Tuesday, January 24, 2017

አማራውን ፍለጋ (መስቀሉ አየለ)

የአማራው ህብረተሰብ በታሪክ አጋጣሚ እንደ ሎተሪ እጣ ከወጣላቸውና ከበታችነት ስሜት (የኢንፌሪየሪቲ ኮምፕሌክስ) ፣ ኤክዞኖፎቢያ፣ ወዘተ መገለጫ የሆነው የዘረኝነት ወይንም ስሙን ሲያጣፍጡት ብሄርተኝነት የሚሉትን የስነልቦና ቀውስ አምልጦ የወጣ፣ አማራዊነትን በኢትይጵያዊነት ተክቶ ማሳደግ (ማኒፌስት ማድረግ) የቻለ ህዝብ ነው። ይሕ መታደል ነው። ከማንነት ወደ ሰውነት ማደግ ነው። ከመንደርተኝነት ወጥቶ ዩኒቨርሳል የሆነ መገለጫን ገንዘብ ማድረግ ነው። ይህንን ነገር ከታደሉት በአለም ውስጥ ካሉት በጣት የሚቆጠሩት ህዝቦች
፩) የሰርብ ህዝብ፤
፪) የራሽያ ህዝብ፤
ይኽ ህዝብ ከናፖሊዮን እስከ ናዚ… ከናዚ እስከ የዘመኑ የአሜሪካ ኒዮ ኮንሰርቫቲቨ በየዘመኑ የተነሱትን አምባገነኖን ልክ ያስገባን በምን አይነት ከሰማይ ባለ መከራ ተፈትኖ ያልተሰበረ ህዝብ ነው። ፫ የእንግሊዝ ህዝብ፤ የመጫረሻው ኢምፓየር ሆኖ መውጣቱ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ከተፈጠረበት ዘመን ጋር መግጠሙ አመች ሁኔታ ፈጥሮለት አሁን አለማችን የምትመራበትን Time & Space መለኪያዎች ወጥነት ባለው መልኩ ቅርጽ መስጠታቸው; የአለም አገሮችን ካርታ መወሰናቸው; ፣ቋንቋቸውን አለም አቀፍ ማድረጋቸው፤ እንዲሁም አለማቀፋዊ ተቁዋማትን በመልካቸው ቀርጾው በማለፋቸው የራሳቸውን አሻራ በመጣል የተሳካላቸው በመሆኑ ይኽ ነገር ዛሬ ድረስ ለማንም በሚታይ መልኩ የፈተረላቸው ሳይኮሎጅካል አድቫንቴጅ የማይካድ ነው።

No comments:

Post a Comment