- በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡
- ለማንኛውም እኔ ያልኩዎት ይኼንን ነው፡፡
- ምንድን ነው ያልከኝ?
- የአሜሪካ ምርጫ ቴአትር አይደለም፡፡
- የእኛ ቴአትር ነው እያልከኝ ነው?
- እህሳ፡፡
- ግን ለምን ቴአትር እንደሆነ ታውቃለህ?
- አላውቅም፡፡
- በሕዝቡ ፍላጐት ነዋ፡፡
[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሮ ቁጭ ብሎ የአሜሪካንን ምርጫ በቲቪ እየተከታተለ ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ደወሉለት]
- አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
- በአስቸኳይ ቢሮ ና፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ቲቪ እየተከታተልኩ ነበር፡፡
- ስማ በሥራ ሰዓት ዛራና ቻንድራ ታይልኛለህ?
- ኧረ ሌላ የሥራ ጉዳይ ነው እየተከታተልኩ ያለሁት፡፡
- ምን አሁን ኢቢሲ ላይ ምን አጓጊ ነገር ኖሮ ነው?
- አይ የአሜሪካን ምርጫ እየተከታተልኩኝ ነው፡፡
- እኔ ጠፋሁ!
- ምነው?
- ዋነኛው ኒዮሊብራሊስት አጠገቤ ተቀምጦ ኖሯላ?
- እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
- የእነሱን ምርጫ ምን ሊያደርግልህ ነው የምትከታተለው?
- ከእነሱ እኮ ብዙ የምንማረው ነገር አለ፡፡
- እየቀለድክ ነው?
- ኧረ የእውነቴን ነው፡፡
- አሁን ማን ይሙት እነሱ ከእኛ ይማራሉ እንጂ እኛ ከእነርሱ እንማራለን?
- እነሱ ደግሞ ከእኛ ምን ይማራሉ?
- ለምሳሌ ምርጫ መድፈን እንደሚቻል፡፡
- ብለው ነው?
- እህሳ? ከእነሱ ግን ምን መማር እንችላለን?
- ለምሳሌ ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሥልጣን ይዟል፡፡
- እኛስ ለመጀመሪያ ጊዜ 100 በመቶ ወንበር ይዘናል አይደል?
- ከዚያም ባለፈ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዚዳንት ልትሆን ትችላለች፡፡
- እኛም እኮ በፓርላማ ባሉን ሴቶች ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ነን፡፡
- ቢሆንም አሜሪካ እኮ ሴት ፕሬዚዳንት ሊኖራት ይችላል እያልኩዎት ነው?
- ግን ያ እንዴት ሊሆን ይችላል?
- ምን ችግር አለው?
- ሴት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልትሆን?
- ለምን አትሆንም?
- ያው ትንሽ …
- ክቡር ሚኒስትር ሴቶች ኢምፓወር መደረግ አለባቸው እያሉ በየቦታው ሲያወሩ አልነበር እንዴ?
- የምታወራውን ሁሉ ታደርገዋለህ ማለት አይደለም፡፡
- እኮ እንዴት?
- በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡
- ለማንኛውም እኔ ያልኩዎት ይኼንን ነው፡፡
- ምንድን ነው ያልከኝ?
- የአሜሪካ ምርጫ ቴአትር አይደለም፡፡
- የእኛ ቴአትር ነው እያልከኝ ነው?
- እህሳ፡፡
- ግን ለምን ቴአትር እንደሆነ ታውቃለህ?
- አላውቅም፡፡
- በሕዝቡ ፍላጐት ነዋ፡፡
- እንዴት ሆኖ?
- በየቴአትር ቤቱና ሲኒማ ቤቱ ሕዝብ እንዴት እንደሚሰለፍ አይተሃል?
- በደንብ አይቻለሁ፡፡
- ስለዚህ ሕዝብ ቴአትር ይወዳል ማለት ነው፡፡
- እ…
- አየህ ምርጫው ላይም የነበረውን ሰልፍ ታስታውሰዋለህ?
- አዎን፡፡
- በቃ ስለዚህ ለዛ ነው የሕዝቡ ፍላጐት ቴአትር ነው ያልኩህ?
- የአሜሪካ ምርጫ ግን ቴአትር አይደለም፡፡
- ነው እንጂ፡፡
- እንዴት ሆኖ?
- ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው የቲቪ ሾው የነበረው አክተር አይደል እንዴ?
- ዶናልድ ትራምፕን ነው?
- ታዲያስ እሱ አክተር/ፖለቲከኛ ነው፡፡
- እርስዎ ግን ምን እንደሆኑ ያውቃሉ?
- ምንድን ነኝ?
- ኮሜዲያን/አክተር!
[የክቡር ሚኒስትሩ ልጅ ስልክ ደወለላቸው]
- ዳዲዬ!
- ወዬ፡፡
- ና በእናትህ፡፡
- ምን ሆነህ ነው?
- ምን እዚህ…
- አፍህ እየተኮላተፈ ነው፡፡
- አንድ ጌ…ጃ… ትራፊክ…
- ምንድን ነው የምታወራው?
- እዚህ…
- ጠጥተሃል እንዴ?
- ትንሽ… ነው… የቀማመስኩት፡፡
- ምን?
- አንድ… ሦስት… ብርጭቆ… ዊስኪ ናት፡፡
- የት ነው ያለኸው?
- የሆነ የሚያስጠላ… ቦታ ነው፡፡
- ሰክረህ ነው?
- በእናትህ… ዳዲ… አታካብድ፡፡
- ጠጥተሃል ወይ?
- ትንሽ… ነው… የቀመስኩት፡፡
- አጠገብህ ማን አለ?
- እንካ አናግረው፡፡
[የጣቢያው አዛዥ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር ማውራት ጀመረ]
- ሄሎ!
- ማን ልበል?
- ማን ልበል ነው ያልከኝ?
- አዎን ጌታዬ፡፡
- በእርግጥ ጌታህ ነኝ፡፡
- ምንድን?
- ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
- እንዴት ሆኖ ነው ልጄን ያሰርከው?
- እኔ መቼ አወቅኩ?
- ሥራህ ምን ሆነና?
- የትራንስፖርቱን ሥርዓት ማስከበር ነዋ፡፡
- ከዛ በፊት ማድረግ ያለብህ ነገር አለ፡፡
- ምንድን ነው?
- የእኔ ቤተሰቦችን ማንነትና ምንነት ማወቅ፡፡
- እሱ የሥራ ኃላፊነቴ ውስጥ እንዳለ አላውቅም ነበር፡፡
- ለዚህ ደግሞ ትቀጣለህ፡፡
- ኧረ ይቅርታ ጌታዬ፡፡
- ምን አድርጐ ነው ልጄ?
- ጠጥቶ ሲያሽከረክር ተይዞ ነው፡፡
- እኮ በአስቸኳይ ይለቀቅ፡፡
- ሕግ ጥሷል ግን፡፡
- እኔ ጠፋሁ፡፡
- በዛ ላይ አንደር ኤጅ ነው፡፡
- አዋልደኸዋል አንተ?
- እንደሱ ማለቴ አይደለም፡፡
- እኮ በአስቸኳይ ልቀቀው፡፡
- ቤት ማን ያደርሰዋል?
- አንተ ምን ትሠራለህ?
- እሺ አደርሰዋለሁ፡፡
- ከዛ እኔና አንተ እንገናኛለን፡፡
- ምን ለማድረግ?
- እየጠጣን ለማውራት!
[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቤት እየሄዱ ነው]
- ምን ሆነህ ነው አንተ?
- ጉንፋን ይዞኛል ክቡር ሚኒስትር፡፡
- የክረምቱ ቅዝቃዜ ለነገሩ ከባድ ነው፡፡
- ቅዝቃዜው ሳይሆን ሌላ ነው፡፡
- ስማ ይኼ ክምር ምንድን ነው?
- የቱ ክቡር ሚኒስትር?
- ከተማው ውስጥ የሽምቅ ውጊያ ተጀምሯል እንዴ?
- የምን የሽምቅ ውጊያ?
- በየቦታው የከረጢት ክምር አያለሁ፡፡
- እንደ እርስዎ ዓይነት ቀልደኛ ሚኒስትር አይቼ አላውቅም፡፡
- እንዴት?
- መቼም በየቦታው የሚያዩት የከረጢት ክምር ለድርቁ የተሰጠን ዕርዳታ ነው አልልዎትም?
- ታዲያ ቀልደኛው ማን ነው?
- እርሱ አይደል እንዴ ጉንፋን ያስያዘኝ?
- ቀልዱ ነው?
- ኧረ በየቦታው ያዩት የቆሻሻ ክምር፡፡
- ለምንድን ነው ቆሻሻው የማይነሳው?
- ያሳመመኝ እሱ ቀልድ ነው አልኩዎት እኮ፡፡
- የምን ቀልድ?
- የቆሻሻ ቀልድ!
[ክቡር ሚኒስትሩ የከተማው አስተዳደር አንድ ኃላፊ ጋ ደወሉ]
- አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ልትጨርሱን ነው እንዴ?
- በምን?
- በጉንፋን፡፡
- ድምፅዎት ግን ጉንፋን የያዘው ሰው አይመስልም፡፡
- ሕዝቡ በጠቅላላ ተለክፏል አይደል እንዴ?
- በምን ክቡር ሚኒስትር?
- በበሽታ፡፡
- እ…
- ቆሻሻው ለምንድን ነው የማይደፋው?
- አልሰሙም እንዴ?
- ባለፈው አንድ ቢሊዮን ብር ያወጣ የቆሻሻ መጣያ ሲመረቅ ጠርታችሁኝ አልነበር እንዴ?
- እኮ መጣል አትችሉም አሉን፡፡
- እነማን?
- የአካባቢው ገበሬዎች፡፡
- ምን?
- አዎ፣ እኛ ቆሻሻ መጣያ አይደለንም አሉ፡፡
- እኔ ጠፋሁ፣ እና ምን አላችኋቸው?
- ምን እንላለን?
- ነገ ደግሞ በዚህ በኩል በመኪና ማለፍ አትችሉም ቢሉስ ምን ልትሉ ነው?
- ምን ማለት እንችላለን ክቡር ሚኒስትር?
- እንዴት አትችሉም?
- ይኼ እኮ የፌደራሊዝም መዘዝ ነው፡፡
- እኔ ጠፋሁ እና በበሽታ እንለቅ?
- በምን በሽታ?
- በአተት፡፡
- እሱ እኮ ስሙ ተቀየረ፡፡
- ምን ተባለ?
- መተት፡፡
- የምን አባህ መተት ነው አንተ መተተኛ?
- አይ እሱኛውን መተት አይደለም፡፡
- ታዲያ መተት ምንድን ነው?
- መደበኛ ተቅማጥና ትውከት!
[ክቡር ሚኒስትሩ ቤት ሲገቡ ከሚስታቸው ጋር ማውራት ጀመሩ]
- ሰላም ውዴ፡፡
- እንዴት ዋልሽ ውዴ?
- አንተን እኮ በሌላ ማዕረግ መጥራት ናፈቀኝ፡፡
- በምን ዓይነት ማዕረግ?
- ለምሳሌ ዶክተር ብሎ መጥራት ናፈቀኝ፡፡
- መቼም ከዚህ በኋላ ሜዲካል ዶክተር መሆን አልችልም፡፡
- እሱንማ አውቃለሁ፡፡
- ወይም ደግሞ ፒኤችዲ አልማር?
- በየትኛው አቅምህ?
- ታዲያ ምንድን ነው የምታወሪው?
- ጥያቄዬ የአንተ ተራ መቼ ነው የሚለው ነው?
- የምን ተራ?
- የክቡር ዶክትሬት የምታገኝበት ጊዜ ነዋ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ነኝ እኮ፡፡
- እስቲ ክቡር ሚኒስትር ከክብር ዶክትሬት ጋር ሲሆን ያለውን ክብር አስበው፡፡
- እሱስ ልክ ነሽ፡፡
- የቀበሌ ሊቀመንበር ሳይቀር እየተሰጠው እኮ ነው፡፡
- እ…
- 12ኛ ክፍል ሳይጨርሱ በአቋራጭ ዶክተር ሲባሉ?
- እ…
- የሚመስለው አምስት ለአንድ እያደራጃችሁ የምትሰጡ ነው እኮ፡፡
- ምን?
- ታዲያ አንተ መቼ ነው የሚደርስህ?
- በቃ ተይው መላ አለኝ፡፡
- ምን ልታደርግ?
- ዩኒቨርሲቲ አቋቁማለሁ፡፡
- ምን የሚያደርግ?
- የክቡር ዶክትሬት አዳይ!
No comments:
Post a Comment