በማሰር ወኔውን ሊሰብሩ ቢሞክሩም አይሆንላቸውም –
የማታወቁት ካላችሁ ፣ ኤሊያስ ገብሩ ይባላል። ኢትዮጵያ ነው የሚኖረው። ጋዜጠኛ ነው። ቀደም ሲል የአዉራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ነበር። ከዚያ በአንድነት ፓርቲ ኤዲቶሪያ ቦርድ በሚዘጋጀው የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ አዘጋጅ ነበርም ከሌላው አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ እጆቹ በወያኔ ታጣቂዎች በድብደባ ከተሰበሩበት ከስለሺ ሃጎስ ጋር።በቅርቡ አዲስ ገጽ የምትባል ግሩም መጽሔትን በዋና አዘጋጅነት ጀመሮ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪ በአገራችን አሉ ከሚባሉት የታወቁ ጦማሪያን ( Bloggers)መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው። በተለያዩ የአገሪቷ የፖለቲክ፣ የኢኮኖሚ፣ የማሀብረሰባዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሳይፈራ፣ ሳይሸማቀቅ የሚጽፍ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በአገራችን አሉ ከሚባሉት የታወቁ ጦማሪያን ( Bloggers)መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው። በተለያዩ የአገሪቷ የፖለቲክ፣ የኢኮኖሚ፣ የማሀብረሰባዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሳይፈራ፣ ሳይሸማቀቅ የሚጽፍ ነው።
በተለይም ወጣቱና አንጋፋው ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው በጠና በታመመ ጊዜ ፣ ሃብታሙ አያሌው የሕዝብ ልጅ እንደመሆኑ፣ የጤንነቱን ሁኔታ በየጊዜው፣ ከዳንኤል ሺበሺ ጋር ሆኖ፣ ያቀርብልን የነበረ ወጣት ነው።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ጋዜጠኝነት፣ መጦርመር ወንጅል በመሆኑም ጋዜጠኛ ኤሊያስ በአሁኑ ወቅት በሕወሃት ታጣቂዎች ታፍኖ ተወስዶ በወህኒ ይገኛል።
ኤሊያስ ገበሩ አንድ ጊዜ በሚያዘጋጀው መጽሄት ፣ ጌታቸው ረዳን. ጃዋርን ቃለ መጠይቅ አድርጎ አቅርቧል። ሰዎችን “እንዴት ?” ሲሉት ቀላልና ፕሮፌሽናል መልስ ነበር የመለሰው። የኔ ሥራ ሁሉንም ማስተናገድ ነው። ከዚያ አንባቢያን የራሳቸውን አቋም ይወስዳሉ ነበር ያለው። እንደ ኤሊያስ አይነት የራሳቸውን ሰዎች ቃለ መጠይቅ የሚያደርግን ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛን ነው ወያኔዎች ያሰሩት።
በጣም የሚገረማው ከማሰራቸው በፊት የወያኔ ደህንነት ሲሰራ የነበረውን አሳፋሪ ተንኮል ነው። ኤሊያስ ተከራይቶ የሚኖርባት አንዲት ክፍል አለች። ከአከራዮቹ ጋር በጣም ጥሩ ቅርበት ነው የነበረው። ምንም አይነት ጸብ የለውም። የቤት ኪራዩን አስቀድሞ የብዙ ወራቱን የከፈለው። አንድ ቀን አከራዮቹ መጡና እንዲለቅ ጠየቁት። እየከበዳቸው። የወያኔ ደህንነቶች ቀበሌ ድረስ በመምጣት አከራዮቹን ስላስፈራሩ።
ኤሊያስ ግን አልተበገራቸውም። መንገድ ላይ፣ በረንዳ ላይ አድራለሁ እንጅ መጻፌን፣ መናገሬን አላቆምም አለ። ይኽው በመጨረሻ ወደ ወህኒ ወሰዱት።በወህኒ መንፈሱን ለመስበር። ግን አይሆንላቸውም። የኤሊያስ ልብ የበለጠ ይጠክራል እንጂ አይሰበረም።
ኤሊያስ ግን አልተበገራቸውም። መንገድ ላይ፣ በረንዳ ላይ አድራለሁ እንጅ መጻፌን፣ መናገሬን አላቆምም አለ። ይኽው በመጨረሻ ወደ ወህኒ ወሰዱት።በወህኒ መንፈሱን ለመስበር። ግን አይሆንላቸውም። የኤሊያስ ልብ የበለጠ ይጠክራል እንጂ አይሰበረም።
No comments:
Post a Comment