በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መልካ ጅሎ አሞራ ቤት በተባለው አካባቢ የአገዛዙ ወታደሮች ሚያዚያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም በአልታሰበ ሰዐት መጥተው 27 የክላሽንኮፍ መሣሪያዎችን መግፈፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
የመሣሪያ ገፈፋው ከፍተኛ የሆነ የገበሬዎችን ቁጣ ቀስቅሶ ገበሬዎቹ ለወረዳው አስተዳደርና ለኮማንድ ፖስቱ መሣሪያቸው በአስቸኳይ ካልተመለሰ እርምጃ እንደሚወስዱ ከአስጠነቀቁ በኋላ የወረዳው አስተዳዳሪዎች አፋጣኝ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሽማግሌዎች ድርድር ከተደረገ በኋላ ሃያ ሰባቱም ክላሽንኮፎች ሚያዚያ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ተመልሰውላቸዋል፡፡ ከተወሰደው ጥይት የጎደለ ስለነበር ከ600 ብር ካሣ ጋር ተቀብለናል ብለውናል፡፡
No comments:
Post a Comment