Tuesday, August 2, 2016

ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል!!


ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል!!
የዐማራ ተጋድሎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው!!
የዐማራ ተጋድሎ ታቦር ተራራ አናት ላይ ሆኖ ደብረ ታቦርን እየጠራ ነው፤ ውዶ አሞራገደል፣ አፈረዋናት፣ እብናትና በለሳን፣ ከምከም ቃሮዳን እስከ መልዛ ድረስ ተነስ! ተራመድ እያለ ነው፡፡ አቤት ቅዳሜ የቴዎድሮስ አደባባይን ያየ ሰው?! ጋዜጠኞች ኢየሱስ ተራራ አናት ላይ ሆናችሁ ቅዳሜ ደብረ ታርቦርን ተመልከቱ!!
በአጅባር ሜዳ፣ በቴዎድሮስ አደበባይ የፋርጣ ፈረሶች ጌቶቻቸውን ይዘው ተሸልመው ደምቀው ይውላሉ፡፡ ዐማራነት ይዘከራል! የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ይሆናል፡፡
ጨጪኾ አምባ ላይ ሆኖ ‹‹አምበሳው ጋይንት ኧረ ምነው ዝም አልክ?›› ሲል የዐማራ ተጋድሎ ድምጽ እስከ ተከዜ ወንዝ በርሀ፣ እስከ ጉና ተራራ አናት፣ ወገዳ፣ ሦስቻምና ሙጃ፣ አርብ ገበያ ቤተልሔም ድረስ ተሰምቷል፡፡ ክምር ድንጋይና ጋሳይማ የሐሙስ ወንዝን ገበሬ ይዘው ከመከሩ ከርመዋል፡፡ ሞክሸዎችን ማን ብሏቸው ለዚህማ!!
እስቴ ዴንሳ ተራራ ሥር ያለችው መካነየሱስ ከተማ ጥሪዋን ለእሁድ ካስተላለፈች ሰንብታለች፡፡ ሰባራ ድልድይ ድረስ ከተሰማ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ የባየ ግራር ሜዳ እንዴት እንደናፈቀኝ እኮ!!
መቄት ዋድላ ደላንታ ይቀጥላል፤ መርጦ ኢየሱስ ላይ የሚሆን ሰው የዋድላና ደላንታ፣ የየጁን ባላባቶች ድምጽ ከመቻሬ ሜዳ ይሰማል፡፡ ራያ ራዩማ፣ ወሎን በፍቅር ለሚይዘው እንጅ በማንነቱ የሚመጣውንማ መቼም ታግሶ አያውቅም! በወልድያ ሰርጥ አልፎ ቆቦ ማዶ ራያ ይደርሳል! ድምጻችን የወያኔን ዙፋን ያርበደብዳል!
ያች ምድር ያች፤ መርሳ አባ ጌትየን አልፋ ያለችው አዎ ውጫሌ ጣሊያን እንደሸወደኝ ለወያኔማ አልሸወድም እንዳለች ሰምቻለው፡፡
ጦሳ ተራራ ላይ ሆኖ የዐማራ ተጋድሎ እየተጣራ ነው፤ ኧረ ሞረሽ እያለ ነው!? ጦሳ ተራራ ላይ ሆኖ ኮምቦልቻ ብትል ሀይቅ፣ ተንታ ብትል አምባሰል ከየትኛውም ቦታ ሁሉ ጥሪያችን ከእኛ አገር ኔት ወርክ ቀድሞ ይነሳል፡፡
(የደብረ ታቦርንና የእስቴን ሰልፍ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ይዤ እቀርባለሁ)
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!
ይህ ሁሉ ግን የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!

No comments:

Post a Comment