Monday, August 8, 2016

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተነሳው አለመግባባት ቅራኔ ፈጥሯል።


በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተነሳው አለመግባባት ቅራኔ ፈጥሯል። 
 ከኬንያ የድንበር ኣከባቢና ደቡብ ሱዳን ቅጥረኛ ወታደሮችን ገዝተን ማሰራት እንችላለን ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ያደረግነውን በመከላከያ ውስጥ እንደግመዋለን የሚሉ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በሰሜን እዝ እና ምእራብ እዝ ከሚገኙ ወታደሮቻቸው ጋር በተነሳው ኣለመግባባት ቅራኔ መፈጠሩን የወታደራዊ ደህንነት ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል፥ ጉዳዩ የከረረ መሆኑ ለሕዝቡ ትግል ኣንድ እመርታ ያሉት ምንጮቹ የሃገር ውስጥ የተቃዋሚ ሃይሎች ስልታቸውን እንድፈትሹና እንዲቀይሩ ኣስፈላጊ ወቅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የወታደራዊ ደህንነት ሱፐርቫይዘሮች የሆኑ ምንጮች በኣማራ ክልል የተነሳውን የሕዝብ የለውጥ እና የመብት ጥያቄ ተከትሎ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ለመገምገም በተሰማሩበት የምእራብ እዝ እና የሰሜን እዝ ውስጥ ያለው ሁኔታ ኣደገኛና ሰራዊቱ ማብራሪያ በተከታታይ እየጠየቀ የሕወሓት መኮንኖችን መረበሹን ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። በማስፈራሪያና በዛቻ ተከበን ማገልገል ኣንፈልግም ወደቀያችን መልሱን የሚሉ ወታደሮች እየበረከቱ የመጡ ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል የተቀጠሩ ወታደሮች በይበልጥ ሰራዊቱን መልቀቅ እንፈልጋለን በማለት በሕወሓት መኮንኖች ላይ ጫና እየፈጠሩ በመገኘታቸው ኣለመግባባቱ በርትቶ ቅራኔዎች እየሰፉ መምጣታቸው ታውቋል። 
Image may contain: text

No comments:

Post a Comment