Wednesday, December 7, 2016

ዘመን አይሽሬው ብዕረኛ ፤ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ህይወታቸው ካለፈ ዛሬ 13 ዓመት ሞላቸው! !!!


ዘመን አይሽሬው ብዕረኛ ፤ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ  ህይወታቸው ካለፈ ዛሬ 13 ዓመት ሞላቸው! !!!!!
/በኢዮብ ዘለቀ/
በኢትዮጲያ አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም.በቀድሞ አጠራሩ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረ ማርቆስ አውራጃ ተወለዱ ፤ ታላቁ የብዕር ሰው ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ።
ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በ ደብረ ኤልያስ ባህላዊውን የቅኔና ዜማ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ።
ከቀደምት የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሀክል አንዱ የነበሩት ሀዲስ እስከ ኢጣሊያ የወረራ ዘመን ድረስ ዘመናዊ ትምህርታቸውን የመከታተል እድሉን አግኝተዋል ።
በኢጣሊያ የወረራ ዘመን አርበኛችን ተቀላቅለው ጠላትን ሲፋለሙ በመማረካቸው እስከ 1936 ዓ.ም. ድረስ ወደ ኢጣሊያ ሃገር ተወስደው በእስር ላይ ቆይተውል ።
ከነጻነት በኃላ ለአመታት በዲፕሎማሲውም ሆነ በተለያዮ የሀላፊነት ቦታዎች በመመደብ አገራቸውን በሚገባ አገልግለዋል ።
Eyob Zeleke's photo.
ሀዲስ አለማየሁ በርካታ የታተሙና ያልታተሙ ስራዎች ነበራቸው ።
*ፍቅር እስከመቃብር
* ወንጀለኛው ዳኛ
* የልምዣት ከዋና ዋና ሥራዎቻቸው ተጠቃሽ ናቸው ።
ስመ ጥሩ አርበኛ ፣መምህር ፥ አምባሳደር፥ ሚኒስትርና የሥነ ጽሑፍ ሰው ክቡር ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ ህይወታቸው ያለፈው ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በዛሬዋ እለት ኅዳር 27ቀን 1996 ዓ.ም. ነበር።

No comments:

Post a Comment