Wednesday, January 18, 2017

ግንቦት ሰባት ሔኖክ የሺጥላን በአማላጅ በነተሾመ ተንኮሉ አስለምኖ ማስቆሙ ሲታወቅ ሔኖክ ይህን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።



ግንቦት ሰባት ሔኖክ የሺጥላን በአማላጅ በነተሾመ ተንኮሉ አስለምኖ ማስቆሙ ሲታወቅ ሔኖክ ይህን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ነገሮችን ግልፅ ስለማድረግ
ላልተወሰነ ጊዜ ከፌስ ቡክ እራሴን ለማግለል በመወሰኔ የተለያዩ አስተያየቶችን ተቀብያለሁ። ጥያቄያቸውን እንዲሁ እንብቤ የማላልፈው ፥ በጎንደር እና ጎጃም የአማሮች ህዝዝባዊ የከተማ አመፅ ሰሞን መረጃዎችን ሲሰዱልኝ የነበሩ ምርጦቹ የጎንደር ወጣቶች « ኄኖካችን ሃሳብህ ይብራራ ፥ እኛ ይገባናል ሌላው ግር እንዳይለው » የሚል ነገር ጠቁመዋል። በዚህ በአማሪካን ሃገር በዳላስ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወዳጄ « ኄኖክ የሺጥላ በነ ተሾመ ተንኮሉ በኩል ግንቦት ሰባት ላይ ያለውን ግጭት እንዲያቆም ተጠይቆ ነበር ለዚያ ነው ከፌስ ቡክ ራሱን ያስገለለው » እያሉ ነው ፥ ይህንን ለህዝቡ አሳውቅ ብሎኛል ።
ሌሎች ብዙሃን « ተስፋ የቆረጠሕ ያስመስልብሃል » ይህ እንዳልሆነ ሰው እንዴት ይወቅ ( ይረዳ ) የሚል ጥያቄ አቅርበዋል ።
በመጀመሪያ ላልተወሰነ ጊዜ ነው ያልሁት። ሁለተኛ ግንቦት ሰባትን በተመለከተ ያለኝን አቋሜን ሊያስቀይር የሚችል ነገር ሊኖር አይችልም ! ግንቦት ሰባት የማይረባ ፥ ህልውናውን በአየር ላይ የገነባ ( አየር ወለድ ) እና ነጣቂ ድርጅት ስለመሆኑ ደግሜ ደጋግሜ ፅፌያለሁ። ከዚያ ባለፈ በድርጅቱ ውስጥ ካሉ የአማራ ልጆች ጋር ቀን እና ሌሊት ያለ እረፍት ውይይት አድርጌያለሁ። ውጤቱን ወደፊት በግንቦት ሰባት አቋም እና ቋቋም ላይ የምናየው ነው ። አፌን ሞልቼ « ስራዬን በሚገባ ሰርቼያለሁ ! » ማለት እችላለሁ! መሬት ላይ አስተኝቼ የረገጥሁት ሃሳብ እና ድርጅት ስለምን ሲባል ነው ሃሳቤን የሚያስቀይረኝ ! ግንቦት ሰባትን እንደ ምክንያት አታንሱት ! እርሱት ! እርግጥ ከነ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ጋር ጤናማ ውይይት አድርገናል ፥ በውይይቱም የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት ጀነራሎች ፥ ሻለቃዎች እና በከፍተኛ ስልጣን ላይ ከነበሩ መኮንኖች ጋር ውይይት አድርገናል። ኤርትራን በተመለከተም ጥያቄ አቅርበው ፥ ለጥያቄያቸው የሚያቁትን ታሪክ መልሼ ውይይቱ ተጠናቋል። ፍቃዳቸው ከሆነ ውይይቱ ስለተቀዳ ለህዝብ ቢተላለፍ እውነቱን መረዳት ይቻላል ባይ ነኝ። ስለዚህ እነርሱም እንዲህ ያለ የድለላ ስራ ሊሰሩ አልመጡም ፥ እኔም ልደለል የምችል ሰው አይደለሁም !
በተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ላላችሁ ወጣቶች ፥ ይህ ትግል ተጀመረ እንጂ መቼ ተጨረሰ። እየተነሳን ባለንበት ሰዓት ስለ መውደቅ የማስብም ሆነ የማወራ ሰው አይደለሁም! ትግሉ ግን የተለየ አካሄድ እንደሚያስፈልገው እሙን ነው። እንዴት እንቀጥል የሚለውን ማሰብ ያስፈልገናል ባይ ነኝ።
ስለዚህ ህዝብን ከማንቃት ባለፈ ፥ የተለየ ስራ ለመስራት የምንችል ከሆነ ፥ ሙቅ ከማሞቅ በተጨማሪ ፥ እስቲ እንሞክረው ብለን ነው። ስለዚህ ለጊዜው ከፌስ ቡክ መራቅ ጥሩ ነው ብዬ የወሰንሁት። በተጨማሪም ለማናቸውም አይነት ጥሩ ነገር መጥፎ መልስን መመለስ እንደ ስራ የተያያዙትንም ሰዎች ከነ መጥፎነታቸው ከሚመጥናቸው ጋር ይውሉ ዘንድ « የቄሳርን ለቄሳር » ማለቴም ጭምር ነው !
ከአማራ ትግል ፥ አይደለም ቦሃ እንደሆነ በታወቀው ግንቦት ሰባት ፥ አይደለም ህዝብ በጠላው ወያኔ ፥ በተፈጥሯዊ ምትሃትም አልገታም ! እኔ አማራ ነኝ ስል ዝም ብዬ አማራ ነኝ አላልሁም ! እኔ የገብርዬ ልጅ ነኝ ! እኔ የቴዎድሮስ ልጅ ነኝ ! ዝም ብዬ የምሰጠው እጅ የለኝም ! ተስፋ የምቆርጥ እንዳልሆንሁ ጠላቶቼ በደንብ ያውቃሉ!!!
ስለዚህ ጉዳዩን እንዲህ ባለው ቁና ስፈሩት! ተመልሼ እስክመጣ የአማራ ወጣቶች ትግሉን እንደምትቀጥሉ እና እንደምታቀጣጥሉ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ !
የትግራይ ህዝብ ለትግሬ ወያኔ የሚሰጠውን ድጋፍ ሳይቆም የኔ ብዕር ቀለም አይደርቅም! የኔ ደም አይቀዘቅዝም ! ፀቤ ከነማን ጋር እንደሆነ በደንብ የምረዳ ሰው ነኝ ! ፀቤ በሰው መልክ ከተሰሩ መርዞች ጋር እንደሆነ ላንድ አፍታም አልዘነጋውም !
በመጨረሻም እጅ እጅ በሚለው ትምህርቱ (የትምህርት ብልጭታው ) የማውቀው የግንቦት ሰባቱ ዶ/ር ታደሰ ብሩ « በፌስ ቡክ ላይ ጥሩ ጦማሪ ስለመሆን የፃፈውን ሳነብ « ሰው እንዴት ራሱ መፃፍ ሳይችል ስለ ጥሩ አፃፃፍ ያወራል ፥ የትኛውስ እውቀቱ እና ክህሎቱ ነው እሱ ስለ ሶሻል ሚዲያ አፃፃፍ ዘዬ አስተማሪ እንዲሆን ያደረገው ? አዎ ከእንደዚህ አይነት አይን ያወጡ ፥ ውሃ የማያነሱ ፥ እንቅልፍ አምጪ ምክሮችም መራቅ እፈልጋለሁ።
ኡመር ደናክል ( ቤተሰቦቹ የአፋር ሰዎች ስለሆኑ ነው ) የሚባል የጎረቤታችን ልጅ « አትምከሩኝ እኔን ምክር ነው ያበላሸኝ » ይል ነበር ። ደደብ የሚያደርግ ምክር ምን ይሰራልናል !
ማሸነፋችን ስለማይቀር እናሸንፋለን አልልም !
ኄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment