የሕወሓት ደህንነት ቢሮ በሃገሪቱ ለአገዛዙ አደገኛ የሆነ የሕዝብ ተቃውሞ እንደሚነሳ አረጋግጫለሁ አለ። ( ምንሊክ ሳልሳዊ)
የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በሃገሪቱ ዙሪያ ባሰማራቸው ጆሮ ጠቢዎቹ አማካኝነት በሰበሰበው መረጃና በሰራው ሪፖርት መሰረት ከፍተኛ የሆነ ለ አገዛዙ አደገኛ የሆነ የሕዝብ አመጽ ይነሳል ሲል አስቀምጧል። በዚህ ሰሞን የሕወሓት ሰዎች በቡድንና በጋራ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ከተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ ግማሽ የሚሆነው የኢሕአዴግ ካድሬ ሕወሓት ስልጣኑን እንዲለቅና የበላይነቱን እንዲያጣ ከሕዝቡ ጎን ተሰልፎ እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
የኢሕአዴግ ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ስበቦችና በማግለያ መንገዶች ፈጥኖ ለማኮላሸት እቅድ ለመንደፍ ያሴረው የሕወሓት የደሕንነት ቢሮ ሕዝቡ በፍጹም ከፍራቻ ውጪ በሆነ ድፍረት አገዛዙን ለመጣል ቆርጦ ተነስቷል ሲል በሪፖርቱ መጋፈጥ የማንችለው እውነት ላይ ደርሰናል ሲል ኣስረግጦ ያትታል። ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ዜጎች ከቤተሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆነ ሁሉ በአገሪቱ ያለውን ችግር መረጃ ያደርሳሉ ያለው ተቋሙ ወታደሮችን በካምፕ ገድበን ከመረጃ ለማራቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ሲል ይገልጻል።
በዲያስፖራው በኩል ያለው ኣስፈላጊ ስራ በመሰራት ላይ ሲሆን በታቀድለት መልኩ እየሄደ ነው የሚለው ሪፖርት የዲያስፖራውን ፖለቲካ ታማኝነት ለማሳጣት የተጀመረው ተግባራዊ ስራ ጥሩ ውጤት ያሳያል ሲል ገልጾ ምስጢራዊ የሆኑ ግንኙነቶች በተጠናከረ መልኩ ከዲያስፖራዎች ጋር በማድረግ መስመር የያዘ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኣስቀምጧል።
ከምዕራባውያን ጋር ያለው የትብብር ስራ ከመንግስታችን ትንፋሽ ጋር የተያያዘ ስለሆነ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ምእራብያውያኑን ለማስደሰትና ጫናቸው ከምላሳቸው እንዳይዘል ጥሪ የዲፕሎማቲክ ስራ መሰራቱን ጠቁሟል።እርዳታና ድጋፍ ቀንሰናል ቢሉም በተዘዋዋሪ ይረዱናል የሚለው ሪፖርቱ ቀጣዩን ለመጠቆም በይደር ሲያስተላልፍ የሕወሓት ስብሰባዎች በየቦታው በተዋረድ እንደሚቀጥሉ ምንጮቹ የገለጹ ሲሆን በዚህ ሰሞን በሙስና ስም ከተመቱት በተጨማሪ አስጊ የሆኑና ከሕዝብ አመጽ ጀርባ አሉ የሚባሉ በተራቸው የኣገዛዙን ጡጫ እንደሚቀምሱ ተገልጿል
No comments:
Post a Comment