ዘርኡ መሃሪ
በ60ዎቹ በነበረው የአብዮቱ ፖለቲካ ተሳትፊያለሁ የሚል የዛን ጊዜው ተማሪ፡ ያሁኑ ሽማግሌ በአብዛኛው እሚያደርገውን የማያቅ፤ ፖለቲካውን፡ በተለይምማርክሰ ለኒንነትን ላይላዩን ካልሆነ በስተቀር፡ ተለቅ ያለ እውቀት አልነበረውም።.ክአገራⶭን ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም ሊያመጣውየሚችለውን ችግር ቀድሜ አውቅ ነበር የሚል ሰው ካለ፡ ገና ከስህተቱ ያልተማረ ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ላይ የወደቅችው፡ በዛን ጊዜ በነበርው የአዲስ አበባ ፍንዳታ ተማሪ፡ በተማሪው ውስጥ በነበሩ ዘረኞች የሻእብያ ሰዎችና ደጋፊዎቻቸው:በወታኛደሩ መፈንቅለ መንግስትና በውጭ ሃይሎች ድብቅ ሴራ ምክንያት ነው። ያ አርቆ ያላየው፡ የዛን ጊዜ ተማሪ፡ ዘገምተኛ ለውጥን ለማምጣት እንደመማር ፈንታ፡ ስልጣንን በኢትዮጵያ ስፕሪንግ (Ethiopian Spring) ለመጨበጥ ባደረገው ሙከራ ነው እዚህ ደረጃ የደረስነው – ፍንዳታው፡ ራሱን አልጠቀመ፡ ለአገር አልረባ ይሀው በስደት አገር እንደተንከራተተ ይኖራል። ያ ነውጠኛ ትውልድ፡ አገርን ለመጥቀም የማርክሰ ለኒንነት ርእዮተ-ሃሳብ የመፍትሄ መንገድ ነው በሚል መንፈስ የአካልና የጊዜ መስዋእት እንዳደረገ ግን አሌ እሚባል አይደለም። ይህን ካልኩ ዘንዳ ወደ ሌ/ጀነራል ጻድቃን ደጋግመውወደሚያነሱት ነጥብና ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ወደ አነሳሳኝ ዋና ጉዳይ ልመለስ።
ጀነራሉ፡ ከዚህ በፊት በድሬ ትዩብ በሰጡት ቃለመልልስ፡ አሁን ደግሞ የወቅቱን ጉዳይ አስመልክተው በሚጽፍዋቸው መጣጥፎች፡ የወያኔን ማርክሰ ለኒንነትንደጋግመው ለመግለጽ አይታክቱም። ወያኔ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ የተማሪ ንቅናቄዎች ምንም እሚያገናኝ ነገር ስላልነረው ነው “ወድዬት ጠጋ-ጠጋ” በሚል ርእስዙርያ ለመጻፍ የተገደድኩት።
ወያኔ በመሰረቱ፡ ዘረኛና ህዋላ ቀር አስተሳሰብ የነበረው፡ አዲስ አበባ በነበሩ አለም ያልተገለጸላቸው(exposure ያልነበራቸው)ጥቂት የትግራይ ተማሪዎች፡በኤርትራውያን ብሄርተኞች አማካይነት የተመሰረተ ድረጅት ነው – አላማውም ትግራይን ለመግንጠል። ህወሃትን ከመሰረቱ አባላት፡ አንድም በተማሪውእንቅስቃሴ ውስጥ በአስተባባሪነት እሚታወቅ ሰው የለም። መለስ፡ ህወሃት ከመመስረቱ በፊት፡ በሻእብያ ውስጥ የተደራጀ ነበር። ሌሎች፡ አሁንም በውጭ አለምያሉትም ጭምር፡ የሻእብያዎቹ እነ ስብሃት ኤፍሬም እና ሌሎች ያደራጁዋቸው ፍጹም ጸረ ኢትዮጵያ አላማ የነበራቸው ናቸው።
ወያኔ ሲመሰረት ጸረ ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያን ለመምታት ደግሞ፤ አማራንና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን መምታት ብሎ የተነሳ ድርጅት ነው። መንደርደሪያውንለማመቻቸት ፡ አፍራሽ ድርጊቱን የጀመረው ኢትዮጵያዊነትን ያራምዳሉ ባላቸው የትግራይ ተወላጆች ነው። በትግራይ የነበሩትን ባላባቶች፤ አብዛኞቹፊትውራሪዎች፡ቀኛዝማቾች፡ ብላምባራሶች…ወዘተ በወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ደምፍላት ተጨፍጭፈዋል።
ይሄ ህዋላ ቀር ድረጅት፡ የትግራይን ሪፑብሊክ ለመምስረት ደፋ ቀና ሲል የኖረና፡ አሁን የሚያነጋግረውን; የወልቃይትን፡ የራያ አካባቢዎችን-ገና ከጅምሩ-በካርታው ያሰፈረ ድርጅት ነው። ከኢትዮጵያውያን ደርጅቶች ጋር ያለውን ግኑኝነት የሞትና የሽረት አድርጎ ሲቆጥረው፡ ከኤርትራውያንና ከሱዳን የጠበቀ ሊባልየሚችል ግኑኝነት የነበረውና ያለው ድርጅት ነው።
እነ ጻድቃን፡ ጊዜና ቦታ ተመቻችቶላቸው፡ በለስ ቀንትዋቸው ለድል ስለበቁ፡ ጸረ ደርግ ተዋግተናል የሚልዋት ነጥብ እንደቁም ነገር እንድትቆጠርላቸውይወተውታሉ። ወያኔ የተዋጋው ኢትዮጵያን ነው። አጋጣሚው በደርግ መፈንቅለ መንግስት ተመቻቸላቸው እንጂ፡ ድርጅቱ ከነ ጸረ ኢትዮጵያ አላማውበሻእብያዎች መሰባሰብ የጀመረው በስልሳዎቹ የመጀመርያ ዐመታት ነው።
በወያኔ ጸር ኢትዮጵያዊነት አሁንም እሚጥራጠር ማንም የለም። የመንግስት መዋቅር፡ ያገሪቱን ሃብት፡ ሰራዊትን በሙሉ የአንድ ዘር ያደረገው ወያኔ፤ በቀላሚኖጸረ ኢትዮጵያ ካሪክለም ቀርጾ የትግራይ ህጻናትን እሚመርዝ ደርጅት፤ ኢትዮጲያዊ አላማ ነበረኝ፡ ማርክሰ ነኒናዊ ነበርኩ ሲል፡ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማያስብላል። ጀነራል ጻድቃን፡ ወድየት ጠጋ-ጠጋ፡ወኔው ካሎት እውነቱን ለመናገርና ትክክነኛውን ኢትዮጵያዊ መንገድ ለመከተል አሁንም አልመሸም፡ ጊዜውአሎት፡፡ እድሜ ለንስሃ ነው።
No comments:
Post a Comment