Monday, August 1, 2016

ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ዐማሮች በባሕር ዳር ሰልፍ ይወጣሉ


ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ዐማሮች በባሕር ዳር ሰልፍ ይወጣሉ  Muluken Tesfaw
ቀጣይ እሁድ የነሐሴ መባቻ ዕለት ዐማሮች በባሕር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን የከተማ አስተዳደሩ ላይፈቅድ ይችላል፤ ግን ማንም አይቀርም፡፡ ከዳንግላ እስከ ወረታ፣ አዴት እስከ ጢስ አባይና ዘጌ ድረስ ያለ ዐማራ ማንም አይቀርም፡፡ ደቅ ደሴት ላይ የሚኖሩ ዐማሮች በጣናነሽ አርብ ማታ ይገባሉ፡፡
ቀጣይ እሁድ የይባብ ኢየሱስን፣ የመሸንቲን፣ የሰባታሚትን፣ የአንዳሳን፣ የወንዳጣን፣ የዘጌን፣ የዘንዘሊማን፣ የአቡነ ሃራን፣ የሮቢት ባታን፣ የሐሙሲትን፣ የአንበሳሜን … ዐማሮች ወደ ባሕር ዳር ይጎርፋሉ፡፡ የዐማራ ሕዝብ አንድነት ይዘመራል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ በጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ይሰተጋባል፡፡
ቀጣይ እሁድ የጢስ ዓባይ ዐማራ ገበሬ እንዲህ እያለ የሚሸልል ይመስለኛል!!
ዓባይ ጥቁር የመሰለ ከሰል የመሰለ፣
እየቀላ ሔደ ደም እየመሰለ፡፡
እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ተጣራ፤
እዚህ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ወይ አለው፣
ጎበዝ ተነቃነቅ ይህ ነገር የእኛ ነው፡፡
ወዲህ ወደ ጎጃም ሰው ላኩ ብያለው፣
ወዲህ ወደ ጎንደር ሰው ላኩ ብያለው፣
ወዲህ ወደ ወሎ ሰው ላኩ ብያለው፤
ወዲህ ወደ ሸዋ ሰው ላኩ ብያለው፣
የጦር ዳናን ሰምተው እንዳይቀሩ አውቃለሁ!!
ከዚህ ቀጥሎ የምትመለከቱት ምስል ለዐማራ ተጋድሎ በ2006 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ በወጣንበት ወቅት ነው፡፡
ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!

No comments:

Post a Comment