Wednesday, January 11, 2017

የጥምቀት በአል በጎንደር አሳሳቢ ሆኗል!

የሚከተሉት ከጎንደር ህዝብ የተሰባሰቡ ሃሳቦች ናቸው!
ለተመሳሳይ ውሳኔ መልእክቱ ለጎጃም ህዝብም ተልኳል!
#ወያኔ ህዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ ሊጠቀምበት ይችላል።
#የጎንደር የሃይማኖት አበው ሊቃውንት በጎንደር ታሪክ መስቀል አደባባይ እንዳይከበር የወሰኑት ለህዝቡ ደህንነት ብለው ነው!
#መንገድ ጠርገው ምንጣፍ አንጥፈው ታቦት የሚያጅቡት ወጣቶች በጅምላ ታስረው እንዴት በአል ይከበራል?! በየመንገዱ የፈሰሰውን የወገኖቻችንን ደም እረግጠን አንሄድም።
#በቱሪስት ድርቅ የተመታውና ጎንደር ጦርነት የለም ለማስባል ወያኔ በአሉ እንዲከናወን ይፈልጋል ካህናቱ ላይም ጫና ለመፍጠር ደፋ ቀና እያለ ነው።
#የሃገረ ስብከቱ ዋና አለቃ ለምን ኮከብ የሌለው ባንዲራ ሰቅለው ስብሰባ መሩ ተብለው ባህር ዳር በእስር ቤት እያሉ እንዴት በአል ይከበራል?!
#ለህዝብ ነፃነት እየተሰው ያሉ ውድ የገጠሩ ወገን የሌለበት ጥምቀት እንዴት ይከበራል?!
#በጎንደር ህዝብ ላይ ወያኔ የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝ ዘንድሮ ጥምቀትን እንደመስቀል በአል በየ አጥቢያ አብያተ ክርስትያናቱ ማክበር አለብን የሚለው ሃሳብ ጎልቶ ወጥቷል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment