አሁን ባለንበት ዘመን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በአጠቃላይም ለአገራችን ሰላም፣ አንድነት፣ ፍትህና እኩልነት የግንባር ሥጋ በመሆን ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሲኖዶስ በሚያደርገው ጉባኤ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝ ማድረጉ የቤተክርስቲያን ልዕልናን የሻረና የሃገሪቱን ክብር የሻረ ድርጊት መሆኑን አስታውቀዋል። አቡነ መቃሪዎስ እንዳሉት እነ ስብሃት ነጋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና አማራን አከርካሪውን መተናል በማለት የተነሱበትን መርዘኛ ድርጊታቸው አያካሃዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከዚህም በማያያዝ አቡነ መቃሪዎስ ሲያብራሩ “…..ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓት ጉባዔ ላይ የመንግሥት ተወካይ ጨርሶ መግባት የለበትም። የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን የሚካሄድበት፣ሚስጢረ ቤተክርስቲያን የሚነገርበት፣ ስለ ቤተክርስቲያን ልዕልና ውይይት የሚካሄድበት ነው። በዚህ መንፈስ ቅዱስ በሚመራው ጉባኤ ላይ በምንም ዓይነት ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት እንዲሁም በበፊቱም መንግሥት እንዲህ ዓይነት ነገር ተደርጎ አያውቅም። በመላው ዓለም በሚገኙ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም አይተን አናውቅም ….” ብለዋል። ብጹዕ አባታችን በዚህ ጉዳይና በአጠቃላይም ወያኔ በሾማቸው የካድሬነት ሥራ በሚሰሩ ፓትርያርክ፣ ጳጳሳት፣ ካህናትና ሌሎችም እንዴት የቤተክርስቲያን ሥርዓት እንደተጣሰና ቤተክርስቲያኒቷም በታሪክ ታይቶባት የማያውቅ ውርደትና መከራ ውስጥ መግባቷንና መፍትሃውንም ጭምር አስመልክተው በኢሳት የሰጡትን ውይይት ይከታታሉ።

No comments:
Post a Comment