ምርጥ እና ምራጭ ለዩ – ኄኖክ የሺጥላ – …….
ብርሃኑ ነጋ የ 2016 ምርጥ ነው የሚሉ ምራጭ አስተስሰቦችን እያነበብን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው። ነው ብለን ብንነሳ ምርጥ የሚያደርገው ምንድን ነው ?
ጎንደር እና ጎጃም ትግሉ በፋመበት እና በተፋማማበት ሰዓት እሱ ከሌንጮ ጋር ሃገር ለሃገር መንሸራሸሩ ነው ምርጥ ያደረግው ? በዚህ ላይ ደም የሚያስተፋ መራጃ ማቅረብ እንችላለን ፥ ብዙ መፃፍም እንችላለን ፥ ያንን ሁሉ ሳናደርግ ግን ስለ እውነት የምናወራ ከሆነ በ 2016 ብርሃኑ ነጋ ይህንን ፥ ይህንን አድርጓል ፥ ይህንን ፈፅሟል ፥ በሉን ። የሰራውን ጥቀሱ ፥ የፈፀመውን አንሱ ! የተወደሰበት እና ከምራጭ ተርታ አውጦ ምርጦች ተርታ የመደበውን ጀብዱ ፥ ገድል ፥ ትግል እና ድል አስረዱን!!! እኛም ተቀብለን እናስተጋባላችሁ!!!
ብርሃኑ ምን ሰራ ? እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ አንድ 10 አመት በርሃ እንደ ኖረ ድርጅት ነው የምናየው ! እንደ ግለሰብም ቢሆን ኤርትራ መግባቱ መውጫ መግቢ በሌለው የተጨማደደ ወረቀት በሚመስለው ተራራ ውስጥ ዱር ቤቴ ብሎ የሚኖርም ሰው አይደለም ! ይህንን ለማድረግ ስለመቻሉም እጠረጥራለሁ!!!
እስኪ ብርሃኑ የጎንደር እና የጎጃም ልጆች ጎንደር እና ጎጃምን በተቃውሞ ሲያናውጧት ፥ የወያኔን መንበር ከስሩ ሲንጡት ብርሃኑ የናንተ ምርጥ ፥ ጥምረት ! ውህደት ! ሁለገብ ትግል ! እና ወዘተ እያለ ከመፎከር ውጭ ምን ሰራ ? የአማራን ተጋድሎ « የነፃነት ሃይሎች ትግል » በማለት ባልዋለበት የጀግኖች አማሮችን ትግል የኔ ነው ለማለት ደፋ ቀና ከማለት ውጪ ይህን ፥ ይህን ሰርቷል ፥ ይህን አድርጓል በሉን !!! አሳዩን እኛም ተቃውሟችንን አቁመን እንደግፋችሁ !!
ብርሃኑ ከገባው ቃል ፥ ከፉከራው ፥ ከአለሁ ማለቱ እና ወያኔም የሱን እና የድርጅቱን ሰም ደግሞ እና ደጋግሞ ከማንሳቱ አንፃር የሰራውን ረብ ያለው ነገር ንገሩን ? የጀግናውን ሻለቃ የገብርዬን እርቃን ሬሳ እንደ ዜና ከመለጠፍ ባለፈ ፥ አንዴ ተራራ ተቆጣጠርን ፥ አንዴ ድንበሩ ላይ ከልክ በላይ ሰራዊት ስላለ ትግል ማድረጉ አስቸጋሪ ነው ፥ ሌላ ጊዜ ደሞ ሌላ ምክንያት እያነሱ የት አላችሁ ፥ ምን ሰራችሁ ሲባሉ እየተሳደቡ ፥ እየዘለፉ ፥ በተራ ማጭበርበር ፥ ህሊናቸው በሸጡ ሰው መሳይ በሸንጎ ታጋዮች በመወደስ ፥ ባልነበረ እና ባልኖረ ነገር አርበኛ ሁኖ ለመታየት ፥ በደረሰበት አንቱ ፥ በሄደበት እርሳቸው ከመባል ውጭ ምን ሰራ ?
ምርጥ የሚያደርገውን አንድ ( ቢያንስ አንድ ተግባር ) ንገሩን ። የሞቀ ኑሮውን ትቶ በርሃ ወረደ የሚለውን የአዘቦት ዜና በማቅረብ ፥ ብርሃኑን የተለየ ሰው አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው የህፃን ልጅ ማታለያ ፕሮፖጋንዳ ከአሁን በኋላ ቦታ የለውም !
እነ ኢንጂነር ሃይሉ ሻወል ብርሃኑ ነጋ ከሰራው ስህተት አንፃር የጎላ ስህተት የሰሩ ሰዎች አልነበሩም ፥ ያም ሆኖ ሰውየው በተፈጥሯቸው የወረደ እና ርካሽ የፖለቲካ ቁማር ውስጥ ገብተው ፥ ክብረ ነክ በሆነ የ ገበያ ፖለቲካ ተወራርደው እና ወርደው ጠላታቸውን መጋፈጥ ባለመቻላቸው ብርሃኑ ልክ እርሳቸው ጥፋተኛ ሆኑ ። እድሜ ልኩን ደባ ሲፈጥምባቸው የነበሩት እኝህ ሰው ሲሞቱ ፥ ከልቡ ባልሆነ ፍፁም የፖለቲካ ስሌትን መሰረት ባደረገ ጉዳይ ብቻ « እኝህ ሰው ሲሞቱ የሃዘን መግለጫ ሰጠ » ። እሱን ተከትሎ የሱ ጀብራሮች ፥ እኔ በቅርብ ሃይሉ ሻወልን ሲሳደቡ የማውቃቸው ሁሉ ፥ አዝነናል አሉ !!! ይህንን ሰውነት እጠየፈዋለሁ ! ይህ የጭራቆች ስብስብ እንጂ ነፃ አጪ ለመሆን እንዴት ይቻለዋል ! የአማራ ህዝብ ፥ በደሙ ያገኘውን ክብር እና ትግል ለማንም ዳንዴ አሳልፎ በመስጠት የዕርሱ የሆነውን ትግል በሞግዚት ብርሃኑ ነጋ እንዲያስተዳድርለት አፈቅድም ! የአማራን ህዝብ በዚህ ጉዳይ ማንቃቱን እንቀጥላለን !
ምርጥ እና ምራጭ ለዩ !!!!
ኄኖክ የሺጥላ
No comments:
Post a Comment