ስብሃት ነጋ ከዚህ ቀደም የተበደለ ሕዝብ ማመጹና መነሳቱ እንደማይቀር በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ ተናግሮ ነበር። ህወሃቶች ይህ የመስራቻቸውና የመሪያቸው ንግግር የሚሰራው ለትግራይ ብቻ እንጅ ለሌላው እንዳልሆነ ባለፈው 25 ዓመታት በኢትዮጵያዊያን ላይ ከፈጸሙት ግድያ፣ ስቃይ፣በደልና ግፍ ለመረዳት ይቻላል። አማራ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ጋምቤላና ሌሎችም ኢትዮጵያዊያን እያሉ ያሉት በህወሃት ተበደልን፣ ተጨቆንን፣ ተጨፈጨፍን፣ ተዘረፍን ነው። ሕዝብ“ተበድያለሁ” ብሎ ሲያማርርና ብሶቱን ሲናገር በዳዩና ጨቋኙ “አልተበደልክም” ብሎ መናገር የህወሃቶችን ጭፍነነትና አረመኔነትንና እራስ ወዳድነን ብቻ የሚያረጋግጥ ነው። ታዲያ ለምንድነው ሕወሃት ከዓለም ታሪክ ውጭና ከነባራዊ ዕውነታ ውጭ የወጣው? የህወሃት ነገር ወሬ ሌላ ተግባር ሌላ ነው። ስብሃት ነጋ በራሱ አንደበት የሚከተለውን ተናግሮ ነበር። ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱና የራሳችሁን ትዝብት ውሰዱ።
- አንድ ህዝብ ታምቆ ማለትም ተጨቁኖ ለዘመናት አይቆይም
- አንድ ህዝብ፣ እንደ ሕዝብ መጠን በዓለም ታሪክ እንዳስቀመጡትና እንደፈለጉ የሚቀመጥ አይደለም፣ ሲመረው ይፈነዳል
- ይህ “ዩኒቨርሳል ትሩዝ” ዓለም አቀፋዊ እውነታ ነው። ሲመረው የማይነሳ ሕዝብ የለም። በዓለ ታሪክ አሁንም ለወደፊትም….
No comments:
Post a Comment