Tuesday, January 3, 2017

የአዲስ አበባ እና የጅማ 19 ሙስሊሞች ላይ በደህንነት ሚመራው የካንጋሮ ፍርድ ቤት የ5 አመት ከ6 ወር እስራት ፈረደባቸው


✔እነ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን ልታስፈቱ ተንቀሳቅሳቹሃል ተብለው ተከሰው የነበሩት በከድር መሃመድ መዝገብ የተከሰሱ የአዲስ አበባ እና የጅማ 19 ሙስሊሞች ላይ በደህንነት ሚመራው የካንጋሮ ፍርድ ቤት የ5 አመት ከ6 ወር እስራት ፈረደባቸው

✔ሃስቢየላሁ ወኒዕመል ወኪል!!

በዛሬው ችሎት ሁለት 2 ጋዜጠኞቹን ጨምሮ በ19 ወጣቶች ላይ 5 አመት ከ6 ወር ፍርድ አስተላለፈ

ቢቢኤን ታህሳስ 25/2009

ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ እና ጋዜጠኛ ካሊድ መሃመድን ጨምሮ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተፈረደባቸውን ፍርድ ዝቅ አድርጎ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው በነ ኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱ 16 ሙስሊሞች ላይ በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ በግፍ የታሰረው ወጣቱ ሙጂብ አሚኖን ጨምሮ ከአዲስ አበባ እና ከጅማ የተያዙት19 ወጣቶች የፌደራሉ አቃቢ ህግ በፀረ ሽብር ህጉ 652/2001 አንቀጵ 7/1 በመጥቀስ በአሁን ሰአት የተፈቱትን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን ጨምሮ በሱ መዝገብ ተጠቅሰው የነበሩት 29 ኡስታዞች እና በቅርቡ ከእስር የሚፈቱትን በነኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱትን ወንድሞች እና ኡስታዞች በሃይል ከእስር ለማስፈታት ተንቀሳቅሰዋል፣ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት አሲረዋል፣ድምፃችን ይሰማ የሚል ወረቀት በትነዋል፣በታላቁ አንዋር መስጅድ እና በኑር መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ ሲያደርገው በነበረው ተቃውሞ ተሳትፈዋል እና መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቱዋል ብለዋል በማለት በሃሰት ከከሰሳቸው ቡሃላ ሃሰታዊ ማስረጃ እና በግድ እየደበደበ ያስፈረማቸውን የተከሳሽ ቃል ለፍርድ ቤት በማቅረብ የካንጋሮ ፍርድ ቤት ባሳለፍነው ግዜ ምንም አይነት ሃሰታዊ ምስክር ባልሰማበት ሁኔታ ተከላከሉ የሚል ብይን መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን ተከሳሾቹ በዚ ፍርድ ቤት አመኔታ ስለሌለን አንከላከልም በማለታቸው ጥፋተኛ የሚል ፍርድ መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት የካንጋሮ ፍርድ ቤት በሁሉም ወንድሞች ላይ የ5 አመት ከ6 ወር እስራት እንደፈረደባቸው ታውቁዋል በዚሁ መዝገብ በሃሰት ተከሰው ሲያበቁ ባሳለፍነው ግዜ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥለዋል ተብለው ከተከሰሱት 38 ንፁሃን ተከሳሾች ውስጥ የሚገኙት 3 ጀግኖች በአሁን ሰአት በጨለማ ቤት የሚገኙት ሚገኘበት እነዚህንም ጨምሮ ሁለም ላይ የ5 አመት ከ6 ወር ፍርደ ገምድል ፍርድ አስተላልፉዋል

በዛሬው ዕለት ህዝበ ሙስሊሙ በፍርድ ቤት በመገኘት አጋርነቱን እንዳሳየም ታውቁዋል

ሃስቢየላሁ ወንዕመል ወኪል

No comments:

Post a Comment