Monday, May 8, 2017

እዉነትና እና ንጋት እያደር ይጠራል፣፣ – ጉግሳ



ዛሬ በዘሀበሻ የጃንሆይ እናት! – ዳዊት ከበደ ወየሳአትላንታ | ለተስፋዬ /አብየጀሚላ እናትምላሽ የሚል እርእስ ሳይ ዝም ብየ አነበብኩት፣፣ ቀስ በቀስ ትኩረቴን እየሳበኝ መጣ፣፣ እስከ መጨረሻዉ ጨረስኩት፣፣ በጣም ደስ ይላል፣፣ ለካ በየ ቦታዉ ሰዉ አለ አልኩኝ፣፣ በሀገራችን ላለፉት 25 አመታት የሚፃፉ የፖለቲካ ታሪኮች ወደፊት ባገራችን ላይ የሚፈጥሩትን ችግር ሳስበዉ ይዘገንነኛል፣፣ እያንዳንዱ ነገራችን ተበርዟል፣ ተጥላልቷል፣ በዉሸት ታሪኮች ተጋኗል፣ ተደብቋል፣ ወዘተ፣፣ ይህ ሁሉ ነገር ደግሞ የሚደረገዉ በግለሰቦች ብቻ አይደለም፣ ይልቁንም እኛ በማናያቸዉ በማንደርስባቸዉ እጅግ ጥልቅ በሆኑ ሀይሎች ስዉር ሴራ ነዉ፣፣ አላማዉ ግልጥ ነዉ፣፣ እኛን ከምድረ ገጥ ለማጥፋት ነዉ፣፣ እኛ የምንመለከተዉ ከፊት የወጡትን የተወሰኑ ሰዎች ነዉ፣፣ ከነዚህ ዉስጥ አንዱ ተስፋየ ገ..ነዉ፣፣
ይህን እንድል ካስቻሉኝ ነገሮች በጥቂቱ
ባለፈዉ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የአማራና ኦሮሞ የዘር ግንድ የሚል መጠሀፍ ሲጥፉ፣፣ አገሩ ሁሉ ተናጋ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወሬዉና ትችቱ ጎረፈ፣፣ በጣም ግን ትኩረቴን የሳበዉና በዚህ አገር በጣም ጠንካራ ስዉር እጅ አለ የሚለዉን ያጠናከረልኝ፣፣ የዶክተሩ መጠሀፍ እንዳይሸጥ ተከልክሎ የተስፋየ ገብረአብ የቡርቃ ዝምታና የአለቃ ታየ ገብረ ማሪያም ስለ ኦሮሞ የጣፉት የአዲስ አበባን ጎዳናወች በአዲስ መልክ ታትሞ ሞልቶታል፣፣ ተስፋየ ካለዉ መንግስት ጋር ተጣልቶ ተብሎ ያለዉ ዉጭ አገር ነዉ በማን ፈቃድ ታተመ ብየ አዟሪወችን ስጠይቅ ለኛ በቅናሽ ታትሞ ነዉ የተሰጠን አሉኝ፣፣ የግል ማጣራቴን በድብቅ ቀጠልኩበት፣፣ ያለቃ ታየን መጠሀፍ አሳታሚ አድራሻ ደረስኩበት፣፣ በጣም ደነገጥኩ ያልጠበኩት ተቋም ሁኖ ሳገኜዉ፣፣ የመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን፣፣ እኔ እራሴ አለቃ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቄስ ይመስሉኝ ነበር፣፣ ሳጣራ ግን በአጤ ዮሀንስ ዘመን በወጣጥነታቸዉ ልክ እን ወለጋዉ ኦነሲሞስ ነሲብ አስመራ ሂደዉ በስዊዲን ሚሽን ትምህርት ቤት ተምረዉ እምነቱን እንዲያስፋፉ በዳግማዊ ሚኒሊክ ዘመን የተመለሱ ናቸዉ፣፣
ላለፉት 40 አመታት የኦነግ ፖለቲከኞች የሳቸዉን ታሪክ በመጥቀስ ተሰድበናል እያሉ እንደማጣቀሻ ያደርጓቸዋል፣፣
ስለ ስዉር እጆች ይህን ካልኩ፣፣ ደራሲዉ የጀሚላ እናት የሚለዉን ድርሰት ከጣፈ በኋላ በኦ.ኤም.ኤን ቀርቦ በኩራት ይህ ታሪክ ሀሰት ነዉ የሚል መጥቶ ይሞግተኝ እያለ ሲያወራ እኔ በተጨበጠ መረጃ እንደምረታዉ አቅ ነበር፣፣ ነገር ግን እሱ በትልቅ ተቋማት ከለላ፣ በከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ፣ በብዙ ማወናበጃወች እየታገዘ፣ እኔ አንድ ለፍቶ አዳሪ ምን ለዉጥ ላመጣ ብየ የወጣት ጉልበቴን አደከምኩት፣፣ ግን ከልቤ አዘንኩ ፈጣሪየንም አምላኬ የዚህን ሰዉ ሴራ ለዚህ ህዝብ ግለጥለት ብየ ጠለይኩ፣፣ ወደ ጭብጡ ልግባ፣፣ ከላይ የለጠፍኩት ፎቶ በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ከተማ ዉስጥ በቀዳማዊ ኀ/ ስላሴ ዘመን የተገነባዉ የልእልት የሽ እመቤት አሊ ትምህርት ቤት ነዉ፣፣ ልእልቷ የአሊ አባ ጋምጮ ልጅ ናቸዉ፣፣ ታሪኩን ዳዊት ከበደ ወይሳ በተብራራ ሁኔታ ስላስቀመጠዉ መድገም አልፈልግም፣፣ እኔ ከነዚህ ሰዎች ቤተሰብ ጋር አብሬ ነዉ ያደኩት፣ ሽማግሌወቹንም ደርሸባቸዋለሁ እሱ የሚለዉን ተረት አንዳቸዉም አልነገሩን፣፣ በተለይ የወንድማቸዉን የደርብ ሀሰን አሊ ቤተሰብ በአካልም ማቅረብ ይቻላል፣፣
ይህ ቤተሰብ ደርግ እስከመጣበት ድረስ በወረኢሉና በጃማ እጂግ የተከበረ ባለብዙ ሀብት ነበር፣፣ የነበረዉ ዘዉዳዊ ስርአት ሲወድቅ ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ ከሀገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ተገለለ እንጂ እሱ እንዳለዉ ሙስሊም በመሆናቸዉ የተገለለ የተገደሉ፣ ወይም  እንዲጠፉ አልተደረጉሩም፣፣ ለዚህ ማሳያዉ በስማቸዉ የተሰራዉ ትምህርት ቤት አንዱ ነዉ፣፣
የተስፋየ ትልቁ ችሎታ የተወሰኑ የታሪክ ጭብጦችን ይሰበስብና ከላይ በልብ ወለድ ታሪክ ከሽኖ ያቀርበዋል፣፣ ሲያቀርብ ደግሞ የወቅቱን የፖለቲካ ትኩሳት በማየት ነዉ፣፣ ይህ ታሪክ ሲጥፍ በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የድምጣችን ይሰማ ሰላማዊ ትግል የነበረበት ወቅት ስለሆነ በግርግር የሰቅሰቂያ ጦሩን ይዞ ያሉብንን ጠባሳወች በደንብ አድርጎ እስኪደማ ድረስ ይሸቀሽቃቸዋል፣፣
ስለ ሀገራችን አፍራሽ ታሪክ በባእዳን ሰዎች ከብዙ አመታ በፊት ጀምሮ ሲጥፉ ነበር፣፣ በተለይ ጣሊያኖች ከአድዋ ሽንፈታቸዉ በኋላ አስመራ ዉስጥ ኤጀንሲያ ፕሮፖጋንዳ የሚባል ተቋም አቋቁመዉ ልክ አሁን ተስፋየ እንደሚያደርገዉ እዉነቱን ከዉሸቱ በመቀላቀል በኤርትራ እና በሶማሊያ ለህዝቡ ይረጩ ይበር፣፣ ያሁሉ መርዝ በኛ በኩል ምንም ጠንካራ ተቋም ስለሌለ እና ጉዳቱንም አርቀን ስለማንመለከት መከላከል አልቻልንም፣፣ ልብ ይስጠን፣፣
ጉግሳ ነኝ
 
የወረኢሉ ከተማ በከፊል

No comments:

Post a Comment