Thursday, January 26, 2017

የአሉባልታ አስማት የሆነው የወሬው ሰርከስ ደርቷል – ቆንጅት ስጦታው



– ሐሜቶቻችንና አሉባልታዎቻችን እኮ በሙያተኛ ቢጠኑ ከነዳጅ የበለጠ ስንት የመፍትሔ ሐሳብ ይፈልቅ ነበር፧የማይሰማ የለም ፖለቲካ እንደ ማስቲካ ጣእሙ ሲያልቅ አኝኮ አኝኮ መትፋት በማስባል በመባባል የአሉባልታ አስማት የሆነው የወሬው ሰርከስ ደርቷል አሉ። መቀጣጠል፣ መንጠላጠል ከዚያ ደግሞ መነጣጠሉና መነጣጠቁ የባሰብን ለዚያ ሳይሆን አይቀርም። እሰይ አበጀን፦ ወሬና አሉባልታ ባይኖሩልን ኖሮ፣ ኑሮ እንደሚሰነዝርብን የከባድ ሚዛን ቡጢ ዘመን እንሻገር ነበር፧ እንኳን የ‘ትራንስፎርሜሽን’ ተራ ቁጥር ልንቀያይር፧ የምሬን እኮ ነው።
እናላችሁ ሰሞኑን በማለት፣ በመባልና በማስባል ሰንጠረዥ ጨዋታ ብዙ ስሰማ ነፍሱን ይማረውና ‘አልን ተባልን አስባልን’ ያለው ድንቅ ጸሐፊ ፅ አለኝ። መቼም ነፍስ ይማር የምንለው ሰው ቁጥር፣ ከዋጋ ግሽበቱ ጋር የእናት ልጅ ሆኗል መሰል። ደግሞ ‘ዲ፡ኤን፡ኤ’ እናስመርምር ብላችሁ በቋፍ ያለውን ሥጋ ለባሽ ‘ዴሊት’ እንዳታስደርጉት አደራ። “ጥናቱ ቀርቶብኝ ወሬ በጋቱኝ” አለች አሉ። እንጃ ማን እንደሆነች።
የአሉባልታውያንን ማንነት ከምንመረምር የሚያምርብንና የምንችለውን ‘አሉን’ ብንመረምር ይኼን ጊዜ ስንት ደህና ነገር ይገኝ ነበር። አንዴ የባሻዬ ልጅ፣ “ነዳጅ ካላወጣን በስተቀር ችግራችን አይፈታም ብለው የሚያስቡ ሰዎች ይገርሙኛል፤” አለኝ። ‘የማይገርምና የማይራገም ሰው አለ፧’ እያልኩ በውስጤ፣ “አንተ ምን ትላለህ፧” ስለው፣ “ሐሜቶቻችንና አሉባልታዎቻችን እኮ በሙያተኛ ቢጠኑ ከነዳጅ የበለጠ ስንት የመፍትሔ ሐሳብ ይፈልቅ ነበር፧” ነበር ያለኝ።
ምንጭ እየደረቀ እሱ ከአሉባልታዎቻችን መፍትሔ እንዲፈልቁ ያስባል። አይ አብዝቶ መማር ግን አንዳንዴ። እኔማ ምን እለዋለሁ ያው እንኳን እሱ የመረጃና የደኅንነት ቢሮ ሳይቀር ሰርጎ በማይገባበት በልቤ አዳራሽ “የደላው ሙቅ ያኝካል” ብዬ ተረትኩበታ፦ “ባልተርት ተረትነቴን በምን አስታውሰው ነበር፧” ነው ያለችው፧ ኧረ እኔ የት አውቄያ፧ ሁሉን አዋቂ ነኝ እንዴ፧ ስምንተኛው ሺሕስ ስምንትን ሲያይ ባሰበት መሰል !!!

No comments:

Post a Comment