Friday, January 6, 2017

ጥያቄው ምን ላይ ትተኙ ነበር ሳይሆን በ 10 አመት የኤርትራ ቆይታችሁ ምን ሰራችሁ ? ኄኖክ የሺጥላ


ጥያቄው ምን ላይ ትተኙ ነበር ሳይሆን በ 10 አመት የኤርትራ ቆይታችሁ ምን ሰራችሁ ? — ኄኖክ የሺጥላ —
ሰውየው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው ጥያቄ ይጠይቁታል
ዳኛው ፡ ጌታው እስቲ ስለራስህ ንገረን
ተከሳሽ ። ምን ጌታዬ እኔ ድሮ ቄስ ነበርሁ አሁን ግን ቀን ጥሎኝ ሽፍታ ሆኛለሁ
ዳኛው ። ምነው ጌታው የኋላውን ወደፊት አዞርኸውሳ ! 
ተከሳሽ ፡ እኔንም የሚገርመኝ እሱ ነው !
እና ምን ለማለት ነው ••• ግንቦት ሰባቶች በድል አጥቢያ ሊነገር የሚገባውን ነገር ኩርማን መሬት ሳይዙ መፎከሪያ አደረጉት ! እርግጠኛ ነኝ እነሱንም የሚገርማቸው ይመስለኛል !!! ጉዳዩን በአዲስ መስመር ላብራራው መሰል•••
ግንቦት ሰባት እንደ ወያኔ ከስህተቱ መማር የማይችል ድርጅት ነው። የገደልከውን አንድ አጋዚ አሳየን ስንለው ፥ ሰሌን እና ብርድ ልስብ እንደ ትልቅ ጀብዱ እየተቀባበሉ ያሳዩናል ። ይህንን የለጠፋችሁትን ሰሌን እና ብርድልብስ አጥቶ እርቃኑን የሚተኛ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ እንዳለ ብታውቁ ኖሮ ይህንን ባላደረጋችሁ። ረጅም ጦር ባይወጉበትም ማስፈራሪያ ነው ነው የሚሉት ! ጥያቄው ምን ላይ ትተኙ ነበር ሳይሆን በ 10 አመት የኤርትራ ቆይታችሁ ምን ሰራችሁ ? እንድትመልሱልን አይደለም የምንጠይቀው ! ሃሳቡን በሙሉ ስድብ የዘረፈው መልስ ከየቱ !!! እንዴት ሆኖለት ???!!!!
በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ትምህርት ውስጥ ጎልቶ የሚነገር የትምህርት ዘርፍ አለ ፥ በዚህ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ስለ ትራንዚስተር ሲነገር PNP እና NPN junction የሚባሉ የአቀማመጥ ( አሰላለፍ ) ስልት ያላቸው የድርቦሽ ( wafering ) ዘዴዎች አሉ ። በዚህ ትምህርት ( ፊዚክሱም እንደሚነግረን ) ፥ የቀዳዳዎች እንቅስቃሴ ( the movement of holes ) የ ግንኙነት ( electrical conductivity ) ምንጭ እንደሆነ ነው። አንድ ጥሩ ተማሪ ታዲያ ቀዳዳ ምንም ነው ፥ ታዲያ ምንም እንዴት ይንቀሳቀሳል ብሎ ጠይቋል ( A hole is nothing and how can nothing moves ???)…..ስለ ግንቦት ሰባት ሳስብ የዚህ ብልህ ተማሪ ጥያቄ ሁሌም ወደ ህሊናዬ ይመጣል።
አንዳርጋቸው ይተኛበት የነበረውን ሰሌን እንደ ጀብዱ እየለጠፉ እኛ እንዲህ ነን ማለቱን ዛሬም እንደ አንድ ሁነኛ የትግል ስልት የሚያዩት የግንቦት ሰባት ደጋፊዎች የሚያደርጉትን ነገር ቆም ብለው ለማሰብ የወደዱ አይመስልም ። እዚያ ሰሌን ላይ ይተኛ የነበረው ሰው አንዳርጋቸው ነው። እዛ ሰሌን ላይ ተኝቶ ፥ በኤርትራ ሃሩር ላይ እንጨት ፈልጦ ፥ መከራውን ያየበት ትግል እንዳች ነገር ጠብ አላለውም ። ስለዚህ ይመርመር ነው ያልነው ። ይህንን ሁሉ ዋጋ የከፈለው ሰው ዛሬ ወያኔ እስር ቤት ነው ያለው ነው ያልነው ። እንዴት ሊታሰር ቻለ የሚለውም ይመርመር ነው ያልነው ።
የናንተ አካሄድ ሰሌኑን መስቀል ነው እንደማለት ይመስላል ። ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል አንገታችን ላይ የምናደርገው በመስቀሉ እኛ ክርስቲያኖች ድነናል ፥ ነፃ ወጥተናል ብለን ፍፁም ስለምናምን ነው ። የናንተ አካሄድ ደበሎውንም ፥ ሰሌኑንም ፥ ብጣቂ ብርድልብሱንም ማተብ አድርጉት ስለሚመስል ነው ። ራሳችሁን ፈትሹ!
ስለ ego ( ራስ ወዳድነት ልበለው ) ያም ይሄም እየተነሳ ይዘባርቃል ። የሚገርመው አንዳቸውም ራስ ወዳድነት ተፈጥሯዊ መሆኑን አለመራዳታቸው ነው ። በሳይንሱ ምናልባት ቃሉን ልቀይርላችሁ ፥ narcissist የሚባል አለ ፥ ይኽኛው ውድ ኢጎ ነው። ዋናው ነገር ራስን መውደድ ወይም መጥላት አይመስለኝም ፥ ዋናው ነገር ራሱን የሚወድ ሰው ራሱን አሳልፎስ መስጠት ይችላል ወይ የሚለው ነው። በብእር ስም ተደብቆ የሚሳደብ ሁላ ስለ ሌላ ሰው ራስ ወዳድነት ሲያወራ ይገርመኛል !
እግዚያብሔር ሰውን በአምሳሉ የፈጠረው የራሱን መልክ ( ማንነት ስለሚያፈቅር ) አይደለምን ? ታዲያ ይህ የአምላክ በሃሪ የሆነው ነገር የሰው ልጆች በሃሪ ቢሆን ምኑ ይገርማል ? ራስ ወዳድ መሆን አይደለም ቁም ነገሩ ፥ ቁም ነገሩ sociocentric ነህ ወይስ አልቦ ራስ ወዳድ ነህ የሚለው ይመስለኛል ! አሁንም ትልቁ ችግር ይቺን አንድ ቃል እንግሊዘኛ ( ኢጎን ማለቴ ነው ) ከማገለባበጥ ቃሉ ምን ማለት ነው በእውነት የሚለውን ማጤን ይጠቅማል ። ራሱን ጥሎ ፥ ጢሙን አጎፍሮ ፥ የሌሎችን ጢም በነጣ ሲያስተካክል እንደሚውል ጠጉር ቆራጭ ወይም እንደ ሲደሃርታ ( ወይም ቡድሃ ) ፥ ከቤተ መንግስት ወጥቶ የእውነትን ምንነት ለመረዳት እንደሞከረው ፥ ወይም እንደ ዲዮጋን የመጨረሻ ንብረቱን ( የውሃ ቅሉን ) ሳይቀር ጥሎ ፥ ሃብቴ ተፈጥሮዬ ነው እንዳለው ብንኖር እንኳ ፥ የዚህም አይነት ኑሮ ምርጫው እራስን ከመውደድ የመነጨ መሆኑን የማያውቅ መንጋን ማስረዳት እጅግ ፈታኝ ነገር ነው !
ኄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment