እፍረተ ቢሱ ወያኔ የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቃዋሚዎችን ሕልውና ኣስጠብቋል እያለ የተቃዋሚ ኣመራሮችን እያፈሰ ማሰሩን ቀጥሏል። የዶክተር መረራ መታሰር ተከትሎ ወያኔን እንደ አዲስ አሳሪ አካል ለማየት የሚሞክሩ ሰዎች ይገርማሉ።የዶክተር መረራ መታሰር የትግሉ አንድ ቅጠል ነው። ወያኔ ከዶክተር መረራ በፊት በርካታ ምሁራንን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችን በየማጎሪያ ካምፑ ቆልፎባቸዋል።
ወያኔ በ አንድ እጁ እየጨበጠ በኣንድ እጁ ቡጢ እያቀመሰ ይገኛል። ዶክተር መረራን ብቻ ሳይሆን በኮማንድ ፖስቱ ስም የታሰሩት ሁሉ እንዲፈታ ጫናው ቀጥሏል።ትግላችንን ማሳደግ እንጂ መዘናጋትና መደናገጥ የለብንም፤ ብርታት ይጠበቅብናል።በመረራ ጉዲና ከሚመራው መድረክ ጋር ስብሰባ የተቀመጠው የኮማንድ ፖስቱ ለተቃዋሚዎች ደህንነት ሕልውና ቆመናል ብሎ እየተናገራቸው ስብሰባው ሲበተን የተቃዋሚ አመራሩን አፍኖ ማሰር ስርዓቱ ምን ያህል አጭበርባሪ እንደሆነ ያጋለጠ ነው።
ወያኔ እስካልተወገደ በቀር ይህ የጭቆና ኣገዛዝ መቀጠሉ አይቀርም። ወያኔ የሚያስረው ለመግደል የትግል መንፈስን ለማንኮታኮት እንዲሁም በቁምህ ስቃይ ሊያሸክም ስለሆነ ይህንን ማስቆም የምንችለው ትግላችንን አጠናክረን ስንቀጥል እንጂ ታጋዮቻችን እየታፈኑ ሲታሰሩ በመደነቅ እና በመበሳጨት አሊያም ወሬ በማውራት አይደለም።
No comments:
Post a Comment