Monday, January 23, 2017

እንጀራዬን በአዲስ ትሪ (አሰገደች ቶሎሳ)

   


እንጀራዬን በአዲስ ትሪ (አሰገደች ቶሎሳ)
አሰገደች ቶሎሳ
አሰገደች ቶሎሳ
መቼም ዘንድሮ ጆሮአችን የማይሰማው፣ዓይናችን የማያየው የለው የኸው ደግሞ የወያኔ ካሚኔ የጭንቁን አዋጅ አውጆ፣የኢንተርኔት መረበን ዘግቶ የሚታፈሰውን አፍሶ፣ የሚተሰረዎን አስሮ ና የሚገደለውን ገድሎ ከጨረሰ በኃላ በፖርላማዬ ተቀምጨ ለአገር የሚበጅ ብልሀት መከርኩ ይለናል።
መምክራቸው ባልክፋ ነበር ማፅደቃቸው ግን አሁንም ፅኑ አቋማቸው አሳብቋል። እንድ ወዳጅ ድሮስ በገዥው የተተከለ አሁን ደግሞ ራሱ አፀደኩ ሲልህ አበጅህ ከማለት ሌላ ምን ምርጫ አልህ ብሎ ማለቱ ዕወነት ብሏል።
ይህንንማ መቺ አጣነው የህዝብን እኩልነት የሚያረጋግጥና እውነተኛውን ነፃ ዲሞክራሲ ሚያጐናፅፈን መንግስት ካቢኔነት ተነቅሎ ሌላ ይተካል አልን እንጂ…? የተተከለውን መቺ አፅደቀልን አለን   ካቢኔነቱ ባለፈው ሀያ አምስት ዓመት እየተከለ፣እየበላ ፣እየጠጣ ብሎም እያደለበና እያፅደቀ ለሰፊው ህዝብ ጠብ የማይል ፍሬን ሳይስጥ መቆየቱ ከመንቀል ሌላ አማራጭ እንደሌለው ዛሬ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል።
አቶ ኃይለማሪያም የሰላም ችሎታቸውን ከቅርብ ግዜ በፌት በዳንስ ትርኢት እንዳሳዩን አስታውሳለሁ ዛሬ ድግሞ አሻሽለው በዕርግጥ አንባቢው እንጅ አፅዳቂው እሳቸው ባይሆኑም የሚኒስተሮችን የስልጣን ሰለሜ ስም እየጠሩ ሲያሽከረክሩ ውለዋል።
አይመጣም ገንፎ ከሜቴ ተርፎ እንዳለቸዋ አገልጋይ ካቢኔቱ አዲስ ትሪ ቀየረልን እንጂ የሚበላውንም የሚረግጠውንም የሚቀይር ሆኖ አልተገኘም። የአባገነን መንግስታት የስልጣን ፍፃሜ ዕርምጃ በእጅጉ ተመሣሣይ ነው ። በመሆኑም የዛሬው የካቢኔነት ስያሜ ለስፊው ህዝብ የሚፈይደው ፋይዳ ባይኖርውም ለትግሉ ግን የምንግስቱን ግራ መጋባት አመልካች ነውና ትልቅ ምራፍ የድል ጉዞ መሆኑንም መርዳትየሰፊው አማራ ፣ ኦሮሞና የደቡብ ህዝብ ጥያቄና የትግል ጉዞ እንዲህ በ አደባባይ እያየ ህዝቦች ማንኞውንም ጥያቄአቸውን ካቀረቡ መንግስት እንደቀደመው ሁሉ መፍት ሄውን ለምስጠትና ባግባቡ ለዳኘት ዝግጆ ነው ይለናል
ዳኛው ዝንጆሮ ፍርድ ቤቱም ገደል
እምን ላይ ተኩኖ ይነገራል በደል
እንዳሉ እንደ እብድ ውሻ በየ ጐዳናው እየተገደለ በየ እስር ቤቱ በዳቦ በእሳት እየጋየና እየተጐረ በሶቱን ለማን እና በምን ሁኔታ እንደሚናገር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በሚቀጥለው የፖርላማ ስብሰባና ኮማንድ ፖስት አዋጃቸው ይነግሩን ይሆን በየተኛው ሀገር ታሪክ በግድና በ አፈና ጥቂት ግዜን የከረመ እንጂ የፈለገውን ውይም የተመኘውን ያህል የቆየ መንግስትን አለየንም የሰፊ ህዝብ ድምፅ ሊመጣ ላለው ደራሽ ጐርፍ የማስጠንቀቂያ ነጐድጓድ ነው ተገድቦ ሲቆይ ኃይሎ ይጨምራል ይልቁኑም ተጠናክሮ የመጣል እንጅ ወደ ኃላ አያፈገፍግም።
ወያኔ እራሱ የተከለውን አፅድቆ ቀጥሎም ኮማንድ ፓስት ብሎ የክልክላ አዋጆን ባወጀብን በዚህ ጥቂት ግዜያት ውስጥ እንኳን በርካታ ወገኖቻችን የ አዋጆ ሰለባ ሆነዋል
ታዋቄ የነበረው የኡጋንዳው አምባገነን መሪ ኤዲ አሚን        ባታከብርኝ ችግር የለውም አገዛዙን መፍራት ግን ግዴታህ ነው እምቢ በልህ ምኑንም ያህል ብትሮጥ ከምተኩስው ጥይት በላይ አትፈጥንም  ብሎ እንዳለ ዛሬም የኛዎም መቃወም በቻ ሳይሆን አብሮ መቀመጥ አብሮ መስራትና አብሮ መኖርንም በ አዋጅ ከልከለውናል። በጠያፍ ድርጊታቸው እንዳልተከበሩ ቢያውቁቱም ያዛለቃቸው ይመስል ማስፈራራታቸውን ግን ቀጥለውበታል።
ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እና የርበኞች ግንቦት ፯ ቱ ፕሮፊስር ብርሀኑ ነጋ በ አንድ አዳራሽ መቀመጣቸው ይሆን ሰውዬውን ተጠያቂ ያደርጋቸው? እንግዲህ ተቃውሞ እንደ ተላላፌ በሽታ እንዳይዛመት መንግስታችን በነፍስ ወከፍ አዳራሽና ወንበር ብሎም መጓጓዥና ማደሪዎችንን እስከሚያዘጋጅልን ደረስ በተሰመረልን ርቀት ሆኖ መጠበቀ ግድ ሆንዋል  ወያኔ አልገባውም እንጄ የነፃነትና የኢዮጵያዊነት ፅናታታችን ያለው በደማችን ውስጥ ነው መቼውንም ከነ አቶ ኃይማርያም የፓርላማ ተከላ፣ነቀላና የ አዋጅ ጋጋታ የሚጠበቀው ቀቢፀ ተስፋ የለም። የትሪው መቀያየር ለእንጀራው ጣዕም የሚጨመረው ፋይዳ የለውም ይልቁኑም ህዝብ እያለ ያለው አገዛዙ ከስሩ መነቀል አለበት የተገባ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች።

ቸር ይግጠመን

No comments:

Post a Comment