Thursday, December 1, 2016

ግንቦት ሰባት ከ ኤርትራ መንቀሳቀስ ጀምሮ ይሆን ?


ግንቦት ሰባት ከ ኤርትራ መንቀሳቀስ ጀምሮ ይሆን ? Girma G. Kassa
ወዳጄ ሙሉነህ ዩሐንስ የግንቦት ሰባት ጦር ከኤርትራ እየገባ እንደሆነ አረጋግጫለሁ የሚል ነገር ጽፏል። ብዙ ጊዜ ግንቦት ሰባቶች ለሚሉት ቦታ አልሰጥም ነበር።ለምን በጣም ስለሚዋሹ። ሆኖም ግን ከግንቦት ሰባት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የማከብረው፣ የጎንደር ልጅ የሆነው ይሄን ሲጽፍ ችላ ልለው አንችልም።
ኢሳት ትላንት የአማራ ተጋድሎ ከፋኝ ቡድን አንዱ መሪ ከሆኑት ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር። እኝህ መሪ ግንቦት ሰባት እንዳልሆኑ በግልጽ አስቀምጠዋል። እርሳቸውም ሆነ ህዝቡ ግንቦት ሰባት ይመጣል ብሎ ለብዙ ጊዜ ይጠባበቅ ነበር። እስከአሁን ግን ምንም የታየ ነገር የለም። ግንቦት ሰባቶች ከመጡ ከነርሱም ጋር አብረው እንደሚሰሩ ነው የከፋኝ መሪ የገለጹት።
እንግዲህ ወዳጄ ሙሉነህ እንዳለው ሻእቢያ ፈቅዶ የግንቦት ሰባት ጦር ወደ ጎንደር መንቀሳቀስ ከቻለ፣ በአገር ቤት ከተስፋፋው ትግል ጋር ተደምሮ፣ ያለምንም ጥርጥር በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም። ለምን ቢባል የትጥቅ ትግሉ በቂ ሎጂስቲክ ሊያገኝ ይችላልና። በዚህ ጉዳይ ላይ የጠሩ ነገሮች ሲኖሩ እንመለስበታለን።
አንድ ነገር ግን እርግጠኞች መሆን አለብን። በአማራው ክልል ማንም ድርጅት ሳይቀሰቅሰው ሕዝቡ ራሱን በጎበዝ አለቆች ተደራጅቶ ለመብቱና ለነጻነቱ እየታገለ ነው። አርፍዶም ቢሆን የሕዝብ ትግል ማገዝ አንድ ነገር ነው። የሕዝብን ትግል ሃይጃክ አድርጎ፣ ህዝቡ ያደረገው እኛን ነን አይደረግነው እያሉ ማጭበርበር፣ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መሞከር ግን እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው።
(በዚህ አጋጣሚ በግንቦት ሰባት ዙሪያ በምንሰጣቸው አስተያየቶች ደስተኞች ያልሆናችሁ ካላችሁ፣ ራሳችሁን unfriend በማድረግ ደስታችሁን ላለማወክ ሞክሩ። ጽሁፎቻችንን እንድታነቡ አላስገድናችሁም። ስለዚህ የመጻፍ መብታችንንም አክብሩ። ያመንበትን እንጽፋለን። በሰለጠነ መልኩ ለሚቀርብበን ትችትና ተቃዉሞ አክብሮት አለን። ለተሳዳቢና ለባለጌ ቦታ የለንም። )

No comments:

Post a Comment