Tuesday, December 6, 2016

ብአዴኖች ጠንካራ አቋም መዉሰድ ባለመቻላቸው እየተበሉ ነው


ብአዴኖች ጠንካራ አቋም መዉሰድ ባለመቻላቸው እየተበሉ ነው
የህወሓት አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ህዝባዊ ትግል ይደግፋሉ ብሎ የጠረጠሯቸውን የብአዴን አመራሮችን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል። የአንገረብ እስር ቤት ሀላፊ የእንፍራንዙን ተወላጅ ኢንስፔክተር አየልኝን አርብ ህዳር 23/2009 ዓም ሕወሃት ማሰሩ ተረጋግጧል። የዕስሩ ምክንያት ኮ/ል ዘዉዱን ፍርድ ቤት ሲቀርብ ደህንነቶች”ለምን በካቴና አስረህ አታቀርብም?” ብለው ሲጠይቁት “ምን አገባችሁ? ካመለጠ የምጠየቀው እኔ ነኝ” ብሎ መናገሩ እና ኮ/ል ደወቀ ዘውዱን ለህወሓት ተላልፎ እንዳይሰጥ ማድረጉ ሣይሆን እንዳልቀረ ይታሰባል።
በሌላ በኩል በወልቃይት ጉዳይ ጠንካራ አቋም እንደነበራቸው የሚገመቱ በርካታ የብአዴን ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
1.ግዛት አብይ የቀድሞው የዞን አስተዳደር እና የብአዴን ማዕከላዊ ምክር ቤት አባል
2. አገኘሁ ተሻገር የቀድሞው የዞን አስተዳደር የብአዴን ማዕከላዊ ምክር ቤት አባል
3. ሙሉጌታ ወርቁ የዞኑ አስተዳደር መኳንንት
4. ም/ል የዞኑ አስተዳዳሪ በሁሉ አንተነህ
5. የዞኑ የት/ት መምሪያ ሀላፊ የሻንበል ፀሀይ የክልሉ የግብርና መምሪያ ሀላፊ
በኪራይ ሰብሳቢነት ሰበብ በሚል ከሀላፊነታቸው ተባረዋል። በቅርቡ ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ይጠበቃል። በምትካቸው ለሕወሃት የበለጠ ታማን እየተተኩ ነው። ከህወሓት ጋር መስራት መጨረሻው ከዚህ አያልፍም ፡፡ Girma Kassa

No comments:

Post a Comment