Sunday, August 7, 2016

ሙሉ በሙሉ ጎንደር እና ጎጃም ሕዝቡ በይፋ ከወያኔ ጋር መዋጋት ጀምሯል።

ሙሉ በሙሉ ጎንደር እና ጎጃም ሕዝቡ በይፋ ከወያኔ ጋር መዋጋት ጀምሯል። ወያኔ በግልጽ በዐማራው ላይ የጅምላ ግድያ አውጇል፤
በወረታ ከተማ ከባድ ተኩስ ተከፍቷል፥በአዲስ ዘመን ከፍተኛ ውጊያ በመደረግ ላይ ሲሆን እስካሁን በደረሰኝ መረጃ ሶስት ሰው መገደሉንና ብዛት ያላቸው ሰዎች እንደቆሰሉ ነው።መተማ ሽንፋ ሸዲ እና ቋራ በመከላኪያና በህዝቡ ማህል ሽምቅ ውጊያ እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
ዛሬ ከሰአት በኋላ 7.30 ላይ የጀመሩት የፎገራ ዐማሮች ከወያኔ ቅጥረኞች ጋር ከባድ ተጋድሎ እያደረጉ ነው፡፡ ከቦታው በስልክ ለማረጋገጥ እንደሞከርነው የወረታ ከተማ ሙሉ በሙሉ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ ዐማሮች ላይ የጥይት ዶፍ እየወረደ ነው፡፡ እስካሁን አንድ ሰው ሲሞት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ቆስለዋል፡፡የፎገራ ዐማሮች የተሰዋውን ዐማራ አስከሬን ይዘው በዞር ከቅጥረኛ ወታደሮች ጋር ከባድ ፍልሚ ላይ ናቸው፡፡ በስልክ በደወልንበት ወቅት የሚሰማው የጥይት ጩኸት ከባድ መሆኑን የተገነዘብን ሲሆን በርካታ የሥርዓቱ አገልጋይ በሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት ንበረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል፡፡ ከተማ በአሁኑ ሰአት ሙሉ በሙሉ ወደ ጦር አውድማነት ተቀይራለች፡፡ ከተለያየ አቅጣጫ የፎገራ ገበሬዎች ወደ ከተማ እየገቡ ነው፡፡ሶሮቃ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ነው። አይምባ ላይም እንዲሁበጣም ከባድ ውጊያ። በሶሮቃ ውጊያው ትግሬ ወያኔ ታንክ ጭምር እየተጠቀመ ነው። ያገሬ ሰው ተወልዶ ያደገበትን መሬት በሚገባ እየተጠቀመበት ነው። ያገሬ ጀግና የጦርነት ቦታወችን በማብዛት ትግሬ ወያኔን እያስጨነቀው ነው። በአገሬ ጀግኖች ታንክን ጨምሮ በርከት ያሉ የጦር መሳሪያ የጫኑ የጦር ተሽከርካሪወች ተማርከዋል።በጌምድር በወሳኝ መልኩ ከትግሬ ወያኔ ግኝ ግዛት ነፃ እየወጣች ነው።
ወያኔን መጣል የሚቻለው ኦሮሞውም ኣማራውም ሌላውም ኢትዮጵያዊ ተደምሮ በጋራ ሲቆም ነው።የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ሲያሰማ ወያኔ ኣማራ ጉያ ይወሸቃል።የኣማራ ሕዝብ ተጋድሎ ሲጀምር ወያኔ ኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ ይወሸቃል በሰላ ጩቤ ምላሱ ሕዝቦችን በማታለል እንዲጋደሉ በር ከከፈተ በኋላ ዳር ላይ ቆሞ ይስቃል። ስልጣኑን ያደላድላል የለም መሬቶችን ሃብት ይዘርፋል ያዘርፋል፥የጎሳ ፖለቲካ የብሄር ግጭት ፈጣሪው ወያኔ ነው።ወያኔን በጋራ በኣንድነት ቆመን ማጥፋት ከቻልን ሰላማችንን እናረጋግጣለን። ልብ ያለው ልብ ይበል #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment