Wednesday, August 10, 2016

በወልድያ ከተማ የብአዴን አመራሮች ተቃውሞ ገጠማቸው


በወልድያ ከተማ የብአዴን አመራሮች ተቃውሞ ገጠማቸው
‹‹ቆቦንም አሳልፋችሁ ስላለመስጠታችሁና አይመለከተንም ስላለማለታችሁ ምንም ማረጋገጫ የለንም ››የወልድያ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች
በያሬድ አማረ
********************************************************
በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ በትላንትናው እለት ማልትም በ3/12/2008 ዓ.ም ከሰዓት በሁዋላ በወልዲያ ባህል አዳራሽ የሰሜን ወሎ ዞን መምሪያ የብአዴን አመራሮች ከመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ወልቃይቶችን እንጂ እኛን አይመለከተንም በማለታቸው ከሰራተኛው ከፍተኛ ውግዘት እንደገጠማቸው ስሙ እንዳይገለፅ የፈለገ የስብሰባው ተሳታፊ ግልፆልናል ፡፡እንደ መረጃ ምንጫችን ገለፃ ከሆነ የዞኑ አመራሮች እንደማወያያ ይዘው የቀረቡት የመንግስትን የአቋም መግለጫ ነው በሚል በንባብ መልክ የቀረበ እንደነበርና ስለወልቃይት የማንነት ጥያቄ የወልቃይት ህዝብን እንጂ ሌላውን የአማራ ህዝብ አይመለከትም የሚል ተካቶበት የነበረ በመሆኑ ቅሬታን ማስነሳቱን እና ተሰብሳቢው የወልቃይት ጉዳይ አይመለከታችሁም ካላችሁን ነገ ደግሞ የራያ ቆቦን አሳልፋችሁ ስላለመስጠታችሁ እና እኛን አይመለከተንም ስላለማለታችሁ ምንም ማረጋገጫ የለንም ስለዚህ የእኛ እዚህ መጠራት አቋማችሁን ልታሳውቁን እንጂ እኛን ለመስማት ዝግጁዎች ባለመሆናችሁ ምንም የንሰጠው ሀሳብ የለም በሚል የመንግስት ሰራተኛው ሌላ ሀሳብ ሳይሰንዝር ከአዳራሹ መውጣቱን ምንጫችን አያይዞ ገልፆልናል፡፡
በተያያዘ ዜና በትላንትናው እለት በወልድያ ከተማ የፌደራል ፖሊሶች ወጣቶችን በየቦታው በመሰብሰብ የተለዩ ስዎች ካያችሁ አሳውቁን እያሉ ስልክ እየሰጡ መሆኑንና በዛሬው እለትም በእሁዱ ሰልፍ ልጆቻችሁ እነዳይወጡ ምከሩዋቸው ለማለት የከተማውን ነዋሪ ስብሰባ ቢጠሩም ህዝቡ ሊገኝ እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሎዋል፡፡በየቦታው እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድም በወልድያ ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment