ሰሞኑን በጎጃም እና በጎንደር በደረሱ የቦምብ ጥቃቶች ሆን ብሎ በመፈጸም የሚከሰሰው የሕወሃት መንግስት የሚያዘው ኮማንድ ፖስት ጥቅምት 11 በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስታወቀ::
በጎንደር ሰላማዊው ሕዝብ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በቤቱ ለማሳለፍ ውስጥ ለውስጥ እየተነጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት ሕዝቡ የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት በቢሾፍቱ ኢሬቻ በዓል ላይ የፈጸመው ዓይነት የዘር ማጥፋት አሸባሪዎች አደረጉት ብሎ ራሱ የጎንደርን ሕዝብ ለማጥፋት ጥቃት ሊፈጽም ይችላልና ከቤት ሳንወጣ ጥምቀትን ቤት እናሳልፋለን እያለ ነው::
ሕዝቡ የሕወሓት መንግስት በአሸባሪዎች አመካኝቶ ጥቃት ያደርስብኛል እያለ ባለበት ወቅት ኮማንድ ፖስቱም በሌላ በኩል በጥምቀት በዓል ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እየተከታተልኩ ነው ሲል መግለጫ ማውጣቱ በሕዝቡ ዘንድ የነበረውን ስጋት ይበልጥ አግሎታል::
የሕወሓት ኮማንድ ፖስት ሰሞኑን በባህርዳር እና በጎንደር የተፈጸሙት የቦምብ ጥቃቶች የተከናወኑት በጥምቀት በዓል አሸባሪዎችና ጸረ ሰላም ኃይሎች ጥቃት እንዳያደርሱ እያጣራሁ ባለሁበት ወቅት ነው ብሏል በመግለጫው::
“የሽብር ጥቃቱ ኮማንድ ፖስቱ በጎንደር ከተማ ጥር 11 ቀን 2009 ላይ በድምቀት በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ በሰላማዊ ህዝብ ላይ አደጋ ለማድረስ ዝግጅት ያደርጉ የነበሩና ከአሻባሪና ፀረ ሰላም ሀይሎች ጋር ትስስር ያላቸው የወንጀል ቡድኖች ላይ ዝርዝር ጥናት በማካሄድ እርምጃ መውሰድ በጀመረበት ወቅት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ተችሏል” የሚለው የኮማንድ ፖስቱ መግለጫ ሕዝቡ በሕወሓት መንግስት ሆን ተብሎ በጥምቀት በዓል ሊፈጸምብኝ ይችላል የሚለውን ስጋቱን ይበልጥ በማዳበሩ አሁንም ለጥምቀት በዓል አደባባይ እንዳይወጣ የሚደረገውን ቅስቀሳ እንዲጠናከር አድርጎታል::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት ከዚህ ቀደም ኦነግን ለመወንጀል በዋቢ ሸበሌ በትግራይ ሆቴል በብሎቶብስና በተለያዩ ቦታዎች ራሱ ቦምብ አፈንድቶ በኦነግ ላይ ማሳበቡ አይዘነጋም:: በተደጋጋሚም ራሱ ወንጀል ሰርቶ በተቃዋሚዎች እና በኤርትራ በሚደገፉ ኃይሎች ላይ ሲያሳብብ መክረሙ በተደጋጋሚ ሲጋለጥ የቆየ ሃቅ እንደሆነ ይታወሳል::
የአሜሪካ መንግስት ከወዲሁ ዜጎቹ ወደ ጎንደር እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱንም ዘ-ሐበሻ ማስነበቧን ልብ ይሏል::
No comments:
Post a Comment