጣቶቹ ወዲህና ወዲያ ይላሉ፡፡ እኔና ጓደኞቼ መንግስት ከመንገድ በማራቅ  ከእይታ ለመሰወር ያደርገው ለመሆኑ አልተጠራጠርንም፡፡ በቲ-ሻየር ግቢ በር አካባቢ  የከተማ ፖሊሶች  ይታያሉ፡፡ እኔም ያሰብኩትን ባለማሳካቴ እየተበሳጨሁ ወደ መስክ ሰራየ ቀጠልሁ፡፡ ነገር ግን ንዴቱ አልበረደልኝም፡፡ ስለዚህ ስመለስ መረጃ የማገኝበትን መንገድ ማፈላለግ ጀመርሁ፡፡ የነበረኝ አማራጭ ከመስክ ስራ ስመለስ ከቲ-ሻየር ቢሮ አካባቢ  መውረድና ማጣራት ነበር፡፡ ነገር ግን አብረውኝ የነበሩት ባልደረቦች ሁኔታውን ለማጣራት መስጋታቸውን  ስለተገነዘብኩ ከመስክ ስንመለስ ከተ- ሻየር ቢሮ በግምት 500 ሜትር ርቅት አካባቢ ጓደኛ እንዳለኝና መጠየቅ እንደምፈልግ ለስራ ባለደረቦቼ ነገሬ ከመኪናው ወረድሁ፡፡ ተፋናቃዮች ከተሰበሰቡበት ግቢ ስደረስ ለፎቶም ሆነ መረጃ ለማግኝት አስቸጋሬ ሆነብኝ፡፡ ከ-ቲ-ሻየር ቢሮ በስተምስራቅ በኩል አንድ መልስተኛ ወንዝ አለ፡፡ወንዙ የቢሮውን የምስራቁን ክፍል የሚያዋስን ነው፡፡ በወንዙና በቢሮው መካከል አጥር የለም፡፡ ስለሆነም አንዳንድ  ተፈነናቃዮቹ  እዚያ  ወንዝ እየሄዱ ልብስ ሲያጥቡ ተመለከትሁ፡፡  ከወንዙ በስተምስራቅ ጥቅጥቅ ያለ የቡና ደን እና አልፎ አልፎ የሚታዩ ትላልቀ ዛፎች አሉ፡፡ በቡና ደኑ ውስጥ ለውስጥ በመሄድ ልብስ የሚያጥቡ ሁለት ሴቶች ከአንዴት ህፃን ጋር  አገኘኋቸው፡፤ በጫካው ውስጥ ስለሄደኩ ሴቶቹ  ምቾት አልተሰማቸውም፡፡ በተለይ ህፃኗ በፍርሐት ነው የተመለከተችኝ፡፡ ህፃኗን ፎቶ ለማሳት ሞከርሁ ግን ሩቅ ስለነበረች ፎቶ ግልፅ ሊሆን አልቻለም፡፡

ይህ ከጎድጓደው ውስጥ ከገላጣው ቦታ ላይ  የምትየው ፎቶ የህፃኗ ነው፤  ከበስተ ኋላዋ በኩል የተጠቀለለ የሚመስለው አረንጓዴ ነገር ሴቶቹ አጥበው ያሰጡት ልብስ ነው፡፤ ሴቶቾቹ  ከህፃኗ በታች ጎድጓዳው  ውስጥ  ስለሆኑ በፎቶው ላይ አይታዩም፡፤




የውይይት መክፈቻ ቢሆነኝ ብየ እህቶቼ! ልብስ የምታጥቡበት ወሃ ቆሻሻ ስለሆነ አይጠጣም አለኳቸው፡፡ እንዲያ ዝም ብየ ነው እንጅ ሴቶቹ ውሃ እየጠጡ አልነበረም፡፡  ነገር ግን መልስ አልሰጡኝም፡፡ ምን ነካቸው? ብየ አሰብሁ፡፡ ከየት ነው የመጣችሁ? ብየ ጠየኩ፡፡ ልብስ ከሚያጥቡት አንደኛዋ  “አማርኛ እምቤኩ” አለችኝ፡፡ እኔም አንዳንድ የኦሮምኛ ቃላትን ብገነዘብም ለተግባቦት የማያበቃኝ መሆኑን በመገንዘብ  በንዴት ከጫካው ወጣሁ፡፡
በአካባቢው የሁኔታውን እንግዳነት በመገንዘብ ወጣቶችና አንዳንድ አዋቂውች በአካባቦው ያንዣብባሉ፡፡ ሁለት ወጣት ቢጤዎች በቲ-ሻየር ቢሮ ፊት ለፊት ቁመው ይወያያሉ፡፡ እኔም በድፍር ሰላም ናችሁ?  ብየ ተጠጋሁ፡፡ አንደኛው የጅማ ነዋሪ ቢሆንም አማርኛ አያውቅም መሰለኝ በአይኑ ወደ ሁለተኛው ሰው አመለከተኝ፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ስለተፈናቃዮች የምታውቀው ካለ ብየ ጠየኩት፡፡

ይህ ሰው ስለተፈናቃዮች  በቂ መረጃ አለው፡፡ ሰዎቹ የመጡት ደዲሳ ከተባለ  ቦታ መሆኑን ነገረኝ፡፡ እንደነገረኝ ከሆነ በመጀመሪያ እነዚህ ተፈናቃዮች ከአርሲ አካባቢ መንግስት በሰፋራ ስም ደዲሳ አካባቢ አስፍሯቸው  ነበር፡፡ ሰፋሪዎቹ ታታሪ ሰራተኞች ስለነበሩ በጥሩ ሁኔታ ይኖሩ የነበረ ቢሆንም የመቱ ከተማ ከንቲባ ሰፋሪዎቹ ይኖሩበት የነበረውን ለም መሬታቸውን በመንጠቅ ለስኳር ፋበሪካ  ይፈለጋል በማለት ሰፋሪዎቹን ለሁለተኛ ጊዜ ከመኖሪያ ቦታቸው ያፈናቅላቸዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ  በምትኩ  የተሰጣቸው መሬት አዝሪዕት የማያበቅል መሆኑን ሲረዱ አንቀበልም ይላሉ፡፡ ለችግራቸው ከመቱ ከንቲባ መፍትሄ ያጡት ሰፋሪዎች ወደ ኦሮሚያ ጨፌ ቢሮ በመሄድ በደላቸውን ለማሰማት ይወስናሉ፡፡ በዚህ ውሳኔያቸው አራት ቀን ሌት ከቀን ተጉዘው ጅማ ይደርሳሉ፡፡ በጉዞ ላይ እያሉ ሶስት ሕፃናት እንደሞቱና  አንዴት ሴት ደግሞ በጫካ ውስጥ እንደወለደች የመረጃ ምንጬ  አጫውቶኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት በጅማ እና አካባቢዋ ዝናብ ነው፡፡ ስለሆነም ህፃናት በብዛት የሚገኝባቸው እነዚህ  ተፈናቃዮች ላለፉት አራት ቀናት ፀይ፤ ብረድ  እና ዝናብ  ሲፈራረቅባቸው ሰንብቷል፡፡ህፃናትንና ሽማግሌዎችን  ይዞ  እንኳንስ በክረምት  በበጋ ወራት ከአካባቢ መፈናቀል ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ሁላችንም የምንረዳው ነው፡፡ እንደተረዳሁት ከሆነ የጅማ ከተማ ህዝብ በሁኔታው በእጅጉ  አዝኗል፤ ተፈናቃዮችንም ለመርዳት ገንዘብ እያዋጣ ነው፡፡
ወደ ኦሮሚያ ጨፌ ቢሮ ችግሩን ለማመልክት በመጓዝ ላይ የሚገኙት የተፈናቃዮች ብዛት ህፃናትን ጨምሮ 1,900 (አንድ ሺህ ዘጠም መቶ) ነው፡፡በብሄር ስብጥር ደረጃም ኦሮሞ፤ አማራና አፋር ይገኙባቸዋል፡፡ ክህዝብ እይታ ለመሰወር ወደ ተ-ሻየር ቢሮ እንዲገቡ ያደረጉት የኦሮሚያ ከፍተኛ ባለስላጣናት መሆናቸውንና ወደ አዲስ አባባም እንዳይመጡ ትዛዝ ማስተላለፋቸውን ከመረጃ ምንጬ ለመረዳት ችያለሁ፡፡
እንግዲህ ኢትዮጵ በህወሓት ኢህአዴግ ዘመን ለደሀ ልጆቿ እንዲህ መራር ነች፡ ህወሐት/ኢህአዴግ ሀገር ሊዘርፍ ደሀው ገበሬ ከአንጡራ መሬቱ ይፈናቀላል፡፡ ችግሩን የሚረዳለት አካል የለም፡፡በእገሩ ተጉዞ እንኳ ችግሩን ለማስረዳት አይፈቀድለትም፡፡ ይህን ደሀ የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሓት/ኢህአዴግ  የሚፈለገው  አንድ በምርጫ ጊዜ  ነው ሌላም በጦርነት  ወቅት ነው፡፡
በስኳር ፋብሪካ ስም በአፋር በአሳይታ አካባቢ በጎንደር በዋልድባ አካባቢ በህወሐት/ኢህአዴግ  የተፈፀመውና እየተፈፀመ  ያለውን ግፍ ኢትዮጵያውያን የሚዘነጉት አይመስለኝም፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን የሚቃወሙ ቡድኖች ተባብረው የሀገርና የህዝብ ጠላት የሆነውን ህወሓት/ኢህአዴግ ካላስወገዱ ይህ በመንግስት ስም የተሰየመ የበላየ ሰብ ቡድን የሰውን ደመ ከመጠጣት ስጋውንም ከመብላት የሚመለስ አይደለም፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

No comments:

Post a Comment