Sunday, May 7, 2017

አዲስ አበባን ያካተተ የሸዋ ክልል አስፈላጊ ነው – ክፍል ( #ግርማ_ካሳ)

   



“የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅምን አስመልክቶ የተጻፈ” ( Concept-Paper-for-Special-Interest-Over-Finfinne ) የሚል አንድ ሰነድ እና አዲስ አበባ ላይ የ”ኦሮሞዎች” መብትን እንዲያስጠበቅ ተብሎ፣ በዉጭ ባሉ የኦሮሞ ፈርስት አቀንቃኞች እንደተዘጋጀ በሚነገርለትና የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር አባላትም ሕግ እንዲሆን በፌዴራል መንግስት አቅርበዉታል በተባለው በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ ተቃዉሞና ውግዘት፣ በተለይም በሶሻል ሜዲያው ተሰተናግዷል። ከዚህም የተነሳ ፣ የፌዴራል መንግሥት ቃል አቀባይ ነገሪ ሌንጮ “እኛ የምናውቀው ሰነድ አይደለም” በሚል ማስተባበያ እስከመስጠት ደርሰዋል።
ከ120 አመታት በፊት አሁን አዲስ አበባ በምትባለውና በሸዋ፣ በአብዛኛው ነዋሪዎች ነበሩ። ያንን የሚከራከር ይኖራል ብዬ አላስብም። ከሶስት፣ አራት መቶ አመታት በፊት በዚያ ቦታ ኦሮሞዎች አልነበሩም። ከደቡብ መጥተው ነው ሸዋን ወረው የያዙት። ወደ ታሪክ ከሄድን ታሪክን ነጥለንና የፈለግነው ብቻ መዘን ብቻ ሳይሆን ማየት ያለብን ሁሉንም ነው። ከ100 አመታት በፊት እነርሱ ይኖሩበት ስለነበረ፣ ከ400 አመታት በፊት ይኖሩበት ያልነበረንና ወረው የያዙትን መሬት፣ የኛ መሬት ነው ብለው መከራከሩ የትም አያስኬድም። መታየት ያለበት አሁን በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ ነው። የድሮ ቁስል ከተነሳ ፣ የድሮ በደል ከተነሳ፣ ተበደልኩ ባዩም እርሱም በሌላ ወቅት በዳይ እንደነበረም መርሳት የለብንም። የሚበጀው የዜሮ ድምር የኋላ ቀር አስተሳሰብ ሳይሆን፣ የሚያቀራረብ፣ የሚያያይዝ፣ ለሁሉም የሚበጅ አስተሳሰብና አሰራር ነው። “ይሄ መሬት የኔ ነው፣ ያንተ አይደለም፣ ይሄ የኦሮሞ ነው፤  ያ የትግሬ ነው …” ከማለት፣ “ሁላችንም እስከኖርንበት ድረስ፣ የሁላችንም ነው” በሚል የጋራ ቤታችን በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር ለመገንባት መነሳቱ ነው።
እስቲ “አሁን በሜዳ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ? ” ብለን እንጠይቅ።፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ይፋዊ የሆኑ የሕዝብ ቆጠራ ሪፖርቶችን እንመለከታለን። በ1994 የህዝብ ቆጠራ ሪፖርት መሰረት በኦሮሚያ የሸዋ ዞኖች ውስጥ 16 ከተሞች ከ10 ሺህ በላይ የህዝብ ብዛት ነበራቸው። ከነዚህ 16 ከተሞች በ13ቱ አፋን ኦሮሞ የማይናገሩ ከስድሳ በመቶ በላይ ነበሩ።
ከ2007 የሕዝብ ቆጠራ፣ በነዚህ ከተሞች ምን ያህሉ አፋን ኦሮሞ እንደሚናገር ለማወቅ አልቻልኩም። ሆኖም ከ1994 ከኔበረው ብዙ ይለያል ብዬ አላስብም። በ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት አዲስ አበባን ጨምሮ በሸዋ፣  41% የሚሆነው ነዋሪ አፋን ኦሮሞ የማይናገር ሲሆን፣ በአዳማ ፣ አፋን ኦሮሞ የማይናገር 74%፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን 30% ናቸው። አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ እና ምስራቅ ሸዋ ዞን ስንጠቀልላቸው ደግሞ 70% የሚሆነው ህዝብ ገጠር ያለውን ገበሬዉን ጨመሮ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ አይደለም።
እንግዲህ ለዚህ ነው “መሬቱ የኦሮሞ ነው” በሚል ጠባብና የኋላ ቀር አስተሳሰብ ፣ አፋን ኦሮሞ ብች የስራ ቋንቋ ሆኖ፣ ሌላው አገሩ እንዳልሆነ ተደርጎ እንዲታየ የሚደረገበት አሰራር መቆም አለበት የምንለው። 70%፣ 60% …. አፋን ኦሮሞ የማይናገሩ ዜጎች የሚኖሩባቸው ቦታዎች እንዴት ሆኖ ነው የኦሮሞው ብቻ የሚሆኑት ? አዲስ አበባ 90% አማርኛ ተናጋሪ እየኖረባት እንዴት ነው የኦሮሞ ብቻ የምትሆነው ? ከ13 በላይ የኦሮሚያ የሸዋ ትላልቅ ከተሞች ከስድሳት በመቶ በላይ አማርኛ ተናጋሪዎች እየኖርባቸው እንዴት ነው የኦሮሞ ብቻ የሚሆኑት?
መፍቴው ቀላል ነው። ከዚህ በታች የምትመለከቱት ሰንጠረዥ እንደሚያሳየው፣ ሸዋ በተለይም አማርኛ ተናጋሪዎችና ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በጋራ የሚኖሩባት አካባቢ ናት። አንዱ ሌላውን እየገፋ፣ አንዱ ሌላውን እያስፈራራ፣ አንዱ ሌላው ላይ እየዛተ መቀጠል አይቻልም። ኦሮሚያ የሚባለው ነገር ሌላውን ማህበረሰብ አይወክልም። በመሆኑም ሁሉንም የሚወክል፣ ታሪካዊ ስሙን የያዘ ፣ አማርኛና አፋን ኦሮሞ የሥራ ቋንቋ የሆኑበት የሸዋ ክልል አስፈላጊ ነው።
የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ በሸዋ የሚኖረው አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ፣ እነ አቶ ለማ መገርሳ ሰሞኑን የመዘዙት አይነት በማናቸዉም ጊዜ ሊመዘዝበት፣ ሕልዉናውም አደጋ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል መርሳት የለበትም።

No comments:

Post a Comment