እንደራደር ….. የወያኔ የማዘናጊያ እና የማጭበርበሪያ ደውል
ወገኖቼ መቸም የወያኔን እኩይ ምግባር የቱን ጥለን የቱን አንስተን እንደምንናገር አናውቅም ሙሉ ሰውነቱ በመጥፎ የፖለቲካ ፈንጂዎች እና በቀሎች የተሞላ በማዘናጋት እና በማደናበር በማጭበርበር የተሞላ መሆኑ ሳይታለም በይፋ የተፈታ እውነት ነው፥በድርድር ስም ሲያጭበረብር የነበረ ከመሆኑም በላይ በትልቁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ያጭበረበረ እና እያጭበረበረ እያዘናጋ ያለ ቅስም ለመስበር የሚራውጥ የሽብር ጀሌ ነው:: ወያኔ ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ አንድም ቀልድ ነው አንድም ማዘናጊያ ስልት ነው::

ትኩስ ወሬ የሆነው የወያኔው ጁንታ እንደራደር የሚለው ጥያቄ እጅም አስገራሚ የማይደንቅ ሆኖም በጭንቅ ሰአት የተጠበቀ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ አሊያም ማጭበርበር ሲጨመርም ማዘናጋት የታከለበት ጠማማ አክሄድ መሆኑ ለማንም አይጠፋውም፥ወያኔ በሃገር ውስጥ ያለውን ሕዝብ እና ከሃገር ውጪ ያለውን ዲያስፖራ ለማዘናጋት እና ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት የመጀመሪያውን ዳገት በመቧጠጥ ላይ ይገኛል::
የወያኔው ጁንታ ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ወጥሮ የያዘውን ከፍተኛ አደጋ ለመወጣት ሲሆን ከዚህም መሃል የኦሮሞ እና የኣማራ ሕዝብ ንቅናቄ – የሕግ የበላይነት – የፖለቲካና የኢኮኖሚ እኩልነት – በሃገሪቱ ይከሰታል ተብሎ የሚሰጋው እና በጥናት ሪፖርት የቀረበበት የኑሮ ውድነት-እንደ ወልቃይት ያሉ ሕዝቦች የማንነት ጥያቄዎች – በሰራዊቱ ተቋማት ውስጥ እየተነሱ ያሉ ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች – በተለያዩ ሃገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ብሄራዊ ውርደቶች – የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ – በሃገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው የትውልዱ ስራ ማጣት እና ስደት -የፖለቲካ ምህዳኡ መጥበብ ያስነሳው አለማቀፍ ጫና -በየእስር ቤቱ ያሉ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ይፈቱልን ጫና -እንዲሁም ተመሳሳይ የሆኑ የዲሞክራሲያዊ መብቶች እና የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ለውጦች ጥያቄዎች ሕዝብ በኣንድ ኣንደበት ወያኔን ኣልፈልግም ማለቱ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ሲሆን በየጊዜው በሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች እና በማይገናኚ የሃሰት እይታዎች የሚዲያ ፍጆታ የፖለቲካ ውሸቶች ሕዝብ በጁንታው ላይ ያለውን እምነት በማጣቱ እና ተስፋው በመሟጠጡ ወያኔ በውጥረት ውስጥ በመሆኑ ይህንን ለማዘናጋት እና የፖለቲካ ማጭበርበር ለመፈጸም የድርድር ጥያቄዎች ማቅረቡ ምንም አዲስ ነገር ካለመሆኑም በላይ የሚጠበቅ እና የማዘናጊያ ደውል ነው:;
No comments:
Post a Comment