የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ፣በአገዛዙ ስርዓት ለእስር ተዳረገ!!! .
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርግ የነበረው፣ እንዲሁም አንድነት ፓርቲ በአገዛዙ ሥርዓት ሲፍረስ የጀመረው ሰላማዊ ትግል ለመቀጠል በቀጥታ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን፤ የፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ በመሆን ፓርቲውን እያገለገለ ይገኛል።
ቅዳሜ ሐምሌ 30 /2008 ዓ.ም የአገዛዙ የደህንነት ሰራተኞች፤ በቁጥጥር ሥር ያዋሉት ሲሆን፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ የ5 ቀን ቀነ-ቀጠሮ ተሰጥቶበታል። የቀረበበት ክስ ከሰሞኑ ከሚደረገው አገር አቀፍ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ እንደሆነና፣ ” መረጃ በስልክ መለዋወጥን ” አስመልክቶ እንደሆነ ተገልጿል ። . ህዝባዊ ትግሉ ይቀጥላል፣ድል የህዝብ ነው!!!
No comments:
Post a Comment